መጤው በነባሩ ፍቃድ የሚኖር ከሆነ አዲስ አበባ የአገዎች ናት (ከሸገር ራዲዮ የተወሰደ

የሚኒስተሮች ምክር ቤት በአዲስ አበባ ዙሪያ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው አስተላልፏል። በዚህ ረቂቅ ሕግ ዙሪያ ተወዳጇ የሸገር ራዲዮ (ሸገር ካፌ) አዘጋጅ መአዛ ብሩ ኢሕአዴግ ስልጣን ከጨበጠ ጊዘ ጀምሮ በአዲስ አበባ ዙሪያ የወጡ የተለያዩ ህጎችን አብዶ ከሚባሉ የሕግ መንግስት ጠበብት እንግዳ ጋር ለመድሰሰ ሞክራለች።

በቃለ መጠየቁ ከተነሱ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ጥቆቶቹ ናቸው፡

  • ፌዴራሊዝሙ በሕዝብ ፍቃድ የተመሰረተ እንደሆነ ቢጠቀስም የአዲስ አበባ ሕዝብ ፍቃዱ እንዳልተጠየቀና በፌዴራል መንግስት ስር ነህ ተብሎ እንደተወሰነለት
  • በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሲባል ፍቃደኝነት የሚጠየቀው ሕዝቡን ነው ወይስ መሬቱ ? አዲስ አበባን በተመለከተ የአዲስ አበባ ህዝብ ፍቃድ ለምን አይጠየቅም ?
  • የኦሮሞ ፖለቲከኞች “በአዲስ አበባ ላይ የታሪክ መብት አለን። የኛ ነበር። በሚኒሊክ ዘመን ነው መሬታችን የተወሰደው” በማለት የመጤና የነባር ጉዳይ ከተነሳ ፣ መጤ የተባለው በነባሩ ፍቃድ የሚኖረ ከሆነ፣ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው የኢትዮጵያ ግዛት ባለቤት ሊባል የሚችለው፣ ኦሮሞው ሳይሆን አገዎች ናቸው።
  • የችግራችን መንስኤው በአንድ በኩል ሕብረ ብሄራዊ አንድነቱን የዘነጋ በሌላ በኩል በብሄረሰባዊ ጊቢው ውስጥና ባለቤትነ ስር የታሸገ የኔ ነው ባይነት ነገር ነው።
  • አዲስ አበባ የሁሉም ዜጎች ናት። ኦሮሞዉን ጨምሮ

ሙሉዉን የሸገር ራዲዮ ቅንብር ለመከታተል ወደ ሚከተለው ሊንክ ይሂዱ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.