ያሻንጉሊት ፀሎት

አቤቱ ጌታ ሆይ የሰለሞን አምላክ
ሰለቸኝ ስድቡ ሰለቸኝ መላላክ፤
ምን ላድርግ አምላኬ ያንተን ክብር ትቼ
በወንበር ጥማቴ ከንቱ ተጎልቼ
አላቅድ አልወጥን
አልዘገይ አልፈጥን
አልፈፅም ፈቃዴን
እየሞላሁ ሆዴን
በስድብ ማንጓጥጠጥ
በስላቅ ማሽሟጠጥ
በመሃይም ቅርሻት በውርጋጥ ድንፋታ
ነፍሴ ተጨነቀች ጠዋትና ማታ ።
እባክህ አምላኬ በሰው አስወድደኝ
ወይም ከዚህ ውርደት ገላግለኝ ውሰደኝ።
አሜን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.