የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ዕዝ የህወሃት ባለስልጣናትን ለስብሰባ ጭኖ ይጓዝ በነበረ ፒካፕ መኪና ላይ ጥቃት ፈጸምሁ አለ

ሃምሌ 9/2009 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ በጎንደር ጭልጋ ልዩ ስሙ ግንት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም ባለስልጣናቱን አጅበው የነበሩት ታጣቆዎች አንዱ ወዲያውኑ ሲሞት ሁለቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ተልከዋል።ሌሎች ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ አጃቢዎ በጭልጋ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። ባለስልጣናቱን ጭኖ የነበረው መኪና ገደል ገብቷል።በተአምር ከሞት የተረፉት ባለስልጣናት የአማራ ክልልን የአስተዳደር ጸጥታን በመወከል አቶ ሐብታሙ፥የሰሜን ጎንደርን የአስተዳደርና ጸጥታን በመወከል አቶ ጎሽ፥እንዲሁም የልዩ ልዩ የጸጥታ አካባቢዎችን በመወከል አቶ መሃሪ ሙጨ የተባሉት ይገኙበታል።
እነኝህ ባለስልጣናት የሞተውን አስከሬንም ሆነ ቁስለኞችን ሳያነሱ ነጋዴ ባህር ወደ ሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ እግሬ አውጭኝ ብለው ፈርጥጠዋል።በኋላም በከፍተኛ እጀባ ይሄዱበት ወደነበረው ስብሰባ ቢወሰዱም ስብሰባው ያለውጤት ተበትኗል።ከሞት የተረፉት ባለስልጣናት በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጠው እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.