የህወሓት ኮማንድ ፓስት ወታደራዊ ዕዝ በቋራ ህዝብ ላይ ቤታቸውን በማፍረስ የበቀል እርምጃውን ቀጥሏል!!

ደም መላሽ ተገኘ

በቋራ በረሃ ለነፃነት የሚዋደቁ ትጥቅ አንስተው የሞት ሽረት ትግል ላይ ያሉ አርበኞች ከዚህ ቀደም ያላቸውን ለም መሬት እንዳይታረስ በመከልከልና በኢንቨስትመንት ስም እየተቀሙ ለህወሓት ባለሀብቶችና ባለስልጣናት ቤተሰቦች ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑ ካለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ ደግሞ በቋራ ወረዳ ገለጉ ከተማ የሚገኝ የመኖሪያ ቤታቸውን በህገወጥነት ስም እያፈረሱባቸው ቤተሰቦቻቸው በክረምቱ ያለመጠለያ እያስቀሩ እየተበተኑ ይገኛል።በከተማው እስካሁን ከ200 ቤቶች በላይ በህገወጥነት ስም የፈረሱ ሲሆን ብዙወች ወጣቶች በዚህ የበቀል በትር ተማረው ወደ ጫካ ገብተዋል።

መቀመጫውን በ1990 ዓ.ም እንደከተማ በተመሰረተችው ገለጉ ከተማ ያደረገው የቋራ ወረዳ ወታደራዊ ዕዝ ኮማንድ ፖስት በኮነኔል ገብረ መስቀል ፀጋየ እየተመራ ከዚህ በፊት በማስመሰያ የምህረት እርቀ ሰላም በካድሬ ቄሶች አማካኝነት ትጥቅ ለማስፈታት፣ ቤተሰቦቻቸውን በማስገደድ እጂ እንዲሰጡ ለማድረግ ሲጥር የነበረው ሲሆን ይህ ሁሉ እንዳሰበው አልሳካ ሲለው እና በየጊዜው የሚደርስበት የደፈጣ ውጊያ መቋቋም ሲያቅተው በአጎራባች የሱዳን ዞን ወታደራዊ አመራሮችን በመሰብሰብ የነፃነት ታጋዩችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በሱዳን ከዲንደር ዞን የተውጣጣ ወታደራዊ አመራሮች በኮነኔል ገብረ መስቀል ፀጋየ ከሚመራው የህወሓት የቋራ ኮማንድ ፖስት ወታደራዊ ዕዝ ጋር በሱዳን ” የዲንደር ፓርክ ” እና በአማራ ቋራ ” አላጥሽ ” ፓርክ በሰፊው ምድር የሚንቀሳቀሱ የነፃነት ሃይሎችን ለመቆጣጠር የሱዳን ባለሃብቶች ከቋራ ገበሬ ተነጥቆ በወያኔ በተሰጣቸው መሬት በዘለቄታ እንዴት ማረስ እንደሚችሉ ከነፃነት ሃይሎች የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በመረጃ ልውውጥ ለመስራት በገለጉ ከተማ ተገናኝተው ቢመክሩም ምንም ውጤት ሲያመጣ አልታየም።ይልቁስ የነፃነት ትግሉ አድማሱን እያሰፋ እየተቀጣጠለ ያለበት ሁኔታ በጉልህ ታይቷል።

የህወሓት ኮማንድ ፖስት የነፃነት ሃይሎች የጉሬላ የተጠና ወታደራዊ ጥቃት ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ይህንና መሰል የተለያዩ የበቀል እርምጃወችን እየወሰደ ይገኛል። የነፃነት ትግሉን ለመቀላቀል በመምሰል ከነሙሉ ትጥቃቸው ያዘመታቸው ወታደሮች የነፃነት ሃይሎችን ለማጥቃት ከሰሞኑ የጠነሰሰው እቅድ ቀድሞ መረጃው በደረሳቸው የነፃነት ሃይሎች ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ እና ሴራው መክሸፉ ከኪሳራ ላይ ኪሳራን ደርቦበታል።
የነፃነት ትግል ጉዞ በበቀል በትር አይደናቀፍም!!
ድል ለጀግኖቹ !!
@እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.