የምርጫ ወጋችን – ከ ዮም አይዛክ

ትላንት ግንቦት 7 የዲሞክራሲ ጮራ ፍንጣቂ ያየንበት ህወሀት/ኢሀዴግ ደሞ ከስተቱ የተማረበት፡፡ ያው ከስተቱ ማለቴ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ምን ያህል እንደተተፋ እና አምባገነናዊው የሆነ የተፈጥሮ ባህሪውን በዴሞክራሲ ጭንብል ለማለፍ ሲሞክር ህዝብ ስለገለጠበት እና ስላወቀበት ተፈጥሮአዊ ባህሪው ያልሆነውን ዴሞክራሲ አይደለም ለመተግበር ለማሰብ እንኳን ፀረ አብዮታዊነት/ልማት መሆኑን ለራሱ የነገረበት እና ያመነበት እናም ላለመድገም የማለበት አክሎም አምባገነናዊ እና ጥላጫ የመፍጠር ባህሪውን ለመቀጠል የወሰነበት ማለቴ ነው፡፡ ከስተቱ ተምሮ አይደል 100 ፐርሰንት ያሸነፈው!! የሰው ፍፁም የለም የፓርቲ እንጂ አለ ኢህዴግ!!! እናም ይህን ክስተት እንግዲ 12 ዓመታትን ወደኋላ ተጉዤ የታሪክ ማህደራትን በርብሬ እናም ጥልቅ የሆነ ጥናትና ምርምር አድርጌ ነው ግንቦት 7/1997 የነፃነት ተስፋ ፈንጥቆ የጠፋበት እናም ህወሓት/ኢህዴግ ከስተቱ መማሩን ያረጋገጥኩት፡፡ እንዴት 12 ዓመትን ብዙ አረገው ነው ያላቹት? ያው የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ነው ይሉን አይደል? ታዲያኮ 12 ዓመት ትልቀ ድርሻ ነው ከ 100 ኣመት (ታሪክ እና ቁጥር ለማያቁ)፡፡ ደሞ ይህ ታሪክ አጻጻፍ ወደአንድ ወገን ያደላ ነው የሚሉም አይጠፉም ያው የእነናተን “ፍላጎት” ሰላላካተተ ነው እያልሁ በተረፈ የ በረከት ስምዖንን የሁለት ምርጫዎች ወግን አንብቡ እላቹኋለው፡፡ ስለሚስማማቹ፡፡

ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባና ምርጫ ማለት ለኛ ምን ማለት ነው? የምንመርጠው ምንን ነው? የምርጫችን መስፈርትስ? መልክ አይተን፣ ጎሳ ለይተን፣ ወይስ ለኛ ስለቀረበን?
መሆን ያለበት ካልን የምንመረጠው የአስተሳሰብ ልዕልናን (ልዩነትን/ክፍፍልን ሳይሆን አንድነት፣ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን)፣ ቅን አመለካከትን (ህዝባዊነት)፣ ፍትሃዊ እሳቤን፣ አማካይ ራእይን፣ ነጻነትን እና ወዘተ ናቸው፡፡ እነዚህ ምርጫዎቻችን መገለጫቸው ሰው ነው ታዲያ የምንመርጠው እና ሃላፊነት የምንሰጠው የጠቀሰናቸውን እና መሰሎቹን ለሚተገብር ሰው ነው፡፡

ስለ ምርጫ ይህን ያህል እንድል ያስገደደኝ አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት የበላይ ጠባቂ እንዲሆን መደገፍ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ነው ለሚሉት እኛ የምንመርጠው ሰውዬውን ሳይሆን አስተሳሰቡን፣ ሰውዬው ከየት ተገኘ ብለን ሳይሆን በቦታው ላይ ሆኖ የሚያራምደው ራዕይ እና ከዚህ በፊት ያለው ህዝባዊነቱ እናም በተጨማሪም ከላይ የጠቀስናቸው የምርጫ መስፈረቶቻችንን ለሚያሟላ እንጂ እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም ከኢትዮጵያ ስለተገኘ ብቻ የምንሰጠው ድጋፍ አይደለም፡፡ በእርግጥ አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ከኢትዮጵያ ወጦ የዓለም ጤና ድርጅት የበላይ ጠባቂ ለመሆን እየተወዳደር ይገኛል ሆኖም ህወሓታዊ/ኢህዴጋዊ ዕሳቤውን፣ አመለካከቱን እና ርዕዮቱን ይዞ እና አዝሎ ነው፡፡ ይህም ማለት አቶ ቴዎድሮስ  በኢትዮጵያ ስም አለም አቀፍ መድረክ ቦታ ይይዛል ግን አዕምሮአዊ ሁለንተናው ፀረ ኢትዮጵያ እና ህወሓታዊ ነው፡፡

ታዲያ ይህ ሰው ቦታውን ከያዘ የህወሀት የጥንካሬ ምንጭ እና አላማ አስፈጻሚ አይሆንም የሚል ግለሰብ ካለማስተዋል፣ የሰውዬውን ማንነት ካለመቀበል እና ማወቅ ካለመፈለግ በተጨማሪ ራሱ ህወሀት እና የህወሀት ሎሌ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ፍላጎት ሳይሆን የተወለደበተን እና የርዕዮተ ዓለም አጥማቂውን ህወሀትን ፍላጎት (ጭፍን ጥላቻ እና ክፍፍል) ነው፡፡ ይህ ሰው እየተወዳደረ ያለው እነደ ሯጮቻችን ባንዲራችን (የኢትዮጵያ) በዓለም አቀፍ መደረክ ከፍ ሲል እንባውን እየረጨ መዝሙር ሊዘምር አይደለም፡፡ እንደ አንድ ባለሙሉ ባለስልጣን የራሱ የሆነ ድምፅና ትልቅ የሆነ የመወሰን የስልጣን ድርሻ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማግኘት ነው፡፡ ይህ ማለት ህወሀት በዓለም አቀፍ መድረክ ወሳኝ የሆነ ድምፅ እና ሽንጡን ገትሮ ተከራካሪ አገኘ ማለት ነው እንጂ ያልሰረፀበትን ኢትዮጲያዊነት እና ህዝባዊ አጀንዳ ያራምዳል ማለት ዘበት ነው፡፡ እንዲያ ከሆነማ እዚሰ በስልጣን ሳለ ኢትዮጲያዊነት እና ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ማን አጠፋበት?

ቅን እሳቤ፣ መልካም ስራ ለመስራት፣ ህዝባዊ ወገንተኝነትን ለማራመድ እና ተመራጭ ለመሆን ቦታ ወይም የመድረኮች (ስልጣን) መለያየት ዋጋ የለውም ዋናው ጉዳይ ባለህበት ቦታ እና መድረክ (ስልጣን) ለህዝብ መታገል እንጂ፡፡ አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ደሞ ይህ እድል በእጁ ለረዠም ጊዜ ነበር ታዲያ ለህዝብ መስራትን ምነው ያልታወሳቸው? በቅርብ ሆነው ያላገለገሉትን ህዝብ በሩቁ እንዴት ታሰባቸው? ብቻ ዋናው ጉዳይ አስመሳይነት የድርጅታቸው ባህሪ እና አሳቸውም መቀየር የማይችሉት በደማቸው ገብቶ ባህሪ ሆኖ ስላለ ነው፡፡
ጉለቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.