ሰበር መረጃ…….. የወያኔ ሶሻል ሚዲያ ሰራዊት ተሸነፈ – ልኡል አለሜ

በ2008 የህወሃት ፖለቲካ ዘርፍ ሐላፊዎች እና ብሄራዊ መረጃዎች ባጠኑት ጥናት መሰረት የወያኔ መንግስት የመጨረሻዉ ገደል አፋፍ ላይ መዉደቁን የሚያመላክት ነበር ለዚያም የስርአቱ መንኮታኮት ዋነኛዉ የጦር ስምሪት ማሕበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ማለትም ፌስ ቡክ፣ ትዊተር፣ ዋትሳፕና የመሳሰሉት እነደ አንድ ጠላት ተፈረጁ። በጦርነቱም ላይ ለመሳተፍ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዉስጥ ሰርጎ ገብቶ የሚያጠቃ 50.000 የሚጠጉ የመሐበራዊ መገናኛ አጥቂና ተከላካይ ሰራዊት ( Social Media warriors ) በመገንባት ወደ ጦርነቱ በይፋ ገባ በዚያም ወቅት ጦርነቱ መጀመሩን አዲስ እራይ የሚባለዉ የህወሃት ልሳን አወጀ።

ይሁን እንጂ ከፍተኛ በጀትና ወጪ ተመድቦለት የተዋቀረዉ የህወሃት ሶሻል ሚዲያ ሰራዊት ስርአቱን ከዉድቀት ለመታደግ ወይም ጥቃቶችን ለመከላከልም ሆነ በቂ ምላሽ ለመስጠት አልቻለም ሲሉ የሰሞኑ የሚዲያ ግንባታ ክፍል ሰራተኞች ሪፖርት ማቅረባቸዉን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል በዚህ ሪፖርት ዉስጥ። ችግር ተብለዉ የተጠቀሱት 

1. በሰራዊት ደረጃ ተመልምለዉ በሚዲያዉ ላይ የተሰማሩት አባላት ከወዲያኛዉ አካል በሚሰነዘሩ የጥቃት ይዘቶች በመማለላቸዉ
2. በብሔር ተኮር የማጋጨት ስራ ላይ በቂ የሆነ ስልት መጠቀም ባለመቻላቸዉ
3. ከወዲያኛዉ አካል በብሎክ በመጠራረጋቸዉ
4. በትዊተር ዘመቻ ላይ እንደምሳሌ ሆኖ የቴድሮስ አድሐኖም አይመረጥም ዘመቻ ላይ በታየ ጥቃት ፈጽመዉ መከላከል አለመቻላቸው
5. በቂ የሆነ የጽሁፍ ስልጠና ስለሌላቸዉ አርእስት ይዘዉ የመጻፍና የምላሽ ብቃት ላይ ዜሮ በመሆናቸዉ
6. በተቃራኒ አካል ቆመዉ የሚተኩሱ ጸሀፍት ሚዲያ ሰራዊቶች እጅግ አደገኛ በመሆናቸዉ 

እና የመሳሰሉት ሲሆኑ ሶሻል ሚዲያ ሰራዊቱ ፈጽሞ አገልግሎት እየሰጠ ባለመሆኑ ስረአቱን ለመከላከል በሚደረገዉ እርብርብ ላይ አይነተኛ ተሳትፎ ለመስጠት የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚዲያ ግንባታ ዘርፉ ሐላፊዎች አበክረዉ አስታዉቀዋል።\

ህወሃት ወያኔ አሁን ከገባበት ከፍተኛ አጣብቂኝ የተነሳ የተለያዩ ስልቶችን ቢጠቀምም እየፈጠነ ከመጣዉ ዉድቀት ለማገገም ፈጽሞ የማይቻልበት ሁኔታዎች ዉስጥ መግባቱን ያመላከቱት ምንጮች አያይዘዉ እንደጠቆሙት በተለያዩ ግንባሮች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጦርነቶችን በህወሃት ልሳነ ሚዲያ ይፋ እንዲደረግ የሚጠይቅ ትእዛዝ በመምጣቱ የሚዲያ ዘርፉ በዚህ ጉዳይ ላይ ባለመስማማት ለሁለት ተከፍሎ እየተነታረከም እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.