የአየር ወለዱ መሃንዲስ……የግንቦት ስምንቱን መፈንቅለ መንግስት ስናስታውስ

ሜጀር ጄነራል ደምሴ ቡልቶ

#ኢዮብ ዘለቀ

በወርሃ ነሐሴ 1953 ዓ.ም፤ አስራ ዘጠኝ ሰዎችን ያሳፈረውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ዲሲ 3 አውሮፓላን በበረራ ላይ እንዳለ በቀድሞው አጠራር በየረርና ከረዮ አውራጃ ፤ዳለቻ በሚባል ስፍራ ላይ ተከሰከሰ፤ አውሮፓላኑ ወድቋል የተባለበት ስፍራ ለነፍስ አድን ስራ የሚመች ባለመሆኑ አየር ወላዶችን በዚህ ስፍራ ላይ በፓራሾት ማውረድ ግድ ሆነ ፤ አየር ወለዶቹ በዚህ የነፍስ አድን ስራ ላይ በመሰማራት የብዙዎችን ተሳፋሪዎች ህይወት ለማዳን ቻሉ ፤ በዚህ ካባድ ግዳጁ ላይ በመሰማራት የወገንን ህይወት ከታደጉልን አራት የአየር ወለድ አባላት መሃከል የያኔው የመቶ አለቃ ደምሴ ቡልቶ የኃላው ሜጄር ጆነራል ደምሴ ቡልቶ አንዱ ነበሩ ።

ከቢልቻ ወንዝና ፎየታ ተራራ በስተጀርባ፤ ሙገር አካባቢ በምትገኘው ገጠራማ ቀበሌ በ1926 ዓ.ም የተወለዱት ስመጥሩ የአየር ወለዱ መሃንዲስ ሜጀር ጀነራል ደምሴ ቡልቶ ከልጅነታቸው አንስቶ ወታደር የመሆን ምኛት ነበራቸው ፤ የክቡር ዘበኛ ጦርንም ሲቀላቀሉ ገና ልጅ ሳሉ ነበር።

እኝህ ቆፍጣና ወታደር በሲውዲን መኮንኖች ስልጠናን ካገኙ የሶስተኛው ዙር የክቡር ዘበኛ ሙሩቃን መሀከል አንዱ ነበሩ ፤ በ 1946 ዓ.ም ወደኮሪያ ካቀናው የኢትዮጲያ ጦር ጋር በመዝመት ግዳጃቸውን በብቃት ተወጥተዋል ፤ስመ ጥሩው የጦር ሰው ሜጀር ጄነራል ደምሴ ቡልቶ ።

ሜጀር ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በእስራኤል ሀገር የአየር ወለድ ስልጠናን ወስደው ወደ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ የአየር ወለድ ጦርን በኢትዮጲያ ካቋቋሙት መኮንኖች መሀከልም በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ ። በ1955 በደጋሀቡር ፣ በ1957 በባሌ የሶማሊያን ጦር በማሳፈር ይታወሳሉ ። ጀነራሉ እዚህ ማእረግ ላይ ለመድረስ ድፍን 38 አመታት ፈጅቶባቸዋል ።

ሜጄር ጄነራል ደምሴ ቡልቶ ከ1981 ዓ.ም ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማሪያምን ከስልጣን ለማስወገድ በተደረገው ሙከራ የአስመራውን እንቅስቃሴ በዋናነት መርተዋል ።ይህ የአስመራው እንቅስቃሴ ሲከሽፍ በአየር ወለድ ሀይሎች በጥይት ተደብደበው ተገድለዋል ፤አየር ወለዶቹ በዚህ ብቻ አላበቁም በአስከሬናቸው ላይ ከአንድ ኢትዮጲያዊ ስነምግባር የማይጠበቅና ነውረኛ ድርጊቶች ሁሉ ፈጽመዋል፤ ይህ ሁሉ የሆነው ከዛሬ 28 አመት በፊት በዚህ ሳምንት ነበር ።

ከጀነራል ደምሴ ጋር በአስመራው እንቅስቃሴ ላይ ተሳታፊ የነበሩና ሁዋላ ላይ የተገደሉ የኢትዮጲያ ስመጥር ጀነሎችና ሌሎች መኮንኖች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

1. ብ/ጀነራል አፈወርቅ ወ/ሚካኤል
2. ብ/ጀነራል ታዬ ባላኪር
3. ብ/ጀነራል ታደሰ ተሰማ
4. ብ/ጀነራል ወርቁ ቸርነት
5. ብ/ጀነራል ንጉሴ ዘርጋው
6. ብ/ጀነራል ከበደ መሀሪ
7. ብ/ጀነራል ተገኔ በቀለ
8. ብ/ጀነራል ከተማ አይተንፍሱ
9. ብ/ጀነራል ከበደ ወ/ጻዲቅ
10.ብ/ጀነራል ሰለሞን ደሳለኝ
11. ዶ/ር ኮሎኔል ጌታቸው አወቀ
12. ኮሎኔል መስፍን አሰፋ
13. ኮሎኔል ፈቃደ እንግዳ
14. ሌ/ኮ ዘርአይ እቁባአብ
15. ሌ/ኮ ዮሀንስ ገብረማሪያም
16.ሻለቃ ካሳ ፈረደ
17. ሻለቃ ሚካኤል ማርቦ
18. ሻምበል ጌታሁን ግርማ

በአዲስ አበባው እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፋና ሁዋላ ላይ ከተገደሉት መሀከል፦

1. ሜጀር ጄነራል መርዕድ ንጉሴ
2. ሜጀር ጄነራል ፋንታ በላይ
3. ሜጀር ጄነራል ኃይሉ ገ/ሚካኤል
4. ሜጀር ጄነራል ወርቁ ዘውዴ
5. ሜጀር ጄነራል አምሀ ደስታ
6. ሜጀር ጄነራል ዓለማየሁ ደስታ
7. ሜጀር ጄነራል ዘውዴ ገብረየስ
8. ብ/ጀነራል ደሣለኝ አበበ
9. ብ/ጀነራል ሰለሞን በጋሻው
10. ብ/ጀነራል ተስፋ ደስታ
11. ብ/ጀነራል እንግዳ ወ/አምላክ
12. ብ/ጀነራል እርቅይሁን ባይሣ
13. ብ/ጀነራል ነጋሽ ወልደየስ
14. ብ/ጀነራል ገናናው መንግሥቴ
15. ብ/ጀነራል ተስፋዬ ትርፌ

# ለበለጠ መረጃ በጄነራሉ ልጅ ደረጄ ደምሴ የተጻፈው
” አባቴ ያቺን ሰዓት ” እና ሌሎች በደርግ ባለስልጣናት የተጻፋ መጽሀፍቶች አግኝታችሁ ብታነቡት ጥሩ ጥሩ መረጃዋችን ታገኛላችሁ ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.