የዐማራ ገበሬዎች ላይ የዘመቱ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነው ተመልሰዋል፤ – ሙሉቀን ተስፋው

  • ‹‹የሁለተኛ ደረጃ ትቤት መልቀቂያ ፈተና ትግርኛ አንፈተንም›› የወልቃይት ተማሪዎች

በሳምንቱ መጨረሻ በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የዐማራ ገበሬዎች ላይ የዘመተው የወያኔ ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ተመልሷል፡፡ ከግንቦት 25 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ወገራ አጅሬ የተላከው የትግሬ ሠራዊት ከዐማራ ተጋድሎ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ያስነሳሉ ያሏቸውን ገበሬዎች ለመያዝ እንደሆነ የገለጹት ምንጮች አስከሬኖችና ቁስለኞች በወታር ኦራሎች ተመልሰዋል ብለዋል፡፡

በጎንደር ዩንቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ 40 ያክል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የአገዛዙ ወታደሮች ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን 8 አስከሬንም አብሮ እንደመጣ እማኞች ገልጸዋል፡፡ በጎንደር ሆስፒታል ከገቡት በተጨማሪ በ24ኛ ክፍለ ጦር ሆስፒታልም መለስተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ቁጥራው የማይታወቅ ወታደሮች እንዳሉ መስማታቸውን መረጃዎቻችን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በወልቃይት ጠገዴ ‹‹ትግርኛ የእኛ ቋንቋ አይደለም፤ መፈተን አንፈልግም›› የሚል ተቃውሞ በተፈታኞች ተነስቶ ነበር፡፡ ሆኖም በትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ተገደው ፈተና ላይ መቀመጣቸውን ተፈታኞች ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.