ተቃዋሚዎች ህዝባዊ አጀንዳ የላቸውም ማለት ጉንጭ አልፋ ክርክር ማንሳት ዘመን ያለፈበት ነው

በአሁኑ ወቅት በም እራባውያን የተያዘው ድርድር እንደተጠበቀ ሆኖ ስልጣን ክፍፍሉም የምርጫ አዘቦትን ተንተርሶ መካሄዱንም አማክሎ ከውጪ ወደውም ይግቡ አሊያም ነጮቹ አሰልጥነው ይላኳቸው የሆነ ይሁን ባቻ ተቃዋሚዎች ህዝባዊ አጀንዳ የላቸውም ማለት ጉንጭ አልፋ ክርክር ማንሳት ዘመን ያለፈበት ከመሆኑም በላይ የነቃ ሕዝብ እና እልሁን በምርጫ ካርድ ለማሳየት ያደፈጠ ህዝብ መሃል ሆኖ ለመንጠራራት መሞከር ነገን ደብቁኝ ያመጣል:: ምርጫዎች ከሃያ ሶስት ዓመት እልህ አስጨራሽ ውጣ ውረድ በኋላ ውጤታቸው መድብለ ፓርቲን የማይወክሉና ዴሞክራሲዊ ተግዳሮቶች የወጠራቸው ሆነዋል፡፡

በእርግጥም ገዢው ፓርቲ ደጋግሞ እንደሚለው “ተመራጭ ፓርቲ” ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሃገር አሸናፊ ወይም ተሸናፊ ፓርቲ መሆን በችግርነት ሊነሳ አይችልም፤ ነገር ግን 99.9 ፐርሰንት ማሸነፍ ሌላው ቢቀር የሚነገርለትን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ትዝብት ላይ መጣሉ አይቀሬ ነው፡፡የተቃዋሚዎች ድክመት እንዲሁ በባዶ ሜዳ የሚፈጠር ችግር ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ከሌላው አለም ስለማትለይ፣ ችግሩ የጋራ መሆኑን መጠራጠር ለፈተናው አይነተኛ ማነቆ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የመንግስት እዳ ከሃላፊነትም ሆነ ከስልጣን አልያም ከተገባው ቃለ መሃላ ጋር ተዳምሮ እዳው ታሪካዊና የትየለሌ ነው፡፡ የሃገሪቱ ዴሞክራሲ ተቃዋሚን መውለድ እንጂ ማሳደግ ለምን አልቻለም ሲባል ሕዝባዊ አጀንዳ ስለሌላቸውና ጠንክረው ስለማይሰሩ የሚለውን ጉንጭ አልፋ ክርክር ማንሳት ዘመን ያለፈበት ይመስለኛል፡፡

ጠንክሮ ለመስራት ቢያንስ ምህዳሩ አማራጭ ሃሳብን ለመፈተሽ በቂ እድል የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሃ መጮህ በመንፈሳዊው ዓለም መልስ ያስገኛል፣ ውጤትም አለው፡፡ በፖለቲካ አለም ግን ፍየል ወድያ ቅዝምዝም ወዲህ ከመሆን አያልፍም፡፡ ተቃዋሚዎች በምርጫ ታሪክ ቀላል የማይባል መራጭ ድምጽ እንደሰጣቸው አሌ ሊባል የማይችል እውነታ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ቢያንስ እንኳን በተመረጡ ሰሞን በሙስናና በአቅም ማነስ ተገምግመው የሚባረሩትንና በሕዝብ ተቀባይነት ያጡትን የገዢ ፖርቲ ተመራጮች ማሸነፍ እንዳቃታቸው ለማሳመን መሞከር፣ በሆድ ይፍጀው ብቻ ሊታለፍ የሚችል አይደለም፡፡

UDJAUEP
·