ኦኤምኤንን እንዴት ታዘባችሁት;እባካችሁ ንቁ! – ሰርጸ ደስታ

እኔን እንምረዳው ሕዝብ በቀላሉ እየተዘወረ ነው፡፡ ሰሞኑን  ኦሮምያ በአዲስ አበባ የሚኖረውን ጥቅም አስመልክቶ የተነበበው ግርድፍ ጽሑፍ ትልቅ ርዕስ ሆኗል፡፡ የፅሑፉ ምንጭ ባይታወቅም ማለት ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ የሥራችን ወጤት ነው ብለው ጮቤ የረገጡትን ያህል አደለም የኦሮሞ ሕዝብ ውርደት ነው ያሉም አሉ፡፡ አንዳንዶች የሰነዱን መሠረታዊ ችግር በዝርዝር እያነሱ ሞገተውታል፡፡ ኦኤም ኤን የተባለው ሚዲያ ልዩ መነጋገሪያው አደርጎ መቅረቡንም ብዙዎች ተመልክተናል፡፡ በኦኤም ኤኑ የራባዶሪ ዝግጅት ሲወያዩ ያየናቸው ገልሰቦች ነገር ግን እኔን ያልገቡኝ አልመሰለኝም፡፡ በመጀመሪያ ግን ፕ/ሮ ሕዝቅኤል የተባለው ግለሰብ እንምሁር ማውራት ቢችል መልካ ነበር፡፡ ምሁር አመክንዮአዊ ትንታኔ ይሰጣል እንጂ ቀድሞ በጥላቻና ድንፋታ መልክ መናገር ከጀመረ ጥሩ አደለም፡፡ ፕሮቶኮል የሚባ ነገርም ደግሞ አለ፡፡ ይህን ለሕዝቅኤል ነው፡፡ ያደመጠኩለት ቃለምልልሶቹ ሁሉ(ሌላም ጊዜ ማለት ነው) ጥሩ አደለም፡፡ እዴሜም አካዳሚክስም እንዲሁም ኤክዝፖዠር ያንጻል የሚል ግምት ስላለኝ ነው፡፡

ወደ ጉደዬ ስገባ እንኔ እንደገባኝ ሰነዱን የጻፉት የኦሮሞ ፈርስት ቡድኖች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ የወያኔ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ናቸው እላለሁ፡፡ አስተውሉ አርሲ አኖሌ ሀውልት ለመሥራት ያንሳሳው ማን ነው; ኦሮሞን በጀምላ ከእኛ ሌላ ማንም የሚመለከተው የለም እያለ የሚደነፋው ማን ነው;   እርግጥ ነው ዛሬ ሚዲያውን ስላላቸው የልባቸውን ሰርተው እንደገና ሌላ ውዥንብር ለመፍጠር አቅም ኖሯቸዋል፡፡ ሕዝቡም በተምታታ ወሬ ስለባዘነ አብሮ ይዋልላል፡፡ ረጋ ቢሎ ላስተዋለው ግን እነዚህ ግለሰቦች ምን አይነት ቁማር በሕዝብ ላይ እንደሚጫወቱ ለመረዳት ብዙም ጥልቅ ምርምር አይጠይቅም፡፡ ጽሁፉን የዘጋጁት የኦሮሞ የጀዋር ቡድን እንደሆነ ብናስብ የተሳሳትን አይመስለኝም፡፡ ጽሁፉ በቀጥታ ከዚኅ በፊት የጀዋር ቡድን እንደሚያወራው ነው የተዘጋጀው፡፡ ገና እንደወጣ እንደልዩ ስኬት ሙገሳን ተችሮት ነበር በዚሁ ቡድን፡፡ እየቆየ አስተዋይ ሰዎች መተቸት ሲጀምሩ ነው እንደገና ኦኤም ኤን ዋና ተቺ ሆኖ የተገኘው፡፡ ሌባ ሲያባርሩት እሱ ራሱ ሌባ ሌባ እያለ እንደሚሮጠው ነው የሆነው፡፡ በጣም የወረደ ዝባዝንኬ ነው ተብሎ ስለተተቸ ነው ይሄን ዝግጅት ራሳቸው የዘጋጁት፡፡ አሪፍ ነው ቢባል ኖሮ ምን ሊሆን እንደሚችል ገምቱ፡፡ የእኛ ውጤት ነው ይሉን ነበር፡፡ አሁን ግን እንደሌለው ጊዜ ኦሮሞ ሁሉ እኛ እንደምናስበው ካልሆነ የሚለው ጊዜ ለነጀዋር የረፈደ መሠለኝ፡፡ ደግማችሁ ራባዶሪን አድምጡት፣ በማህል ሳይቀር ሕዝቡን ለመሸወድ ምን እንደተነጋገሩ ትታዘባላችሁ፡፡ በመሕል አንድ 3-4 ደቂቃ ቆይተን እንመለሳለን በለው የተመለሱበት ውይይት ራሱ በፊት ሲያወሩት ከነበረው ቶን ይለያል፡፡  በሕዝብ መካከል ባልተፈጠረ ታሪክ የጥላቻ ሀውልት ለማቆም እንደተሰራበት ጊዜ አደለም፡፡ ኦሮሞን ሁሉ በአንድ ቋት ጨምሮ በእኔ ብቻ አመለካከት ካልሆነ ኦሮሞ አደለህም የነፍጠኛ ቅጥር ነህ እያሉ ማሸማቅቅና ሕዝብን ከማንነቱ አምክኖ መነገጃ ማድረግ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ አሁን ሁሉም በየማንነቱ ማሰብ የጀመረበት ወቅት ነው፡፡ በጅምላ ኦሮሞ እየተባለ ሕዝብ ራሱን እንዳያድን ሆኗል፡፡ መጨረሻም የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ መበት ሁሉ በሙስሊም አክራሪዎች እጅ መውደቁ ነው፡፡ ለእነጀዋር የኦሮሞ ሕዝብ የሰጠውን ድጋፍ ለመረራ ሰጥቶት ቢሆን ዛሬ ላይ እንዲህ የመከነ አይሆንም ነበር፡፡ ምሁር ነን በሚል በኦሮሞ ሕዝብ ስትነግዱ ብዙ ዘመን ተቆጠረ፡፡ ምን አልባት የሚያውቁት እውነት ይኖራል ብለን መስማት ጀምረን ነበር፡፡ እየቆየን ስናስተውል ታሪክም ሳይንስም ሳይሆን የጀዋር ጋሻ ጃግሬ የኦሮሞ ምሁር ተብዬዎች ጥላቻን በሕዝብ መካከል በመፍጠር የኦሮሞን ሕዝብ ለእነሱ መጠቀሚያ ባሪያ አድርገውት ከሌሎች ጋር አንደም ሕብረት እንዳይኖረው ሆነ እውነተኛ ምሁርነታቸው፡፡

አሁን ላይ ሁሉም ራሱን ይጠይቅ፡፡ ወለጋ ጂጂ በተባች ሴት ተወክሏል፣ አርሲና ደቡም ምስራቅ ጀዋር ራሱ አለ ሸዋ የጎበና ዳጬ አገር ስለሆነ ውክልና የለውም ግን ስለራሱ አያገባውም፡፡ ጀዋር ነው የሚወስንለት፡፡ ሰሞኑን የሸዋ ሕዝብ እራሱን ችሎ ክልል እንዲኖረው ሰዎች ሀሳብ እየሰጡ ነው፡፡ ግልግል ነው፡፡ በእርግጥም በወሮበላው የወያኔ ዘመን ሸዋ አማራው ነፍጠኛ ኦሮሞው ጎበና ዳጬ እየተባለ ምንም አይነት አድል ሊሰጠው አልቻለም፡፡ ግን እኮ ወያኔን አሁንም ያርበደበዳት ሸዋ ነው፡፡ አምቦና ጊንጪ የጋደላል ጀዋር እያቀነባበረ በኦሮሞ ሥም ለራሱ ለገበያ ያውላል፡፡ ሕዝቅዬል አዲስ አበባ ውሥጥ የነበሩ ኦሮሞዎች ተገፍተው ተጥለው ነው ከተማዋ የተመሰረተችው ሲል ነበር፡፡ ስለዚህ ቦታ የሚመለከተው ግን ከሆነም ነዋሪዎቹ ናቸው፡፡ መጠየቅ ከአለባቸው የሸዋ ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ እናንተ አያገባችሁም የጎበና ዘር እያሉ በኦሮሞ ሥም አጅሎ ስለፊንፊኔ ማውራት ስህተት ሆኖ ሊታያቸው አልቻለም፡፡ እስኪ እውን ሪፍረንደም ይሰጥ ቢባል በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሌ ከተሞች አዲስ አበባ ሥር መጠቃለልን እንደሚፈልጉ አልጠራጠርም፡፡ ይህ በደህናው ቅን የሚያስቡት ነው፡፡

ሰሞኑን ሸዋን እንደክልል ማዋቀር እንደመፍትሄ እየነተሳ ያለው ሀሳብ በጣም ወድጄዋሁ፡፡ ዛሬ የተነሳው ሸዋ ራሱን ችሎ የተዳደር ቢባል በሸዋ የሚኖሩ ሁሉ እፎይ ተገላገልን እንደሚሉ አልጠራጠርም፡፡ ሸዋ ሁሉንም ነው፡፡ ጉራጌው ኦሮሞው አማራው ሌላውም፡፡ የተነሳው ሀሰብ ከቀጠለ በሸዋ ምክነያት ያጣንው ኢትዮጵያዊነታችንን እናገኘዋለን፡፡ ሸዋ ራሱን ከቻለ አንተ ኦሮሞ ነህ አንተ አማራ ነህ ምናምን ይቀራል፡፡ ኦሮምኛ ለኦረሞ ስለሚያስፈልገው ሳይሆን ለሸዋ ስለሚያስፈልጋት ሁሉም ሸዌ በደስታ ይማረዋል፡፡ ጉራግኛም ከአስፈለገ እንደዛው፡፡ በአውሮፓ አገሮች እንደምናየው ብዙዎች የፈረንሳይ የሰፓኒሽና  የኢንጊሊዘኛ ቋንቋ ያስተምራሉ፡፡ በዚህ መልኩ ሸዋ ወልኬሳ ሆና በህብረብሄርነት ታብባለች፡፡ እነጀዋርም በዚያን ጊዜ እዛው አርሲያቸው ይቆማሉ ወይም ከዛም ይወገዳሉ፡፡ ምክነያቱም ሸዋ ሀሳቡን ያነሱት እንሙሏት ከገነቧት ማን በጎጥ ጉሮኖ ይኖራል፡፡ አዲስ አበባም ባለቤት የላት ትሆናለች፡፡ በእርግጥም ሸዋ ለሌሎች ኖረ እንጂ ብዙ ዘመን ተጎጂ ነበር፡፡ ለመሆኑ የትኛው የሸዋ ሕዝብ ነው ያልተጎዳ፡፡ ሸዋ አማራው በሉት ኦሮሞው የረባ ትምህርት ቤት እንኳን የለውም፡፡ ለተነሳው ሀሳብ ሌሎች ሳይቀሩ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አልጠራጠርም ከጀዋራዊያን በቀር፡፡

በአጠቃላይ ለዚህ ሁሉ እየዳረገን ያለው በብሔር ሥም እያጨቁን ለራሳቸው መጠቀሚያ ህዝቡን የንግድ ዕቃ እያደረጉት መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁሉም የተሻለውን ቢያስብ ይሻላል፡፡ ከማይተዋወቀውና ከማይገናኘው ህዝብ ጋር በቋንቋ አንድ ነህ እየተባለ በግድ ነው የተጫነበት፡፡ ሁሌም እለዋለሁ የሸዋ ኦሮሞ ከጉራጌና ሰሜን ሸዋው አማራ ጋር እንጂ ከባሌ ኦሮሞ ጋር ምን አገናኘው፡፡ እንደእውነቱ በዘርም በባሕልም ህዝቡ አንድ ነው የተለያየ ቋንቋ ከማውራቱ በቀር፡፡ ወለጋስ ከሀርጋር እንዴት ይገናኛል፡፡ ቋንቋ ካልን እኮ ሱማሌ ሁሉ የሚያወራው ሱማልኛ ነው፡፡ እንዴ አረብ በሙለ አረብኛ ያወራ የለም እንዴ; ደም ከውሀ ይወፍራል፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በደም በቅርብ ከአለው አጎራባቹ ጋር በጣም ይዛመዳል፡፡  ወደ ወሊሶ ብቅ ያለ ሕዝቡ ጉራጌ ነው ኦሮሞ ብሎ ግራ እስኪጋባ ያስተውላል፡፡ ፍቼስ ብንሄድ ኦሮሞ አማራ የሚል መታወቂያ ስለሰጡት ምን አልባት በመታወቂያ ነው፡፡ ይህ ሁሉም ሕዝቦች ጋር ያለ ነው፡፡ ለሁሉም ግን ወያኔ የሰራችልንን ሕዝብን በአንድ ማጨቀር ጉሮኖ መጣስ አለብን፡፡ የአማራው ጀዋራውያን ቨርሽን የአማራ ብሄረተኛው ቡድንን አስተውሉት፡፡ ዋና አቀንቃኞቹ ወያኔ ያሰለጠነቻቸው ቅጥረኞች ናቸው፡፡ ከድሮ ጀምሮ የምናውቀው ሰውን በአገሩ እንጂ በዘሩ አልነበረም፡፡ ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ሸዌ ነው፡፡ ከዛም ወርዶ እንዲሁ ነው፡፡ ቡልጋ፣ ሰላሌ፣ አቢቹ፣ ጉለሌ፣ መርሀቤቴ፣ ይፋቴ ነው የሚባለው ሕዝቡ፡፡  ሕዝብን ማጨቅ ሲቆም የሕዝብ ትርጉሙ ይገባናል፡፡ በኦሮሞ ሥም እየታጨቀ ቦረናም ቦረና ባሌም ባሌነቱን ሸዋም ሸዋነቱን ጣለ፡፡ ሥለዚህ ማንነት የለሌው ህዝብ ማንም ይዘውረዋል፡፡ አርሲ በኦሮሞ ሥም በጅምለ መነገድ ተያያዘው፡፡ ይህ መቆም አለበት፡፡ ድሮ እኮ ኢጆሌ ጂማ ሲማል አማራ ኦሮሞ ምናምን አይታወቅም፡፡ ኢጆሌ ባሌም ነበር፡፡ ዘፈኖቻችን ሳይቀር በግድ ታጭቀው ይህን የሚያህል ግዙፍና በጣም ውስብብ ባሕል የአለውን የአሮሞ ሕዝብ በኦሮሞ ሥም በጅምላ ይዘፈንለታል፡፡ ቀጥሎ የአማራ ብሔረተኞች የሚያሰሙን ዘፈን እንግዲህ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ቡልጋ ምናምን ይቀርና የአማራ ቆንጆ ሊሆን ነው፡፡ ነገሩ አሁን እየጀመሩት ነው፡፡

ሕዝቦች እርስ በእርስ እንዳይቀራረቡ፣ ገደል ፈጥረውለት የሕዝብ ጥያቄ ነው ይሉናል፡፡  አሁንም የአዲስ አበባም ሆነ የሌሎች አካባቢዎች በሚኖሩባቸው ሕዝቦች ይሁንታ መወሰን አለበት እንጂ የማይመለከተው እየመጣ ለሚኖረበት ሕዝብ ሸክም መሆን የለበትም፡፡ የሚገርመው ሲጀምር ሕገ ምንግስት የተባለውን የጥንቆላ ዶሴ ያዘጋጁት ኦነግና ወያኔ ናቸው እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው አደለም፡፡ አዲስ አበባን ከጅምሩም በሕገመንግስት ውስጥ ማስገባቱ ውንብድና ነበር፡፡ አዲስ አበባ ከክልልም በላይ የፌደራል መንግስቱም መቀመጫ ነው፡፡ ባይሆን ፌደራል ምንግስቱ ለአዲስ አበባ ክልል ልዩ ጥቅም መሥጠት ግዴታው ነው፡፡ ክልሉ በኦሮሚያ መሀል ስለሚገኝ ብሎ ለኦሮሚያ ጥቅም ይገባዋል ማለት በራሱ ስህተት ነበር፡፡ ሕገ መንግስት ተብዬው እኮ እያለ ያለው አዲስ አበባ ከኦሮሚያ መረት ተከራይታ ነው ክልል የሆነቸው ነው፡፡  በብዙ አገሮች ከተሞር ራሳቸውን ችለው ክልል ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ በጀርመን የበሬመን፣ የበርሊን፣ ሐምቡርግ የመሳሰሉት ከተሞች ራሳቸውን ችለው ክልል ናቸው፡፡ አሁን ለሁሉም መፍትሔ የሚሆነው አዲስ አበባን ለሸዌዎቹ ሰጥቶ፣ እንደድሮው በየክፍለሀገራችን መኖር ነው፡፡ አየንው 26 ዓመት ህዝብን በማጨቅ ለከፋፍለህ ግዛው እንዲመቻት በዘር እያነታረከች ለምትኖረው ወያኔ ነው የጠቀማት፡፡  ለመሆኑ ግን ሀረሪ የሚባለው ክልል አሁንም አለ;

ሌላው አሁን ሳላነሳ የማላልፈው፣ የታሰሩትን ወገኖቻችንን ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ እንደሕዝብ አንድ ነኝ ከአለ በተለይ የሚሰማችሁ ዲያስፖራ ኦሮሞ ሆንክ ሌላ በአንድነት ለሕዝብ መስዋዕት እየሆኑ ስለሉት ድምጽህን ከፍ አድርግ፡፡ በአሁን ጊዜ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ የወገኖቻችን ከሥቃይ መላቀቅ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ጉዳይም ሆነ ሌላ ከእንግዲህ ወያኔ በምትጠው ይሁንታና ክልካይነት ሳይሆን በራሳችን ጊዜ የሚሆነንን እናደርጋለን፡፡ የጉዳዩን ባለቤቶች አሸባሪ ብላ አስራ ወያኔ ከእነጀዋር ጋር ውል አትፈራረምብን፡፡ እነ በቀለ ገርባ እኮ የታሰሩት የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ደሀ ገበሬዎች እያፈናቀለ ነው ስላሉ ነው፡፡ ጥያቄ ለአዋጅ ከበቃ እነሱ የመጀመሪያዎቹ ረቂቅ አቅራቢ በሆኑ ነበር፡፡ ኦሮሞን አምክነንዋል ብለው ስለሚያስቡ ነው ጀዋራውያንና ወያኔ እንዲሀ እንካ ከረሜላ ብለው እንደሚያታልሉት ሕጻን የዛሬ 21 ዓመት በህገ መንግስት ያስገባሁልህን አጸደቅኩልህ በዚህ ላይ 15 በመቶ ኮንደሚኒየም፣ የኦሮምኛ ትምህርት ቤት  ምን ቀጡ ሰጠንህ እያሉ የሚያሹፉት፡፡ ኦሮሞ ነኝም የምትል ሌላው መጠየቅ ያለበት ስለሕዝብ የታሰሩትን ጉዳይ ነው፡፡ መዘናጋትም አይኑር፡፡  እነጀዋር አራሳቸው ጽፈው ቀጣይ የምተለያይበትንና ለእነሱ ተገዥ የምትሆንበትን እየሰሩልህ ነው፡፡

 

ማስተዋሉን ይስጠን!

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!

አሜን!

 

ሰርጸ ደስታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.