ታምራትና ስብሃት – አርአያ ተስፋማሪያም

10897854_776962339046109_4854305913154480156_n (1)ጠንቋይ ታምራት ገለታ ለእስር የበቃበት ምክንያት ተከታዩን እንደሚመስል የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠንቋይ ታምራት ሸራተን ጐራ ይላል፤ አካሄዱ ስብሃት ነጋን ለማግኘት ነበር። ሲያገኛቸው ትእቢት በተሞላበት አነጋገር « እርሶ ዘንድ የላኩኝ ባለስልጣናት ናቸው። ከበቂ በላይ ገንዘብ ያለኝ ሰው ነኝ። በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘቤን ኢንቨስት ማድረግ ስለምፈልግ መሬት እንዲሰጠኝ ትእዛዝ ያስተላልፉልኝ» ይላል። ስብሃትም « ምናልከኝ?» ይሉታል። ታምራት ደረቱን ለጥጦ « አልሰሙኝም?…መሬት እፈልጋለሁ። እነአባዱላ የእኔ ሰዎች ናቸው። በኦሮሚያ ችግር የለብኝም። አሁን የምፈልገው መሬት አዲስ አበባ ላይ ነው። እርስዎ እንደሚፈቅዱ አውቃለሁ። ስለዚህ ያሰጡኝ.» ሲል ይናገራል። ስብሃት መልስ ሳይሰጡ ለደህንነቶች “ይህን ሰው ተከታተሉና እሰሩት” ሲሉ ያዛሉ። በቀናት ውስጥ ጠንቋይ ታምራት ዘብጥያ ወረደ።..በነገራችን ላይ ታምራት ገላታ አሜሪካ በተለይ ዲሲና ቨርጂኒያ እየመጣ ከበርካታ ሃበሾች « 20 ፐርሰንት ግብር ስጡ፤ ያልሰጠ ደግሞ..» እያለ በ10ሺህ የሚቆጠር ዶላር ይሞጨልፍ እንደነበረ ያውቃሉ?….ሰጪዎቹ ማፈር ይገባቸዋል።…ከታች የምትመለከቱት ፎቶ ስብሃት ነጋ እዚህ የመጡ ጊዜ ባረፉበት ሆቴል የተነሱት ነው። ሌሎች ፎቶዎችም አሉ። የባለስልጣናቱ ነውረኝነት ከዚህም በላይ ነው…ፎቶዎቹ በየተራ ይለቀቃሉ…

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.