ተክለ ሚካኤል አበበ-ግራህን ለመምረጥ-አይገባህም ቀኝህን መቁረጥ – ከወንድወሰን ተክሉ

**አንድ-የጽሁፌ መነሻ-
ሲጀመር በቶሮንቶ የአግ7 ስብሰባ ላይ ለፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ላቀረበው ጥያቄ የፍላጎቱን መልስ ባለማግኘት ንዴት የተክሌ የበላበትን ወጪት ሰባሪ እሚያደርገውን ድርጊት በፕ/ሩ ላይ ተከታታይ የማጥላላት ዘመቻ ሲያጣጡፍ ተመልከትኩ። በአንድ ወቅት “Inspire ” አድርጎኛል ያላቸውን መምህሩን ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን “ወረደብኝ..እታች ወርዶ አነሰብኝ..” እያለ ባብጠለጠለበት ፓልቶክ ላይ ስለ አቶ ልደቱ አያሌው ያለውን ያልተለወጠ እና እማይለወጥም ፍቅርና ጥብቅናን ሲተርክ ሰማሁት። ሰሞኑን ደግሞ በሲያትሉ የኢትዮጵያዊያን በሰሜን አሜሪካ እስፖርትና ባህል ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናት ከታደመ በሃላ በዘ-ሐባሻ ላይ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳን፣አርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁንን [ቴዲ አፍሮ]የፌስቲቫሉን ጠቅላላ ታዳሚ፣ኢትዮጵያዊነትን፣ሰንደቅ ዓላማን እና አማርኛን ለኦሮሚኛ፣ለባለኮከባማው ባንዲራ እና ለእነ ጁሀር መሀመድ የቁቤው ቄሮ ትውልድ ያለውን ፍቅርና ወገናዊነትን ለመግለጽ ሲል ክፉኛ ሲያብጠለጥላቸው ሰማሁ። በተክሌ መብጠልጠል ኢሳት፣ተቃዋሚዎች በተለይም የአንድነት ሃይሎችም አልተረፉም።
በእርግጥ ተክሌ ለተማገተላቸው ግራዎቹ ተቆርቁሮ፣አምኖበትና የአመለካከት ለውጥ አድርጎ ነውን? መልሱን እራሱ ይመልሰዋል እንጂ እኔ እንደ እሱ ልመልስለት አይቻለኝምና እሱን ለእሱ ትቼ ይመንበት አይመንበት በተናገራቸው ላይ መልስ መስጠት በማስፈለጉ እነሆኝ ብእሬን አነሳሁ። የጽሁፌ አስካልም ተክለሚካል አበበ ኦሮምኛ በአማርኛ ስለመጨቆኑ፣ባለኮከቡም ባንዲራ የኢትዮጵያውያን ምርጫ ባንዲራ ስለመሆኑ፣ኢትዮጵያዊ አንድነት በአርቲስት ቴዲ አፍሮ ዘፈኖች እና በፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ “ጎሰኝነትን አስወግደን ኢትዮጵያዊነትን እናለመልማለን” ትምህርት እንዴት የኢትዮጵያ ህልውና ስጋት ምንጭ ተደርገው በተገለጹት አባባሎቹ ዙሪያ እንዲወሰኑ በመወሰን የተቻለኝን ጥሬያለሁ።

ወንድወሰን ተክሉ

ተክሌን ማእከል ያደረገ ጽሁፍ ስጽፍ ይህ የመጀመሪያዪ አይደለም። ማንም ስለተክሌ አረፍተ ነገር ሳይጭር እኔ በመጽሄት ደረጃ ገና ተማሪ እያለ የጻፍኩ እና ኢንተርቪው ያደረኩት ሰው ነኝ። ግን የአሁኑ ጽሁፌ ያኔ በ1992 መገባደጃ ላይ በጎሕ መጽሄት እና በ1993 በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ስለተክለሚካኤል አበበ እና ጋደኞቹ መስፍን ገብረስላሴ እና የአ.አ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከጻፍኩት በእጅጉ ይለያል። ኬኒያም ከገባሁ በሃላ እየጻፍኩ በሀገር ቤት እንዲታተሙ ካደረኩት በይዘትም ሆነ በአቀራረብ ይለያል እንጂ የመጀመሪያዪ አይደለም።
**ሁለት-የተክሌ ግራውን ለመምረጥ ቀኙን አጣጥሎ የመቁረጥ አበዜ

ባለፈው ዓመት የትግራይን ህዝብ በኢትዮጵያ ሕዝብ በህወሃት ዓይን መታየት እና በጅምላ የመፈረጅን አዝማሚያ አግባብ ያለመሆን በስልክ ተወያይተን በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ እኔና ተክሌ እንደተስማማን ተክሌ ቀድሞኝ ጽሁፉን ለቀቀው። የጹሁፉ ይዘት እና መንፈስ የትግራይን ሕዝብ በጅምላ በህወሃት ዓይን በመፈረጅ ድርጅቱ ለሚሰራው ወንጅሎች ተጠያቂ አድርገን አንፈርጀው የሚለውን ፍትሃዊውን አመለካከት ተክሊሻ የአማራውን ጨቃኝነት ተጠቃሚነትን እና የበላይነትን እያጣቀሰ አቀረበና ብልሽትሽቱን አወጣው። ደወልኩለት እና የትግራይን ህዝብ በህወሃት ዓይን አንይ ለማለት ለምን የአማራውን ጉዳይ ማካታት አስፈለገ? የአማራው ጉዳይ እራሱን የቻለ ትልቅ አርእስት አይደለም ወይ አልኩት፣ ተክሌም “እውነትህን ነው-ማካተት አልነበረብኝም ..” አለኝ። ይህ እንግዲህ ባለፈው ዓመት የውግዘት ጎርፍ የጎረፈለት ጽሁፉ ነበር። ዛሬም ከዓመት በሃላ በሀገሬ -በኢትዮጵያዊነት፣በኢትዮጵያዊ አንድነት እና በሰንደቅ ዓላማችን ላይ አማርኛ ቃንቃ፣የአማራው ባህል እና የቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ ” እና “ጎንደር ጎንደር” ዘፈን እንደ የኢትዮጵያ ህልውና የስጋት ምንጭ አድርጎ ያለምንም ይሉኝትና እና እፍረት ሲገልጽ ሰማነው።በሲያትሉ ፌስቲቫል [ተክሌ የአማራ ፌስቲቫል ነው ያለው] ባለኮከባማው ባንዲራ ነበር መሰቀል የነበረበት፣ኦሮሚኛ በአማርኛ ተገፍትሮ ተጨቁናል የቴዲ አፍሮ ዘፈን ያሰጋኛል፣የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጎሰኝነትን አስወግደን ኢትዮጵያዊነትን እናለመልማለን ንግግር በጣም አናዶኛል እያልክ ተውረገረክ። እናም እስቲ እንየው መሰረት ይኑረው ትችት ወይም መሰረት አልባ የሆነ እንደሆነ።

**ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ

ባለኮከባማው ባንዲራ በ1987 ዓ.ም በጸደቀው ሕገ-መንግስት የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት የሚወክል ምልክት ብሎ የገለጸው ውጤት ነው።ሕገ-መንግስቱ ይህንን ስለአለ በእርግጥ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚወክል ባንዲራ ነውን? እንደ አንተ አባባል አዎን ይወክላል ሲሆን እኔ ደግሞ የለም ተሳስተሃል አይወክልም እልሃለሁ።ምክንያቱም ሕገ-መንግስቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮቹን መርጦ እኔ እና አንተ እንዳየነው ቢያንስ እንደ ኬኒያ በተወካዮቹ ተረቆና መጨረሻም ለህዝበ ውሳኔ ቀርቦ የጸደቀ አይደለም። [የኢሰፓ ሕገ-መንግስት እቀበለዋለሁ -አልቀበለውም የሚል የይስሙላም እንካን ቢሆን ህዝበ ውሳኔ ተደጎበታል] በ1987 በአቶ ክፍሌ ወዳጆ የተመራው ሕገ-መንግስት አርቃቂ ኮሚቴ በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ግቤ በኢህአዴግ በተመረጡ ተወካዮች በአቶ መለስ ዜናዊ የቀጥታ ትእዛዝ ተቀርጾ የጸደቀን ሕገ-መንግስት እንደ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና ውሳኔ አድርጎ መግለጽ አላማውን መገመት ባልሻም ፈሩን የሳተ መሆኑን ግን ሳልገልጽ አላልፍም።

**በፌስቲቫሉ ላይ የታየው ልሙጡ አረንጋዴ፣ቢጫ እና ቀይ ባንዲራ እንዴት ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ መገለጫ ህጋዊ ባንዲራ የሆነው?

ከሺህ ዓመታት በፊት ሰንደቅ ዓላማችን አረንጋዴ፣ቢጫ እና ሰማያዊ ቀለማትን ተሰጥታት ተፈጠረች።ትርጋሜውም ልምላሜ፣አንድነት እና መንፈሳዊነትን የሚወክል ማለት ነው። ከዓመታት በሃላ ሀገራችንን ለመውረር በሚመጡ የውጭ ሃይሎችን ለመከላከል እየተከፈለ የመጣው መስዋእትነት ስለበዛ መስዋእትነቱን ለመዘከር ሰማያዊው ቀለም በቀይ ቀለም እንዲተካ ተደረገ። አረንጋዴ፣ቢጫ እና ቀዩ ባንዲራ ሕዝብን እና ሀገሪታን ኢትዮጵያ በመወከል ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ሲሆን በየትውልዱ የተነሱት ነገስታትም የመረጡትን እና ይወክለኛል ያሉትን የመንግስታቸውን መለያ ምልክት ዓርማ በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ በማስፈር እየተጠቀሙ አልፈዋል። እያንዳንዱ ነገስት የራሱን ዓርማ እየለዋወጠ ሲያስቀምጥ አረንጋዴ፣ቢጫ እና ቀያ ባንዲራ ሕዝብን በመወከል ሳትለወጥና ሳትቀየር የኖረች ሰንደቅ ዓላማ ነች። [የቅርብ ዘመኑን የአጼ ቴውድሮስ፣የአጼ ዮሃንስን፣የአጼ ምንሊክን፣የአጼ ሃይለስላሴን እና የኢሰፓን ተመልከት]

ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ የተባለው ዙፋናዊው ስርዓት ያሻውን ህግ እና ዓርማ አውጥቶ የሀገርና የህዝብ ነው ቢል ዘመኑ ነበርና ምንም አይደረግም የሆኖው ሆኖ አልፎዋል። ከ40ዓመት በሃላ ኢትዮጵያውያን ሁለት ሕገ-መንግስት እና ሁለት ሰንደቅ ዓላማ መክረው ሳይመርጡ የእናንተ ነው ተብለው ተጭኖባቸዋል። ሁለቱም የእኛ አይደለም ማለታቸው ፍትሃዊ እውነታ ነው። በኢሳፍና የተውለበለበችው ሰንደቅ ዓላማ እውነተኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ማንኛውንም አገዛዝ የማይወክል ግን ህዝቡን እና ሀገሪታን የሚወክል ባንዲራ በመሆኑ ተገቢና ትክክለኛ ሲሆን የአንተው ምርጫ ባለኮከቡ ባንዲራ ግን ስርዓቱን [ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት] የሚወክል እንጂ ብሔርብሔረሰብን የሚወክል እንዳልሆነ አሳይቻለሁ።

***የኦሮሚኛ ቃንቃ በአማርኛ ቃንቃ ተጨቁናል የሚለውን ክስህን በተመለከተ

በእኔ እና በአንተ ዘመን ኦሮምኛ በአማርኛ ተጨቁናል? የሲያትሉ ክስተት አንተን ኦሮምኛው በአማርኛ ተጨቁናል እንድትል አደረገህ ? ወይስ ያልበለውን እንደሚያክክ ያልኖርክበትን እየተረክ ነው ያለህው? ዘመንህን ዋጅ ይላል የእግዚአብሔር ህያው ቃል። አንተም ሆንክ እኔ ዘመናችንን ነው እጂ እምንቃኘው የትናንቱን ያን ያለፈውን ዛሬ ላይ አምጥተን በዛሬው ብቃት፣አቅም፣እድል እና በዛሬው ችሎታ ልንመዝነው ብሎም ልንፈርደው አይቻለንም። ያ-ትናንት-መልሰን እማንጋልበው የሞተ ፈረስ ሲሆን በአስተማሪነቱ ግን ሃያል ሞተር ሆኖን ያገለግለናል። በእኔ እና በአንተ ዘመን ኦሮምኛ በአማርኛ ተጨቆነ ካስባለህ አሁንም መንገድ ስተሃል። በሲያትል ብቻ አይደለም በየሄድክበት አማርኛ ብቻ ልትሰማ ትችላለህ። ኦሮምኛ ወይም ትግሪኛ ብቻ የምትሰማበትም ዝግጅቶችና ስፍራዎች ሞልተዋል ወደፊትም ይገጥምሀል።ግን ኦሮምኛና ትግሪኛ አማርኛን ጨቆኑ ማለት አይደለም።

የቃንቃን እኩልነት ህዝቦችን በግድ እንዲናገሩትና እንዲጠቀሙበት ማድረግ ማለት አይደለም። የኦሮምኛን ቃንቃ ለመውደድ እና ለማሳደግ አማርኛን በመጥላትና ያላግባብ በማጠልጠልም አይደለም። የአማርኛ ቃንቃ ከ11ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቃንቃ ሆኖ የኖረ የ81ብሔር ብሔረሰቦች የስራና የመግባቢያ ቃንቃ ነው። ለምን ሆነ -ሌሎች ቃንቃዎች ተጨቁነው ነው ብለህ አትፈላሰብኝ-የሆነው ሆናል በማይለወጥ ደረጃ። ዛሬ ነገዶች በአፍ መፍቻ ቃንቃቸው እንዲማሩና ብሎም እንዲሰሩ ባወጀው መንግስትም አማርኛ ቃንቃ የፌዴራሉ መንግስት ብሔራዊ ቃንቃ ሆኖ እያገለገለ ያለን ቃንቃ በሲያትል ፌስቲቫል ላይ ዶሚናንት የሆነው ኦሮምኛን ጨቁኖ ነው እንድትል ማድረጉ ልጁ መጨቆን ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙ ሳይጠፋበት አይቀርም እንድል አድርጎኛል።

በህግ ደረጃ የቃንቃ እኩልነት ከታወጀ 40ዓመት ሞልቶናል። ላለፉት 26ዓመታት ደግሞ ቃንቃ አፍቃሪ እና አምላኪ ተደርገናል። በእነዚህ ዓመታት በቃንቃ ላይ ያነጣጠረ ጭቆና እና ጥቃት ከኦሮምኛው ይበልጥ አማርኛው ላይ ያነጣጠረ ነው ማለት ይቻላል። ይህው አንተ እንካን በአቅምህ ትናንት በልጅነትህ የአፍ መፍቻ ቃንቃዪን አልተውም ብለህ በመምህራኖችህ የተቀጣህበት የአማርኛ ቃንቃን ጨቃኝ ነው- ኦሮምኛን ጨቁናል ስትል ባያስደስተኝም ግን ብለሃልና የአማርኛን ዘርፈብዙ አጥቂዎቹን እያየን ነው።

በነገራችን ላይ የኦሮምኛ በአማርኛ ተጨቁናል ድምዳሜህ በከፊል እውነታነት ያለው ሆኖ አይቼዋለሁ።ኦሮምኛ በአንተ-በኦሮሚያ ምድር በሆነችው ነገሌ ተወልዶ ባደገው ተክለሚካኤል አበበ ክፍኛ ተጨቁናል። እኔ በኦሮምኛ ቃንቃዪ አስማምቼ ብሸጥህ መምለጥ የማትችል የኦሮምኛ ዱዳ የሆንክበት ምክንያት ቃንቃውን ስለጨቆንክ ነው። እኛን ግን አትደምረን እዚያ ውስጥ። በአዲስ አበባ እና ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቃንቃቸው ካልሆነው ቤተሰቦች የተወለድኩት እኔ አንተን በኦሮሚያ ምድር ተወልደህ ያደከውን ልጅ በኦሮምኛ ቃንቃዪ አስማምቼ ብሸጥህ እማትሰማ የኦሮሚፋ ዱዳ ነህና ተክሌ። ስለዚህ ኦሮምኛ እና አማርኛ ዛሬ አንተ እንዳልከው እየተጨቃቆኑ አይደለም። እየተግባቡና እየተባበሩ እንደሆነ እረዳለሁ።

አንተም ንሰሀህን [በኦሮምኛ ላይ ያለህን አመለካከት ማለቴ ነው] ኦሮምኛን በማፍቀር፣በማድነቅ እና ብሎም ቃንቃውን ለማወቅ በመጣር ልታካክሰው ትችላልህ እንጂ በአንድ ወቅት ከአማርኛ በስተቀር ኦሮምኛ ለምኔ ያልከው ልጅ ምልስ ብለህ አማርኛን እንደጨቃኝ እና ኦሮምኛን ደግሞ እንደተጨቃኝ በመግለጽ መሆን የለበትም። አማርኛን ሳትከስና ሳታጣጥል ልክ እንግሊዘኛን ከአማርኛህ ጋር አቻችለህ መጠቀም እንደጀመርክ-የኦሮምኛን ቃንቃ መውደድ፣ማክበርና ለእድገቱም መስራት ትችላለህ። ግን አሁን ያሳይህን አካሄድ አፖሎጄቲክ አፕሮች ይመስላል። ግን ያ-እራስን ጠልፎ ጣይ [ሱሳይዳል] ነው የምልህ።

*** ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፣ኢትዮጵያዊነት እና የቴዲ አፍሮ ዘፈን፣የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በተመለከተ

ለመሆኑ ምን የሚያናድድ ነገር ተናገሩና ነው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳን “እኔን በጣም ያናደደኝ ፍቅሬ ቶሎሳ ጎሰኝነትን አጥፍተን ኢትዮጵያዊነትን እናለመልማለን ማለቱ ነው ” ያልከው? ክፋቱ ምኑ ላይ ሆኖ ነው እስከመናደድ ያደረሰህ? በእርግጥ ለሀገራችን ህልውና ተቆርቁረህ ነውን? ፕ/ሩ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ይልምልም ኦሮሚያ ትገንጠል ኢትዮጵያ ትበጣጠስ ማለት ነበረባቸው የአንተ አንጀት የደስታ ቅቤ እንዲጠጣ? በእርግጥ በአንድ ወቅት ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ በጆሮዪ ስለሀግራችን ጉዳይ ሳነሳልህ [Who cares ?] ያልከኝን በማስረጃ እያረጋገጥክ ትመስላለህ አንተ በቴዲ አፍሮ ዘፈን እና በፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ንግግር አንዴ “ሰጋሁ” ቀጥሎም “በጣም ተናደድኩ” የሚለውን ስሰማ። ግን ወንድም ተክሌ ደጋግመህ በጆሮዪ I am a business man እያለክ እንደነገርከኝ እና ብሎም
Who cares ?] ካልክ Why you care this time round about our beloved country ? ተብለህ ብትጠየቅ መልስህ ምንድነው? ስብዓዊነት?ኢትዮጵያዊነት? ወይስ Business oriented interest ? ነው እያናገረህ ያለው? እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

ጎሰኝነት ሰው ሰራሽ[የሀሳብ] ነው። ነገድ/ጎሰ ተፈጥሮአዊ ነው። ነገድን/ጎሳን ማጥፋት አይቻልም ነገር ግን ግዜ አመጣሹን የጎሰኝነት ሃሳብ መስማማቱ እስካለ ማጥፋት ይቻላል። በምን-በመግባባት፣በፍቅር፣በእኩልነት እና በመማማር።የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ሎጂካል ነው። ምክንያታዊም ነው። የአንተ በፕ/ሩ መናደድ ስሜታዊና ግላዊ ነው። አሳማኝ ነጥብ አልሰጠህም።

የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ እና የአንተ ኢትዮጵያ ሰማይና ምድር ይለያያሉ። የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ምድር ፣በኢትዮጵያ ግዛት ያለች ወደ ፊትም የምትኖር ሀገር ስትሆን የአንተዋ ኢትዮጵያ ግን በአንተ አእምሮ ውስጥ እንካን በቅጡ ጎልታ የታየችህ አትመስልም ከአገላለጽህ።

የቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” አልበም 14 ዘፈኖች ያለው ድንቅ የጥበብ ስራ ነው።ኦሮምኛን፣ትግሪኛን እና ሲዳምኛን ከዋናው አማርኛው ጋር አካቶ የሰራበት አልበሙ-ነገድን ነጥሎ አንዱን አኮስሶ እና አንዱን አራክሶ የዘፈነበት ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን አንግሶ ያቀነቀነበት ስራው ለአንተ የስጋት ምንጭ ሆነና አረፈው እንደ አንተ አገላለጽ ።

ቴዲ አፍሮ አልክ “በባለፈው ጥቈር ሰው አልበሙ ምንሊክን፣አሁን ደግሞ ቴውድሮስን አግንናል ” አልክ። በዚህ በአሁኑ አልበም 14 ዘፈን ውስጥ ለአጼ ቴውድሮስ አንድ ዘፈን እና በባለፈው የጥቁር አልበሙ ደግሞ አንዲት ዘፈን ስለ እምዪ ምንሊክ መዝፈኑ በአንተ ቤት ቴዲ አፍሮ እነዚህን ንጉሶች አግንናል አሰኘህ። አጋናኙ እራስህ እንደሆነክ አይታወቅህምን?

ቴዲ-አፍሮ ከመጀመሪያው አቡጊዳ 1993 አልበሙ የአሁኑ ኢትዮጵያ 5ኛ አልበሙ ነው። ከ40-50 የሚገመቱ ነጠላ ዜማዎችን ለቃል፡፣ በአጠቃላይ ከመቶ በላይ ዘፈኖችን በዚህ አስር ዓመት ውስጥ ለቆልናል።

ሰለ ቀ.ሃ.ስ ሁለት ግዜ፣ስለ አጼ ምንሊክ አንድ ግዜ ስለ አጼ ቴውድሮስ አንድ ግዜ ዘፈኖችን ዘፍናል። በአጠቃላይ ከመቶ በላይ ዘፈኖች ውስጥ 4 ያህሉን ለሶስት የኢትዮጵያ ነገስታት ስራ መግለጫነት አውሎዋል። እንግዲህ አግንናል የምትለው ይህንን ነው።
እሺ የዘፈኖቹን በተለይም የጥቁር ሰው እና የጎንደር ጎንደር እያንዳንዳን ስንኝ ዘርዝሬ ባስቀምጥልህ ሁለቱ ነገስታት ብቻ ተቆጣጥረውት የነገሱበት ስራ እንዳልሆነ በእርጋታ ግጥሞቹን አንብብና ተረዳቸው።

***ማጠቃለያዪ

በ1992 እና በ1993 ዓ.ም በአ.አ ዪንቨርስቲ ቆይታህ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ስለ መብትና ሰብዓዊነት ተከታታይ ትምህርታቸው አንተን ጨምሮ ብዙዎቻችሁን ኢንስፓየር እንዳደረጉ እናውቃለን። አብረን ስንጨዋወትም ይህንን በእስሊው 10ኛ መንገድ በባዝራ ሆቴል ነገረህኛል። መምህርህ ነው ማለት ነው። በቶሮንቶው ስብሰባ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አጥጋቢ መልስ አልስጠኝም በሚለው ንዴትህ በየመድረኩ ፕ/ሩን ማብጠልጠልህ የበላበትን ወጪት ሰባሪ ያደርግሃል።ግን -ግን -በፕ/ሩ ላይ ማግኘት የሚገባኝን ባለማግኘቴ የአመለካከት ለውጥ አምጥቻለሁ ካልክ ለምነው በአቶ ልደቱ አያሌው ላይስ የአመለካከት ለውጥ ያልፈጠርከው።
ግን ያሻህን የመውደድና የመጥላት መብትህን ባከከብርም የህዝብ መሪዎች ላይ የምታራምደው ግላዊ አቃምህ ግን ከግልህ አውጥተህ ወደ መድረክ ካመጣህው በጉዳዩ ላይ ሂስም ሆነ ትችት ወይም ድጋፍም ከመስጠት አልመለስም።

እስቲ የቴዲ-አፍሮ ኢትዮጵያ የጥንታ፣ጨቃኛ ብለሃል-የአንተ የተራማጁ ኢትዮጵያስ ምን ትመስላለች?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.