ይልቅ ወሬ ልንገርህ ስለ ወልቂጤው ማረሚያ ቤት እስረኛ ግድያ – ቁምነገር መፅሔት

መቼም በየዕለቱ በየሰዓቱ ከአራቱም የሀገራችን አቅጣጫ ስለሚሰማው ዜና ለመገመት ከባድ ነው አይደል? ባለፈው ሰሞን በደቡቧ ከተማ ወልቂጤ ምን ሆነ መሰለህ?
ሰኔ አራት ማታ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ይሆናል፤ እሺ አልክ? በግምት ዕድሜው 25 ዓመት የሚሆነው መስፍን አዳነ የሚባል ወጣት የቀቤና ብሔር ተወላጅ ከሆነችው ወጣት ሲቲና ጀማል ጋር የነበረውን የግል ፀብ መነሻ በማድረግ ጠብ ውስጥ ይገባል አሉ፡፡ መስፍን ዕድሜዋ 28 ዓመት የሆናትን የ8 ወር ነፍሰጡር አስቀድሞ ተዘጋጅቶበት የነበረውን ጩቤ ከጀርባው ላይ ላጥ አድርጎም እዛው አደባባይ ላይ ደጋግሞ ይወጋታል፡፡ 

ወጣቷ ራሷን ለመከላከል ብትሞክርም ህይወቷን ለማትረፍ ሳይቻል ይቀራል፡፡ ወጣት መስፍንም የፀጥታ ሰራተኞች በፍጥነት በቦታው ደርሰው ይዘውት ወደ ወልቂጤ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ይወሰዳል፡፡
እናስ? እናማ ወጣቷ በማግስቱ እዛው ወልቂጤ ውስጥ ባለ ቤተክርስቲያን ቀብሯ ይፈፀማል፡፡ ከቀብሩ በኋላ ግን ለህግም ፤ለሞራልም ከባድ የሆነ ድርጊት ስለመፈፀሙ ነው በወቅቱ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች የሚናገሩት፡ ፡ ምን ሆነ አልክ? 

በማግስቱ ከቀኑ በሰባት ሰዓት ሲሆን የሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች ድንጋይ ዱላና ሌሎች ስለት ያላቸውን መሳሪያዎች ይዘው ተጠርጣሪው እስረኛ ወደሚገኝበት ወልቂጤ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡ እናስ? እናማ በወቅቱ ፖሊስ ጣቢያው በር ላይ የነበሩት የጥበቃ ሰራተኞችን ረዳት ሳጅን በቀለ በዳሳና ኮንስታብል ትዕግስት አለሙን ጥሰው በመግባት ተጠርጣሪው ወጣት መስፍን አዳነ ላይ የድርንጋይ ውርጅብኝ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ 

በመጣው ሰው ሁሉ በደም ፍላት የተወገረው ወጣት መስፍን ብዙም ሳይቆይ እዛው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ህይወቱ ያልፋል፡፡ ተጨማሪ የፀጥታ ሀይሎች ወደ ፖሊስ ጣቢው ተጠርተው ሲመጡ ግን ጣቢያው ውስጥ የተገኘው የወጣቱ አስከሬንና ሁለቱ የጥበቃ ሰራተኞች ብቻ ነበሩ፡ ፡ ወጣት መስፍንም በማግስቱ በምዕራብ ሸዋ ሸነን ወረዳ ስልክ አምባ ላይ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡
እናስ? እናማ ጉዳዩን በተመለከተ ጭፍጨፋ የፈጸሙ ሰዎች እየተፈለጉ ሲሆን ሁለቱ የጥበቃ ሰራተኞች ዱላና ድንጋይ እንዲሁም ስለት ታጥቀው የመጡ ሰዎችን መከላከል አልቻላችሁም የተባሉት ሁለት ፖሊሶች በሚል በቁጥጥር ስር ሆነው ምርምራ እየተጠራባቸው ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ ምን ይሄ ብቻ መሰለህ፤ እነዚሁ ሰዎች እንደገና በማግስቱ ዲያስፖራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ያለውን የሟች ቤተሰቦች መኖሪያ ቤትን በእሳት አጋይተውታል ተብሏል፡፡የህግ የበላይነቱስ አልክ? ተግባራዊ ከሆነ ስሰማ እነግርሀለሁ፤ በል ቻዎ…

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.