የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ፣ ኦነግ፣ ወያኔና የራስ ገዝ (የፌዴራል) ሥርዓት ክሽፈት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ዛሬ ልብ ብላቹህ ተከታተሉኝ፡፡ የችግሩን መንስኤና መፍትሔ እንዲገባቹህ አድርጌ ለመናገር እሞክራለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጽፌበታለሁ፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመሠረተብኝ ክስ ለእስር የተዳረኩትም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ 2006ዓ.ም. መጋቢት ወር ዕንቁ መጽሔት ላይ በጻፍኩት ጽሑፍ ነው፡፡ የኦሮሞ ዐመፅ የተቀላቀለበት ተቃውሞም ሀ ብሎ በጅማ ዩኒቨርሲቲ (መካነ ትምህርት) የተጀመረው በዚህ ጽሑፌ ምክንያት ነበር፡፡ መጀመሪያ ላይ የጅማ ዩኒቨርስቲ (መካነ ትምሕርት) ተማሪዎች እኔና የመጽሔቱ አርታኢ ለፍርድ እንድንቀርብ ላቀረቡት ጥያቄ “አፋጣኝ ምላሽ አላገኘም!” በሚል የጅማ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሒደት ከሳምንት በላይ የተቋረጠበት፣ ንብረት የወደመበት፣ በፈንጅ (በእጅ ቦምብ) ፍንዳታ የሙትና ቁስለኛ አደጋ የተከሰተበት ዐመፅ ተቀሰቀሰ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም ዐመፁ ወያኔ ኦሮሚያ ብሎ በሚጠራው የሀገራችን ክፍል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዛመተ፡፡ ኦሕዴዶችም የዐመፁን መቀስቀስ መልካም አጋጣሚ መጠቀም ፈለጉና ዐመፁን የአዲስ አበባን የማስፋፊያ አቅድ (ማስተር ፕላን) ወደመቃወም ወሰዱትና የሆነው ሁሉ ሊሆን ቻለ ማለት ነው፡፡

ይህ አዲስ አበባንና የራስ ገዝ (የፌዴራል) አሥተዳደርን በተመለከተ የሚፈጠር ችግር አንዲት ሀገር በደናቁርትና ሕዝብ ባልመረጣቸው ወሮበሎች ስትመራ ከሚፈጠሩ ችግሮች አንዱ ነው፡፡ የወያኔ ሕገመንግሥት እርስ በእርሱ ከሚጋጭበት ነጥቦች አንዱ ይህ የመብትና ልዩ ጥቅም አንቀጽ ነው፡፡ ወያኔ በሕገመንግሥቱ ላይ ዜጎች ሁሉ እኩል መሆናቸውን ይደነግግና የአንዱ ብሔረሰብ አባል በሌላው ብሔረሰብ ክልል ሲገባ ግን ሁለተኛ ዜጋ ያደርገውና እኩል ዜግነቱን ያፈርሰዋል፡፡ ወያኔ በሕገ መንግሥቱ “ዜጎች ሁሉ በሀገሪቱ የትኛውም ስፍራ በነጻ የመዘዋወር፣ ኑሮን የመመሥረት፣ ሰርቶ ራስን የማስተዳደር መብት አላቸው!” ብሎ ያበቃና “የራስ ገዝ አሥተዳደር መብት” ብሎ ደግሞ እንደገና ይሄንን የዜጎች መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መብት በክልል አሥተዳደር እንዲሻር እንዲጣስ እንዲፈርስ ያደርገዋል፡፡ በደናቁርት ለመገዛት ስትፈቅድ እንዲህ ትታመሳለህ፡፡

ወያኔ የጎሳ ፌዴራሊዝም (ራስ ገዝ) ሥርዓትን የመረጠበት ምክንያትም አንዱ ይሄ ነው፡፡ እርስ በእርስ እያሻኮተ ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲመቸው፡፡ ሌላው ምክንያቱ ደግሞ እሱ በወደቀ ጊዜ እንድትፈራርስ ለማድረግና የሚጠይቀው የሚበቀለው አካል እንዳይኖር ለማድረግ ነው፡፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም (የራስ ገዝ) የአሥተዳደር ሥርዓት ተፈጥሯዊ የሆነ ኢዲሞክራሲያዊ (ኢመስፍነ ሕዝባዊ) ባሕርይ ስላለው ነው ከሕገ መንግሥቱ ጋር ከላይ የገለጽኳቸው ሁለት መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መርሖዎች ጋር የሚጋጭ ሊሆን የቻለው፡፡

የጎሳ ፌዴራሊዝምን እየተከተሉ በአንድ ሀገር ላይ እኩልነትን አሰፍናለሁ ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም፡፡ ምክንያቱም የጎሳ ፌዴራሊዝም ሥርዓት የሀገሪቱን መሬትና ሀብቷንም (It’s resource) በሀገሪቱ ላሉ ጎሳና ብሔረሰቦች ከፋፍሎ የሰጠ፣ የመንፈግና የመስጠት መብትን ለተከፋፈሉት ጎሳና ብሔረሰቦች የሰጠ በመሆኑ አንዱ ሌላውን ዜጋ መንፈግ የሚችልበትን፣ አንዱ ከሌላው በልጦ የሚታይበትን የሚስተናገድበትን ሁኔታን የሚፈጥር ሥርዓት ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ይህ ሥርዓት ሁለት ዓይነት ዜግነት ማለትም አንደኛ ዜጋ ሁለተኛ ዜጋ በአንድ ሀገር ውስጥ እንዲኖር የሚያደርግ ሥርዓት የሚሆነው፡፡

የጎሳ ፌዴራሊዝምን ተቀብለን ሁለት ዓይነት ዜግነትን ልንቃወም አንችልም፡፡ ሁለት ዓይነት ዜግነትን የምንቃወም ከሆነ መቃወም ያለብን የጎሳ ፌዴራልዝምን ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደምታስታውሱት መግቢያየ ላይ በገለጽኩላቹህ ምክንያት የተቀሰቀሰው ረብሻ የአዲስ አበባን ዐቢይ የማስፋፊያ አቅድ (Master plan) ወደ መቃወም ዐመፅ ወደተቀላቀለበት ተቃውሞ በተለወጠበት ወቅት ዐመፁ የወያኔን የጎሳ ፌዴራሊዝምን ሥርዓት ክሽፈት ያሳየ ስለነበር ዐመፁን እየደረጉ ለነበሩ ወገኖች “ወያኔ እየተከተለው ባለው የጎሳ ራስ ገዝ ወይም ፌዴራሊዝም ሥርዓት ኦሮሚያ ብሎ ከልሎ ሰጥቷችኋልና ሕገመንግሥታዊ መብታቹህ በመሆኑ መቃወም መብታቹህ ነው! ይሄ ተቃውሞ ግን የወያኔን የጎሳ ፌዴራሊዝም ሥርዓት ከንቱነት ለማጋለጥ ያህል እንጅ ለሌላ ጊዜ ግን ከዚህ ባለፈ ጉዳዩን የምር አድርጋቹህ እንዳትይዙት አደራ! ምክንያቱም እውነታው ይሄ የምትሉት እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለንና!” የሚል ማሳሰቢያ የያዘ ጽሑፍ መጻፌ ይታወሳል፡፡

ወያኔ አዲስ አበባን ኦሮሚያ ብሎ ከሚጠራው የሀገራችን ክፍል ቆርሶ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቁጥጥር ውጭ ነጻ የማዕከላዊ መንግሥት መቀመጫ የማድረግ መብት ይኖረው የነበረው የሚከተለው የራስ ገዝ ሥርዓት ቋንቋንና ዘርን ወይም ጎሳና ብሔረሰብን የተከተለ ባይሆን ኖሮ አንዱ ሲሆን ሌላው አሐዳዊ ሥርዓትን የሚከተል ቢሆን ነበረ፡፡ ምክንያቱም ዘርንና ቋንቋን መሠረት ያላደረገ የፌዴራሊዝም (የራስ ገዝ) አሥተዳደር ለአሥተዳደር አመችነት ብቻ (ያልተማከለ አሥተዳደር ከሚሰጠው ጥቅም ሕዝቡ ተጠቃሚ እንዲሆንና የተሳለጠ አሠራር እንዲኖር) መሠረት አድርጎ ሀገሪቱን በክልሎች ይከፋፍላል እንጅ መሬትን፣ መብትንና ሀብትን (ሪሶርስን) ለጎሳና ብሔረሰብ የሰጠ ባለመሆኑ፣ ሀገርን መብትንና የሀብት አጠቃቀምን ለሁሉም ዜጋ እኩል የሰጠ በመሆኑ ክልሎች ያለክልሉ የመጣውን ዜጋ አያገሉም፣ ከክልላቸው ካለ ዜጋ አሳንሰው አያዩም አያስተናግዱም፡፡ ይሄን እንዲያደርጉም ሕጉ አይፈቅድላቸውም፡፡

ጎሳን ወይም ብሔረሰብን መሠረት ያደረገ የቡድን መብትም ፖለቲካዊ አደረጃጀት እንዲኖረው አይፈቀድለትም፡፡ የመብት ባለቤትነት የሚገኘው በዚህ ወይም በዚያ ጎሳ ወይም ብሔረሰብ አባልነት ሳይሆን በሰውነት ወይም በዜግነት ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም እንዲህ ባለ አሥተዳደር ውስጥ ለሀገር ጥቅም እንደሆነ የታመነበትን ጉዳይ ሁሉ የማዕከላዊ መንግሥትን አቅዶች የክልል የራስ ገዝ መንግሥታት ከብሔረሰብ ወይም ጎሳ ጥቅም አንጻር ዓይተው የማደናቀፍ ዕድል የላቸውም፡፡ ይሄንን የማድረግ መብትም የላቸውም፡፡ በመሆኑም ማዕከላዊው መንግሥት መቀመጫውን ከክልል የራስ ገዝ መንግሥታት አሥተዳደር ግዛት ወስዶ መመሥረትን ጨምሮ የሚይዛቸውን አቅዶች በሀገሪቱ የትኛውም ክፍል ላይ በቀላሉ መፈጸም ይችላል ማለት ነው፡፡ የክልል የራስ ገዝ መንግሥታት ያላቸው ሥልጣን በጎሳ ፌዴራሊዝም አሥተዳደር ውስጥ እንዳሉት ክልላዊ መንግሥታት ፍጹማዊ አይደለም፡፡

አሜሪካን በምሳሌነት መውሰድ እንችላለን፡፡ አሜሪካ የመንግሥቷን መቀመጫ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲን ከቨርጂኒያ እና ከሜሪላንድ ክልላዊ መንግሥታት ክፍለግዛት ቆርሳ ነው የመሠረተችው፡፡ ወያኔ የሚከተለው ቋንቋንና ዘርን መሠረት ባደረገው የራስ ገዝ ሥርዓት ግን ሙሉ ወይም ፍጹማዊ መብትን የሰጠው ለጎሳዎችና ለብሔረሰቦች በመሆኑ ያለ ባለመብት የሆነው ብሔረሰብ አባላት ፈቃድና ይሁንታ ማዕከላዊው መንግሥት ባለመብት ካደረገው ብሔረሰብ የራስ ገዝ ክልል ቆርሶ ከክልሉ አሥተዳደር ነጻ የሆነን የማዕከላዊ መንግሥት መቀመጫ ከተማን ሊመሠርት ከቶውንም አይችልም፡፡ ቋንቋንና ዘርን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ አሥተዳደር መርሖ ይሄንን መብት አይሰጥም አይፈቅድም፡፡ ይህ እንግዲህ አንዱ የወያኔ የራስ ገዝ ሥርዓት ክሽፈት ማሳያ ነው፡፡

እንደሰማቹህት መሰንበቻውን ወያኔ በፌዴሬሽን (በራስ ገዛዊ) ምክር ቤት “የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ለመወሰን!” የሚል አዋጅ አጽድቋል፡፡ ወያኔ ይሄንን ያደረገው አዲስ አበባ የኦሮሞ መሆኗን የሚያምን ስለሆነ የሚመስላቸው ካሉ የዋሀን መሆናቸውን ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡ እንዳልሆነ ልጠቅስላቹህ የምችላቸው ሁለት መረጃዎች አሉ፡፡ አንደኛው በሽግግር መንግሥቱ ጊዜ የሽግግር መንግሥቱ ፕሬዜዳንት (ሊቀ ሥልጣናት) አቶ መለስ ዜናዊ በይፋ በአደባባይ ኦሮሞዎችን “አርፋቹህ ተቀመጡ! በቅርብ ጊዜ ከማዳጋስካር የመጣቹህ እንግዶች ናቹህ!” ብሎ ማሸማቀቁ ይታወሳል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ በቅርቡ ሕዝባዊ ዐመፁ እየተቀጣጠለ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ጊዜ ኦሮሚያ የሚሉትን የራስ ገዝ መንግሥታዊ አሥተዳደሩን ጦር ሠራዊቱ ወስዶ በያዘው ጊዜ ወያኔ በዚሁ ኦሮሚያ ብሎ በሚጠራው የሀገራችን ክፍል ላሉ የኦሕዴድ ካድሬዎች ለሕዝቡ እንዲነግሩ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ ሕዝቡን እንዲሰበስቡና ለሕዝቡ እንዲነግሩ አድርጎ ነበር፡፡ ትዕዛዙ ይሄንን ይል ነበር “ሀገሩ ባለቤት አለው፡፡ ባለቤት የሌለው ሀገር አይደለም የምትኖሩበት፡፡ ከዛሬ ጀምሮ እኛ ሥልጣን የለንም ለሀገሩ ባለቤት አስረክበናል!” የሚል ነበር፡፡ ወያኔ ለኦሮሞ ያለው አመለካከት ይሄ ነው፡፡ ወያኔ ኦሮሞን የሚያውቀው በእንግዳነቱ ነው፡፡ ወያኔ ኦሮሞን ኦሮሚያ ብሎ የሚጠራው የሀገራችን ክፍል ባለቤት አድርጎ ማሳየት የሚፈልገው ከአማራ ጋራ ማሻኮት ማጋጨት በፈለገ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ቀደምም እንደነገርኳቹህ ከአናሳነት የሚመነጭን የአቅም ውስንነት ክፍተት ለመሙላት ወያኔና ሸአቢያ ኦሮሞን መጠቀሚያ በማድረግ አማራን ገትቶ የመያዝ ስልትን ሲጠቀሙ ነበር የኖሩት እየተጠቀሙም ይገኛሉ፡፡ ወያኔና ሸአቢያ አማራና ኦሮሞ በሰላም እስካሉ ወይም ስምም እስከሆኑ ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ዕድል እንደሌላቸው የተረዱት ገና ከድሮው ነው፡፡

በመሆኑም ጥቅማቸውን ሁለቱን አብላጫ ቁጥር ያላቸውን ብሔረሰቦች በማጋጨት ላይ መሠረቱ፡፡ በዚህ ስሌት ምክንያትም ነበረ ሸአቢያና ወያኔ በደርግ ውድቀት ዋዜማ አሶሳ ላይ፣ ደርግ ከወደቀ በኋላ ደግሞ በአርባጉጉ አቦምሳ፣ በበደኖ፣ በአሰቦትና በተለያዩ አካባቢዎች ኦነግን በአማራ ላይ አረመኔያዊ የሆነ ጅምላ ጭፍጨፋ እንዲፈጽም በማድረግ በኦሮሞና አማራ መሀከል ጠላትነት እንዲነግሥ ያደረጉት፡፡ ኦነግ መጠቀሚያ እንዳደረጉት እያወቀ ነው በቂልነቱ ጥቅሜ የሚለውን ከእነሱ ጋር በማበር ማግኘት እንደሚችል አስቦ ከምሥረታው ማግስት ጀምሮ ከሸአቢያ በኋላም ከወያኔ ጋር ተወዳጅቶ የሚፈጽመው ወንጀል “ነገ ምን ዓይነት ውጤት ያስከትላል?” ብሎ አርቆ ማሰብ ማመዛዘን ሳይችል አድርግ ያሉትን በማድረግ የደም ቁርሾ ሊተክል የቻለው፡፡

ወያኔ የሰሞኑን አዋጅ ያወጣውም ግብአተ መሬቱን እያፋጠነለት ያለውን የአማራና የኦሮሞን ሕዝባዊ ዐመፅ የትኩረት አቅጣጫውን ከራሱ ላይ አዙሮ በአማራና በኦሮሞ መሀከል እንዲሆን በማድረግ ነፍሱን ለማትረፍ የሚያደርገው ጥረት መሆኑ ነው፡፡ ኦነግም ሆነ ኦሕዴድና ደጋፊዎቻቸው ከወያኔ ጋር በመሆን ምን ያህል አግባብነት የሌለው ጥቅም ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር ምናልባት ሰዎች ናቸውና ተደጋግሞ ሲነገራቸው ይረዱ፣ ይገባቸው ይሆናል በሚል ተስፋ ከዚህ ቀደም ደጋግሜ የተናገርኩትን እውነት አሁንም እናገረዋለሁ፡፡ ይሄንን የምናገረው በዚህች ሀገር ላይ ሰላም እንዲሰፍን የሚፈልግ ካለ ሰላም ለማስፈን ብቸኛው አማራጭ ይሄ በመሆኑ እንደሆነ እንዲያሰምሩበት እወዳለሁ፡፡

ኦነግና ደጋፊዎቹ እስከመቸ ድረስ መጠቀሚያ እንደሚሆኑ አይገባኝም፡፡ አሁን ላይ ሆነን ስናየው የኦሮሞ ሕዝብ በታሪክ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ሆኗል፡፡ ተዋልዷል ተጋብቷል ተዋሕዷል፡፡ እንዲያውም ከኦሮሞ ሕዝብ ኦሮሞ ነኝ ብሎ ከሚያስበው ከግማሽ በላይ የሚሆነው ኦሮሞ ባደረገው የመስፋፋት ዘመቻ በኃይል ኦሮሞ እንዲሆኑ የተደረጉ የሌላ ብሔረሰብና ጎሳ አባላት ናቸው እንጅ የኦሮሞ ደም ያለባቸው እንኳ አይደሉም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ የዚህን ያህል ነው የደም አንድነት የሌለው ወይም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተዋሕዶ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል የሆነው፡፡ ዛሬ ላይ ግን ጥቂት የማይባሉ የኦሮሞ ተወላጅ ነን የሚሉ ቡድኖችና ግለሰቦች በዚህ ታሪካዊ ዕድል ብቻ ሊረኩ ባለመቻላቸው እላፊ ነገሮችን በመጠየቅ ላይ እንደቆዩ ይታወቃል፡፡ በዚህን ጊዜ ታዲያ አንዳንድ ነገሮችን እንድናስታውሳቸው እንገዳለንና እሱን እናነሣለን፡፡

እነኝህ በኦሮሞ ሕዝብ ስም እየነገዱ ያሉና የኦሮሞን ሕዝብ ለማሣሣት እየተጣጣሩ ያሉ አካላት ኦሮሞ አሁን ቅርብ ጊዜ ማለትም በ16ኛው መቶ ክ/ዘ የግራኝ አሕመድ ወረራ ድል የፈጠረለትን ክፍተት ወይም መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ከሶማሊያ ቤናዲር ተነሥቶ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ፈጽሞ የረሱ ይመስላሉ፡፡ ይሄንን እውነት ካሉ ታሪካዊ መረጃዎች በተጨማሪ ስለራሳቸው ይናገሩት ከነበረው አፈታሪክና ከባሕላቸው ውስጥ ካለው ትውፊታዊ መዝሙራቸውም መረዳት ይቻላል፡፡ በሶማሌዎችና በባንቱዎች ከላይና ከታች እየተወጉ ሲሰቃዩበት ከነበረው ሱማሌ ቤናዲር ለቀው ወደኢትዮጵያ ገብተው ከተቀመጡባት እንደገነት ከሚቆጥሯት ወላቡ ስለነበራቸው የደስታ የፍስሐ ዘመን ከሚያወዳድሰው ትውፊታዊ መዝሙራቸው ይሄንን እውነታ መረዳት ይችላሉ፡፡
ሶማሊያ ገብተው ረዘም ላለ ዘመን ከመቆየታቸው አስቀድሞም ማዳጋስካር እንደነበሩ ይነገራል፡፡ ይሄንንም ታሪክ የታሪክ ጸሐፍት ጽፈውታል፡፡ ጥቂቶችን መጥቀስ ካስፈለገም፡፡

የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት አቶ 1ኛ. ይልማ ደሬሳ ስለ ኦሮሞ ጥልቅ መረዳት ካላቸው አባገዳዎች ያገኘሁት መረጃ ነው ብለው “የኢትዮጵያ ታሪክ በ16 መቶ ክ/ዘ” በሚለው መጽሐፋቸው፣ 2ኛ. ተክለ ጻድቅ መኩሪያ “የግራኝ አሕመድ ወረራ የሚለው መጽሐፍና የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ”፣ 3ኛ. አለቃ ታዬ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ” ፣ 4ኛ. አባ ባሕርይ ስለ ኦሮሞ አገባብ በጻፉት መጽሐፍ፣ 5ኛ. ዐፄ ልብነ ድንግል በግራኝ ሲሸነፉ ለፖርቹጋሎች ባቀረቡት የእርዳታ ጥሪ መሠረት አብሮ መጥቶ የነበረውና የኢትዮጵያ ጳጳስ ካልሆንኩ ብሎ ከዐፄ ገላውዴዎስ ጋር የተጋጨው ቤርሙዴዝ ሀገሩ ሔዶ ስለ ኢትዮጵያ በጻፈው መጽሐፍ፤ እነኝህ ጸሐፍት ኦሮሞ ወደ ኢትዮጵያ ገባ የሚሉበትን የተለያየ ዘመን ያስቀምጡ እንጅ ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ መምጣቱን ያረጋግጣሉ፡፡

ተ/ጻድቅ መኩሪያ በመጽሐፋቸው ላይ “ኦሮሞ የገባው በ16ኛው መቶ ክ/ዘ ከግራኝ ወረራ በኋላ ከሆነ ከዚያ በቀደመው ዘመን እነ አዛዥ ጫላ፣ አነ ላሎ፣ እነ አጋፋሪ ቱሉ ከግራኝ አሕመድ ወረራ በፊት በእነ ዐፄ ዓምደ ጽዮን፣ በእነ ዐፄ ልብነ ድንግል ታሪከ ነገሥትና ዜና መዋዕሎች ላይ እንዴት ሊገኙና ስማቸው ሊጠቀስ ቻለ?” ሲሉ ይጠይቁና ኦሮሞ ከ16ኛው መቶ ክ/ዘ በፊት እንደገባ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ የተጠቀሱት ግለሰቦች በዚያ ዘመን እዚህ ሊገኙ የቻሉበት ምክንያት ግን ኦሮሞ ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበረ ሳይሆን ኦሮሞ ከነበረበት ሞቃዲሾ አቅራቢያ ወይም ከቤናዲር እየተነሣ ለከብት ዝርፊያና ለወረራ ይመጣ ስለነበር በእንደዚህ ዓይነቶቹ አጋጣሚዎች ተማርከው የሚቀሩት ግለሰቦች በታማኝነታቸውና በጉብዝናቸውም ሞገስ እያገኙ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን እንደታየው በጦርነት ተማርከው መጥተው ለአዛዥነትና ለሥልጣን እንዲበቁ እንደተደረጉት እንደነ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴና ሌሎች እነኝህም ተመሳሳይ ዕድል ገጥሟቸው በዚያ ዘመን ሊገኙ ስለቻሉ ነው፡፡

ከነኚህ የታሪክ መዛግብት ምስክርነት በተጨማሪም ዛሬ ኦሮሞ ሰፍሮ ባለበት ከታች እስከ ላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ግራኝ ያፈራረሳቸው በርካታ የጥንታዊ አብያተክርስቲያናትና ገዳማት ፍርስራሾች ያሉ መሆናቸው ነው፡፡ ይሄ ሊስተባበል የማይችል ተጨባጭ መረጃ ነው፡፡ ግራኝ አሕመድ ነባሩን ሕዝብና መንግሥት ወደ ሰሜን እየገፋ እየጠረገ ነጻ ባደረገበት ወቅት ነው ገብተው ለመስፈር የበቁት፡፡ የቀረውንም በቱርኮች በዓረቦች በፋርሶችና በሕንዶች ተዋጊዎች ታግዞ ሀገሪቱን ለ15 ዓመታት ባደቀቃት አረመኔያዊ የግራኝ አሕመድ ወረራ የተዳከመውን ሕዝብና መንግሥት በመውጋት ነው አሁን የያዙትን የሀገራችን ክፍል ነባር ስማቸውን እየቀየሩ ዳሞትና ቢዛሞ የነበረውን ወለጋ፣ ጠፈርጋ የነበረውን አርሲ፣ ደዋሮ የነበረውን ሐረርጌ፣ ላኮመልዛ የነበረውን ወሎ ብለው እንደያዙ የቀሩት፡፡ እስከ ጃንሆይ ጊዜ ድረስ እነዚህ ነባር ስሞች ያገለግሉ ነበር፡፡ የእነሱ ሰዎች በርትተው በመጣራቸው አዲሱን ኦሮምኛ ሥያሜዎቻቸውን እኛንም ሳይቀር አስለምደው ዛሬ ሀገሩ ሁሉ ከድሮውም የእነሱ የነበረ እስኪመስል ድረስ በኦሮምኛ ሥያሜዎች ሊሞሉት ቻሉ፡፡ አዲስ አበባን ነጥለን ማየት ካስፈለገ አዲስ አበባ ከ229ዓ.ም. እስከ 461ዓ.ም. ድረስ ከአክሱም በተጨማሪ ለ232 ዓመታት ያህል ከነኢዛና እና ሳይዛና እስከ አምሲ ድረስ የረር በመባል በሚታወቀው ምሥራቃዊ ተራራማ ክፍሏ ላይ ከእስራኤል ንጉሥ ከጠቢቡ ሰሎሞን ልጅ ከቀዳማዊ ምኒልክ ለሚጀመረው ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት ዋና መቀመጫ የነበረች ታሪካዊት ከተማችን ነች፡፡ ይሄንንም እዛው ከስፍራው የረር፣ በአቅራቢያውና በዙሪያው ሁሉ በግራኝ አሕመድ ወረራ ክፉኛ በፈራረሱ በርካታ ጥንታዊ አብያተክርስቲያናትና አብያተመንግሥታት አሻራዎችና ፍርስራሾች አሁንም ማረጋገጥ የሚቻል ጉዳይ ነው፡፡

ታዲያ ሀቁ ይህ በሆነበት ሁኔታ ለዚህች ሀገር የቅርብ ጊዜ እንግዶች ሆነው እያለ እንዴት ነው እሱ አዲስ አበባ የኛ ናት፣ እንገነጠላለን፣ ቋንቋችን የሥራ ቋንቋ ይደረግ ምንትስ ሊሉ የሚችሉት? የጥፋት ኃይሎች የኢትዮጵያን ታሪክ በመቶ ዓመታት ገድበው ሁሉም ነገር ከዚህ በመነሣት እንዲለካ የሚፈልጉበት ምክንያት ከላይ የተገለጸውን ታሪክና ቅርሶችን ማስተባበል ስለማይችሉና ፈጽሞ አግባብነት የሌላቸው ጥያቄዎቻቸው ሊስተናገድላቸው እንደማይችል ስለተረዱ ነው፡፡ ነገረ ግን ይሄ ብልጠት ምን ያህል ያስኬዳቸዋል? “ውንብድና ሕጋዊነት ያግኝና የበረታ ይዝረፍ!” እያሉ እንደሆነ ይገባቸዋል ወይ? ለዚህ የውንብድና ተግባር ያለ የሌለ ኃይላቸውን አንጠፍጥፈው እየተረባረቡ እያለ እንዴት ብለው ነው ስለፍትሕ፣ ስለ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) ፣ ስለ መብት፣ ስለ እኩልነት፣ ስለ ሰብአዊ መብት ሊያወሩ የሚችሉት? እነዚህ ሰዎች ፊደል የቆጠሩ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ለሞራል (ለቅስም) ድንጋጌዎች የሚገዙና ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ የዚህ ተግባራቸው አግባብነቱ እንዴት ይታያቸዋል?

ይሄንን ፍጹም አግባብነት የሌለው ኢዲሞክራሲያዊና ኢፍትሐዊ ጥያቄያቸውን ኢሞራላዊ በሆነ ድርቅና ማስፈጸም የሚችሉ ይመስላቸዋል ወይ? “እነኝህን የውንብድና ጥያቄዎቻችንን ወይም ፍላጎቶቻችንን ካልተቀበላቹህ ወይም እኛን ካላጠፋቹህን በስተቀር ፍጹም አብረን መኖር አንችልም! ወይ እናንተን እናጠፋለን ወይ ደግሞ እናንተ ታጠፉንና እንገላገላለን እንጅ!” የሚል ነውረኛ የሆነ ጽንፈኛ የውንብድና መልእክት እያስተላለፉ እንደሆነ ይገባቸዋል ወይ?

እንዲህ ብለው ድርቅ ሲሉ እኛ ደግሞ “ሕሊናና እፍረት የሚባል ነገር ከሌላቹህማ ወደ መጣቹህበት ተመለሱ! ውጡልን!” ብንል መግቢያ ይኖራቸዋል ወይ? ይሄንንም ቢያስቡ መልካም ነው፡፡ እንዲያው እውነቴን ነው የምላቹህ ተምሬያለሁ የሚሉና ይሄንን እፍረተቢስ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ አካላትና ግለሰቦች ሕሊና ካላቸው በራሳቸው ሊያፍሩ ሊሸማቀቁ ይገባቸዋል! በዚህ ካላፈሩ ሊቀረፍ የማይችል የሰብእና ድንቁርና (personality stupidity) እንዳለባቸው ሊያረጋግጡ ይችላሉ፡፡

እንግዲህ ይሄው ነው ያለው ነገር፡፡ “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል!” ብለን የተረትነው ነገር ነው የደረሰብን፡፡ የዋህነታችንን እንግዳ ተቀባይነታችንን አለአግባብ እጅግ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ የምናያቸውን ያህል እንዲሳሳቱ እያደረገ በመሆኑ በምንም ዓይነት መልኩ ይሄ የዋህነት መቀጠል አይኖርበትም፡፡ ሁሉም ኦሮምኛ ሥያሜዎች ቀሪ ሆነው ወይም ተሠርዘው ነባር ስሞች መልሰው አገለግሎት ላይ መዋል ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ኢሞራላዊ (ኢቅስማዊ) እንቅስቃሴዎቻቸው የማይታረሙ ከሆነና የሚቀጥሉ ከሆነም እንዲህ አግባብነት የሌለውን ጥያቄ የሚያነሡትንና የሚበጠብጡትን እየለየን ወደመጡበት እስከመመለስ የምንገደድ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል! እነሱ ትናንትና መጥተው ወርረው ከያዙብን ከገዛ ሀገራችን “አሮሚያ ለኦሮሞ ብቻ! ፣ ከሀገራችን ውጡልን!” ምንትስ ቅብርጥስ እያሉ መዓት ነገር ሲያወሩ ያላፈሩትን ይልቁን እኛማ እንዴት እንፈር? እንዴትስ ነው ይሄንን ማለት የማንችለውና የማይገባንስ???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.