የማነ ማንኪ በመጥረብያና በስለት መዶሻ የመደብደቡ ዝርዝር ተከታታይ ዜና

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ Ethio Semay)

የኢሳያስ ልዩ አማካሪ የማነ ገብረአብ፤ ቅጽል ስሙ “ማንኪ”(monkey)

ባለፈው ሰሞን ዜናውን እንዳነበባችሁት የኤርትራው ኢሳያስ አፈውርቂ በሆነ ምከንያት ከሥልጣን ቢታጣ ዙፋኑን ይተካል ተብሎ የሚነገርለት የፖለቲካ ጉዳይ ሐላፊና የኢሳያስ ልዩ አማካሪ የማነ ገብረአብ፤ ቅጽል ስሙ “ማንኪ”/ monkey/ ጣሊያን አገር ሮማ ከተማ ውሰጥ ድብደባ እንደደረሰበት ዜናውን አንብባችሁ ይሆናል።

ስለ ድብደባው ዝርዝር ዘገባ ሰፋ አድርጌ አቀርብላችኋለሁ።

ማንኪ የተደበደበበት ቦታ ሮማ ውስጥ ረቡዕ ከምሽቱ 11፡00  ሰዓት አካባቢ ጣሊያን አገር ሮማ ከተማ ውስጥ ‘ቪያ ሞንተብሎ’ በሚገኝ፡ ‘ረስቶራንት ማሳዋ’ በሚባል የሻዕቢያ ምግብ ቤት ውስጥ በጣሊያን አገር የሻዕቢያ አምባሳደር ከሆነው ‘ፍስሃጼን’ ከተባለው ጋር እራት በልተው ሲወጡ፡ አድፍጠው ሲጠብቋቸው በነበሩ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች በመጥረቢያና ስለት ባለው ሞዶሻ ነበር ክፉኛ የተጨፈጨፉት።

ጭፍቸፋው ሲከናወን ምግብ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ብዙዎቹ የሻዕቢያ ደጋፊዎች  እግሬ አውጪኝ’ በማለት ፈርጥጠው ከጥቃቱ አፈግገዋል። ሁኔታው ለፖሊስ እንደደረሰ፤ እስካሁን አንድ ተጠርጣሪ ተይዟል። ሁኔታው ከተሰማ በኋላ በሮማ አደባባዮች/ፒያሳዎች/ ኤርትራኖች ጭፈራ እያካሄዱ ናቸው። ተቃዋሚዎችን የሚደግፉ ጣሊያኖችም ከጎናችሁ ቆመናል እያሉ እያበረታትዋቸው ይገኛሉ።  በዓለም ውስጥ የተበተኑ ኤርትራዊያን የገንዘብ እርዳታ በማዋጣት ጠበቆች ለማቆም ዝግጁ እንደሆኑ ቃል ገብተዋል።

ጥቃቱ እንዴት ነበር?

አምባሳደሩ እጆቹ ላይ፤ የማነ ‘ማንኪ’ ደግሞ  በመጥረቢያ የተጨፈጨፈው አካሉ አገጩ ላይ፤ አንገቱ፤ እራስ ቅሉ ላይ ደጋግመው በመጨፍጨፍ ‘ዛሬ የኛ ተራ ነው፤ የናንተ ደም እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ የሕዝባችን ደም አይፈስም፤ ዛሬ አንተን እንገድላልን” እያሉ ሁለቱንም በእሪታ እስኪጮኹ ድረስ እየደጋገሙ ደብድበዋቸዋል ። የማነ ክፉኛ ስለተጨፈጨፈ ወዲያውኑ “መሬት ላይ ተዝለፍልፎ ወደቀ”። ደብዳቢዎቹ የማነን ተረባርበው እንደጐዱ፤ አምባሰደር ፍስሀጼን ወደ ተባለው ሲዞሩ፤ ሰዎች እመሃል ደርሰው ሲከላከሉለት እጁ ቢጎዳም፤ አጥቂዎቹ በየማነ እንጂ በፍስሀጼን ላይ ብዙም አትኩሮት ስላላደረጉ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል።

አጥቂዎቹ ድብደባው ከፈጸሙ በኋላ ‘ፕያሳ ኢንደፐንደንሳ’ ወደተባለ አቅጣጫ በመሸሽ አምልጠዋል። ምግብ ቤቱ ውስጥ የነበሩ የሥርዓቱ ደጋፊዎች፤ ኡኡታ ሲሰሙ፡ በመጥረቢያና ስለት ባለው መዶሻ እየተጨፈጨፉ መሆኑን ካስተዋሉ በኋላ፤መሪዎቻቸውን ከመከላከል ይልቅ ግድግዳ፤ግድግዳውን/ ጥግ-ጥጉን በመያዝ  “ኦፊቾ ፊናንሳ” ወደ ተባለው የኋልዮሽ አቅጧጫ አፈግፍገው አፈትልከዋል።

የሮማ ፖሊስ ሁኔታውን በመከታታል፤ እስካሁን ድረስ አንድ ተጠርጣሪ ይዘዋል። ’የማነ ማንኪ’  ኦስፒዳለ ሮማ በሚባል ሆስፒታል እርዳታ ሲደረግለት ቆይቶ፤ ጉዳቱ ብርቱ በመሆኑ ‘’ሚላኖ’ ወደ እሚገኝ ከፍትኛ ሆስፒታል ተወስዷል። በሌላ በኩል ኢሳያስ የማንኪን ሁኔታ በዝርዝር ለማወቅ ዶ/ር ሃይለ ምሕፁን የተባለ ሓኪም ወደ ጣሊያን ልኮታል። ማንኪ ከመደብደቡ በፊት ዕሁድ ዕለት ሮማ ውስጥ ለደጋፊዎቹ ስብሰባ ማድረጉ ሲታወቅ፤ ለተመሳሳይ ስብሰባ ላለፈው ቅዳሜ ጊሰን በተባለ የጀርመን ከተማ ለማድረግ ዕቅድ ነበረው፤ በመሃሉ ግን ይህ ድብደባ ስለደረሰበት አልተካሄደም።

በሌላ በኩል ‘ማዶት’ በመሳሰሉ የሻዕቢያ ድረገፆች ጥቃቱ የደረሰው ወያኔ በከፈላቸው ቅጥረኞች የተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ያትታሉ። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ግን *መሸፈኛ ያጣ ‘ሐፍረት’ * በማለት አጣጥለውታል። ይህ በእንዲህ አንዳለ ፤ በማንኪ ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ ሲሰማ፤ ሊብያን አቋርጠው የመጡ ኤርትራዊያን ስደተኞች ፤እንዲሁም በየአብቶብስ ማረፊያዎች፤ በየማጎርያዎች (ካዛ ኦኩፓታ) ተጥለው ተስፋ ርቆአቸው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ፡ ከደስታቸው ብዛት የአካባቢውን ተመልካች የሳበ ጭፈራ እያደረጉ ይገኛሉ።  ‘ወድ ትኹል’ የተባለ እውቅ የኢሳያስ አፈወርቂ ደጋፊ (አሁንም ኢሳያስን በማገልግል አስመራ ውስጥ ይኖራል) ዘፈን እየዘፈኑ

“ወደ እኛ ያቀዱት ወደ እነሱ ዞረ፤
የኢሳያስ ወገብ ድንገት ተሰበረ  ,,,,,”

በማለት በሮማ ጎዳናዎች እየጨፈሩ ደስታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ሮማ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የግል እና የማሕበራዊ ድርጅቶች በየማነ ማንኪና በፍስሀጼን የደረሰው ጥቃት፤ ኤርትራ ውስጥ እየፈሰሰ ያለው የንጹሐን ደም ለማስቆም የተወሰደ የቁጭት ነጸብራቅ ነው። ይላሉ። በጥቃቱ ተሳትፈዋል የሚባሉ ተጠርጣሪዎች ከተያዙ በገንዘብና በሞራል በመደገፍ የሕግ ጠበቃ በማስቆም እንከላከልላቸዋልን፡ ሲሉ ቃል ገብተዋል።ከዚህ በታች ያሉ ፎቶግራፎች፤ አጥቂዎቹ በጥቃቱ ላይ የተጠቀሙባቸው መሰሪያዎች አይነት እና ድብደባው የተፈጸመበት ሬስታውራንት እና ቦታ ይምልከቱ። በእኔ እይታ “ሮማ የዘርአይ ደረስ ትውስታ ትዝ ያላት ትመስላለች”።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ Ethio Semay)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.