በአቶ ማሙሸት አማረ እና በአቶ ለገሰ ወልደሃና ላይ የሚደረገዉ ኢሰበአዊ አያያዝ ቀጥሏል (ሸንቁጥ አየለ)

አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሊቀመንበር የነበሩ

በእስር ላይ በሚገኙት በመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ላይ የሚደረገዉ ኢሰበአዊ አያያዝ ቀጥሏል::
በተለይም በአቶ ማሙሸት አማረ  እና በአቶ ለገሰ ወልደሃና  ላይ የከፋ ኢሰበአዊ አያያዝ እየተፈጸመባቸዉ መሆኑ ታዉቋል::
በየቀኑ በሚደርስባቸዉ ድብደባ እና ስቃይ የከፋ የጤና አደጋ ዉስጥ ናቸዉ::

አቶ ለገሰ ላይ በደረሰበት ድብደባ ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት ደርሶበታል::አይኑ: እጁ : እግሩ: ጆሮዉ እና መላ ሰዉነቱ ለከፋ ጉዳት ተዳርጓል::

ወያኔ የመኢአድ አመራሮችን እና አባላትን አሁን ድረስ ከመላ ሀገሪቱ እየለቀመ ወደ እስር ቤት እያስገባ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰባቸዉ ነዉ::

የወያኔ መንግስት በፖለቲካ ተቃዋሚነትም ሆነ በጋዜጠኝነት ያያዛቸዉን እስረኞች ሁሉ በጭቃኔ እንደሚያሰቃያቸዉ እና በመጨረሻም ብዙዎቹ ለጤና መታወክ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ ይታወቃል:: የመላዉ አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) መስራችን ፕሮፌሰር አስራትን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል::በቅርቡም አቶ ሀብታሙ የሰጠዉን ምስክርንት ማስታወስ በቂ ነዉ:: በተለይም የአማራ ዘር ያላቸዉን እስረኞች በተለዬ እና በረቀቀ የማሰቃያ ስልት እያሰቃያቸዉ እንዳለ ይታወቃል::አቶ ለገሰ እና አቶ ማሙሸትም የዚሁ የከፋ ሰለባ ሆነዋል::

በመላዉ አለም የምትገኙ የመኢአድ ደጋፊዎች እንዲሁም ኢትዮጵያዉያን የዲሞክራሲ እና የሰበአዊ መብት ተቆርቋሪ ሀይሎች በአቶ ለገሰ እና በአቶ ማሙሸት አማረ ላይ የሚደርሰዉን እጅግ ዘግናኝ ኢሰበአዊ አያያዝ እንድታወግዙ እንጠይቃለን:: እንዲሁም ይሄንኑ ሁኔታ ለልዩ ልዩ አለም አቀፍ ተቋማት እንድታሳዉቁ አበክረን እናስገነዝባለን::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.