ቀጨኔም ጉልበት አግኝታ – ማሞ ማስረሻ

 
የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል “ተጠና” የተባለውን ባለ 46 ገጽ ወረቀት አንብቤ ጨረስኹ። “ለካንስ ያለነገሩ አይደለም ሲያዝቃዠኝ የነበረው” እንደምትለው እናቴ – ለካንስ ያለነገሩ አለነበረም በጠዋት “መሳቁን ይስቃል ጥርሴ መች አረፈ፣ ልቤ ነው በጣሙን እጅግ ያኮረፈ” የሚለውን የጥላሁንን ዜማ ለብድ ለብድ ያሰኘኝ።
 
ምን አግኘቼ መሰላችሁ፦ እትብቴ የተቀበረባት የሰፈሬ ስም ከሰንጠረዥ መሀል ዱቅ ብላለች። ያው አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት “ቀጨኔ” ሲባል ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው “ቡዳና ሰው ከመብላት ጋራ” የተያያዘ ታሪክ ነው። እኔም ብዙዎች ስለ መጨቆን፣ ስለ መገለልና ስለመጨፍለቅ ሲያወሩ ቀጨኔን እያሰብኹ እጄን ባፌ ላይ ጭኜ የትዝብትና የስላቅ ሳቅ እስቃለሁ።
 
እና “ጥናቱ” ምን ቢል ጥሩ ነው፦ ቀጨኔ በኀይል ስሟን ያገኘቸው ከዶቢ ቀምታ ነው። ቀጨኔም ጉልበት አግኝታ የመንድር ስም ቀምታለች ተባለ።
 
ለነገሩ
 
“ሰው ሁሉ እንዳይኾን ፍጹም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ”
 
የሚለውንም ዜማ ሰምቻለሁና እጽናናለሁ።
 
እንግዴህ ይኼ የአዋጅ ረቂቅ ተግባራዊ የሚኾን ከኾነ – የቀጨኔ ልጅ መኾኔ ይቀርና “የዶቢ ልጅ” ልባል ነው። The Shift-delete politics!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.