በሮናልድ ሬገን ውስጥ ቴዲ ኣፍሮ – ንጉሤ አዳሙ

የዚህ ጽሁፍ ጽንሰ ሃሳብ ቴዲ አፍሮ ወይም ቴዎድሮስ ካሳሁን በቪኦኤ የአማርኛዉ ፕሮግራም ላይ ካደረገዉ  ቃለመጠይቅ ላይ መሰመር ያለበትን ሃሳብ ለመጠቆም ነው፥ ይህ ጨዋና ኣርቆ ሳቢ የሆነ ወጣት:-
” ኢትዮጵያዊነት ኣደጋ ላይ የወደቀበት ሰኣት ላይ ነን እንዳለመታደል ሆኖ የዚህ ችግር ደግሞ እኛ ወጣቶች ላይ  የተጋፈጧል ብሎል።”
ይህ ኣንደበተ ርእቱ የዘመናችን ወጣትና የብዙሃን ድምጽ የሆነው ቴዲ ኣፍሮ በመቀጠልም
“መቻቻል፥ መከባበር፥ መስማማት፥ የሃገራችንን ህልውና ከራስ ህልውና ጋር በማጣመር ለሃገራችን የሚበጀውን መሞከር ብቻ ሳይሆን ማድረግ ኣለብን ብሏል።”
በዚህ ጠንካራ ኣቆሙ ነው ቴዲ ኣፍሮን ከሊሎች የሙዚቃ ባለሙያወች እኩል ልንተቸው ኣይገባም ተብሎ ስንከራከርለት የከረምነው።
ቴዲ አፍሮ ከፖለቲከኞቻችን በተሻለ፤ ከታሪክ ኣዋቂቀቻችንን በበለጠ፥ ከምሁራን በላቀ መልኩና ከሃይማኖት መሪወች በተሻለ ኢትዮጵያዊነትን ትክሻው ላይ የተሸከመ  የዚህ ዘመንና ትውልድ ልሳን ነው።
እያንዳንዱ ትውልድ የራሱ የሆነ የትውልድ ልሳን እንዳለው ሁሉ ቴዲም የዚህ ዘመን ምሳሌ ነው፤ ልዩነቱ ግን እንደ ቴዲ ኣይነት ለማግኘት ከ፻ ኣመት በላይ ፈላጊ መሆኑ ኣያጠያይቅም።
ረጋ ባለ ልቡና ካሰብነው ኢትዮጵያ የሚለውን መንፈስ መልሶ ለመፍጠርና ለመገንባት ስንት ፖለቲከኞች ኣቦኩት፥ ስንት የታሪክ ጻህፍት ተቀኙበት፤ ከ26 ኣመት በላይ ብሄርተኝነት የተዘራብን ትውልድ በቀዬው ብቻ እንዲደናቆር ወያኔ ቀን ከለት መሰሪ ተግባሩን ዘራ፤ የሃገራችን ባንዲራ ዝቅ ብላ የብሄርተኝነት ባንዲራ ምድራችንን ኣጥለቀለቃት፤ ባለፉት 26 ኣመታት ያደጉት ወጣቶች ጀግና ማለት ሃየሎም ኣረኣያ፤ መለስ ዜናዌ፤ ቴወድሮስ አድሃኖምና እነ ገብረ-ጽቡቅ ብቻ ናቸው ተብሎ ተተረከላቸው።
ህዝባችን በጠባቦች እጅግ ተመርዞ ክፉኛ ኣደጋ ባንዣበበብን ሰኣት ቴዲ ኣፍሮ ከትፍ ኣለና የኢትዮጵያን ባንዲራ ሰማያ ጥግ ስር ሰቀላት። ማንም ተነስቶ ሊያወርዳት በማይችል ሁኔታ ባንዲራችንን አሳየን። የ አጤ ቴዎድሮስ ራይ እውን ይሁን ኣለ። ትውልዱ ሁሉ ስለ አጤ ተወድሮስ የተጻፉትን መጸሃት ጠላሸት ከወረሰዉ መደርደሪያ ዉስጥ ስቦ ማገላበጥ ጀመረ። ራሱን የሚመረምር ትውልድ ገነባን። የተከፋፈለ የሚምስልን ትውልድ በኣንድ ሃገር በኣንድ ባንዲራ እንባ እያራጨ ኢትዮጵያ.. ኢትዮጵያ.. ኢትዮጵያ.. ኢትዮጵያያያያያያያያን ተዘመረ። ከለፈዉ ይበልጥ መጭዋ ኢትዮጵያ ታለመች። አንድነት፥ እኩልነት፥ መቻቻልና የህግ የበላይነት የሰፈረባት ሃገራችን ታሰበች።
እንግዲህ ሮናልድ ሬገን ይህኔ ትዝ አለንና በቴወድሮስ ካሳሁን ላይ ያለምነዉ።
  ሮናልድ ሬገን የሚባል ኣሜሪካዊ የሆሊውድ ፊልም ባለሙያ ነበር በዘመኑ ጉደኛ የተባሉ የሆሊውድ ፊልሞችን ሰርቶ በችሎታው ድንቅ የተሰኘም ነው።
 ከ14 በላይ ፊልሞችን ሰርቶ ኣንቱ የተሰኘ ኣርቲስት መሃል ነበር። ይህ ድንቅ ባለሙያ በወቅቱ የነበረውን የሃገሩን ሁኔታ በማጤን ፖለቲካ ዉስጥ ገባና ለካሊፎርኒያ ስቴት ገዥ በመሆን ተመረጠ በመቀጠልም 40ኛው የኣሜሪካን ፕሬዘዳንት በመሆን ለ8 አመታት ኣግልግሏል። ከሚነሳለት በርካታ በጎ ምግባሮቹም ኣንዱ ከሶቬት ህብረት ወይም ራሺያ ጋር የነበረውን የቀዝቃዛውን ጦርነት በመቋጨት ይታወቃል።
የዚህ ሰው መነሻው ፊልም ነበር ጥበብ።
ቴዲ ኣፍሮም ተመሳሳይነት ኣለው። በኢትዮጵያ ወጣቶች ልብ ውስት ክፉኛ ዘልቆ ገብቶል። ለብዙወቻችን ሙሴ ነው፤ ኢትዮጵያዊነትን ይዞ ከባህር ሊያሻግረን የሚችል ድንቅ የዘመናችን ፈርጥ ነው።
ሮናልድ ሬገን ከፊልም ተነስቶ ኣሜሪካንን ከመራ ቴዲስ ምን ያንሰዋል? በርግጥ የዚህ መልስ ያለው ራሱ ቴዲ ላይ ነው፤ ወደፊት የምናየውም ይሆናል።
በኔ እምነት ግን….
 ኣንደበተ ርእቱነቱ፣ ትእግስቱ፣ ታሪክ ኣዋቂነቱ፣ ለይቅርታ ያለው ጽኑ እምነቱ፣ ለህዝባዊ ወገንተኝነት ያለው ፍቅር እና ሃገር ወዳድነቱን ሳይ የሮናል ሬገንን ፈለግ በተከተለ ብየ እመኝለታለሁ።
ቸር ያባጀን እና አናያለን ብሎል ራሱ ቴዲ እና እናያለን፦
ንጉሤ ነኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.