በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔና  እድምታው- ታምራት ይገዙ 

ክፍል ሁለት

በመጀመሪያ ለኦሮሞ  ዲሞክራት ፍሮንት  አመራሮች በተለይ ለዶ/ር በያን ኣሶባ ያለኝን ከፍተኛ አክብሮት ልግላጽ እወዳለሁ:: በማስከተልም የኦሮሞ ዶሞክራት ፍሮንት አመራሮች ከሰላሳ ዓመት በላይ የኦሮሞ ነጻ አውጭ በሚል መጠሪያ ሲታገሉ ከቆዩ ቦሃላ ዘመኑን ዋጅተው እና እንደ አባቶቻቸው ኦሮሞ የኢትዮጵያ ግንድ ነው::  ግንድ ደሞ አይገነጠልም በማለት ሰላሳ ዓመት እንደ እምነት ይዘውት የኖሩትን ከኢትዮጵያ ተገንጥለው የመውጣት ሰንካላ ዓመለካከት በመተው እኛ ኢትዮጵያዊ ነን በማለት ቆርጠው ሲናገሩ መስማት በነሱም  ሆነ በድርጅታቸው ላይ የሚያደርሰው ተጽኖ ቀላል እንዳልሆን መገንዘብ አያዳግትም::  ለምን ቢሉ የዝሁ ጽሁፍ ከታቢ በጣሊያን ሃገር በስደት በነበረበት ዘመን ከተለያዩ ቤሔረሰብ ከመጡ ኢትዮጵይያውያን ጋር በተለያዮ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ አብሮ ኖሮል በተለይ ተወልዶ ያደገው በወለጋ ክፍለ ሀገር ውስጥ ከነበረ ወጣት ጋር እንደ እኩያ ወንድማማቾች በመተያየት ጥሩውንም መጥፎውንም ግዜ አብረው አሳልፈዋል::  ይህ የኦሮሞ ዘር ተወላጅ የሆነው  ልጅ ከሚታወቅበት ልዩ ጸባዩ በምንም መልኩ የማይከፋውና ሁልግዜ ደስተኛ ሆኖ መታየቱ ነው:: እንደ እውነቱ ከሆነ  ክፉውንም ደጉንም ስቀው የሚያሳልፉ ሰዎች ማግኘትና ከነሱ ጋር በጎደኝነት መዝለቅ የሚሰጠው ደስታ ቀላል አይደለም::  ታዲያ  እንዲህ አብረን እያሳለፍን ባለበት ግዜ አንድ ቀን ሮም ከተማ አፍሪካ ምግብ ቤት በሚባለው ምግብ ቤት ውስጥ እያለን ሌላ የኦሮሞ ዘር ተወላጅ የሆነ ወንድም መጣና ተቀላቀለን ከዛ ቦሃላ ሁለቱ ወንድሞቼ ወሪያቸው ሁሉ ኦሮምኛ ሲሆንብኝ ግራ በመጋባት አማርኛ አውሩ እንጂ ጦጣ አደረጋችሁኝ ስላቸው ከንግግሩ በፊት ሳቅ የሚቀድመው ወዳጄ አፉን በእጁ ሸፍኖ እየሳቀ የሚለኝ ታውቃለህ ብሎ ጠየቀኝ?  እኔም ኦሮምኛ አላውቅ ምን አይነት ጥያቄ ነው አልኩት::  እሱም ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ይኽውልህ ከአንተ ጋር አማርኛ ስላወራሁ ዼሺ ሚላ (አስር ሺ ሊሬ) ክፈል ነው የሚለኝ ብሎ አረፈው::  ይህንን ሳስታውሰ ነው ከሃያ አመት በፊት ከኢትዮጵያ የመግንጠል አላማ አንግቦ የነበረ ድርጅት እና በዛ ዘመን አማርኛ የሚናገሩ የኦሮሞ ተወላጆችን $10 የአሜሪካ ዶላር ይቀጣ የነበረ ድርጅትና የደርጅት መሪዎች በአሁኑ ሰዓት እኛ የኢትዮጵያ ግንድ ነን ግንድ ደሞ አይገነጠልም እያላችሁ በአማርኛ ስትናገሩ ከላይ እንደ ገለጽኩት በናንተም ሆነ በድርጅታችሁ ላይ ያለው ፈታኝ ነገር ቀላል እንዳልሆነ ስለተረዳሁት ነው ከመጀመሪያው  አድናቆቴን ለመግለጽ የወደድኩት::  ወደ ፊት ደሞ አንድ እርምጃ ተራምዳችሁ የድርጅታችሁ ስም ይበልጥ ሃገራዊ ስሆን እንደኔ ዓይነቱን ከሶስት እና  ከአራት ቤሄረሰብ የምንወለድ እና በቤሔር ሆነ በጎሳ መደራጀት የማንፈልገውን  ኢትዮጵያኖች ያለ ምንም ችግር የድርጅታችሁ አባላቶች እንደምንሆን ምንም ጥርጥር የለኝም:: ይህን ካልኩ ቦሃላ

ወደ ስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔ  ሳቀና  ዶ/ር ቢያና በሲያትል በተደረገው ስብሰባ ላይ ሲናገሩ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ለአኦሮሞው; ለአማራው; ለደቡቡ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ከዛም አልፎ ለአፍሪካ ክዛም ከፍ ሲል ለዓለም ሲሉ እድምጫ ስለ ነበር  እውንውት ይህንን አባባል ደጋግመው ሲናገሩ ሒሊነቸው ያመነበትን ልባቸው የተቀበለውን ነው አንደበታቸው የሚናገረው የሚል ጥያቄ እራሴን እንዲጠይቅ ገፋፍቶኛል ምክንያቱም ከአገር ውጪ ከሃያ በላይ የሚቆጠሩ የአገራቸው የኢትዮጵያ ንበራዊ የፖለቲካ አስተላለፍ ይመለከተናል የሚሉ ባሉበት ዘመን የሳቸው ድርጅት የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት እና ሌሎች በቁጥር ሶስት የሆኑ ድርጅቶች ብቻ የሃገራችንን የተመሰቃቀል ፖለቲካ እንፈታለን ሲሉ ማዳመጥ አገራችን ያለችበትን ሁኔታ በቅጡ አልተገነዘቡም የሚያስብል ነው::  ምክንያቱም   የደርግ ዘመን ችግር ትተን ቢያንስ የህወሓት መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ያለውን  ያደረሰውን ሐገራዊ; ፖለቲካዊ እና ኢኮኖማዊ ቀውስ  በጥሞና ብንመለከተው  የአገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ  ድርጅቶች በሙሉ ተሰባስበው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ውስጥ ገብተው እጅ እና ጎንት ሆነው ቢሰሩ እንኮን ሕወሐት ላለፈው ሃያ አምስት አመት ያደረሰው ጥፋት በቀላሉ የሚቀለበስ አይደላም::

በሌላ በኩል  የህውሐት መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ያለውን  የአገራችንን መሀበራዊ ኢኮነማዊ እነ ፖለቲካዊ ችግሮች ላስታወላ ሙህር እና የደርጅት መሪ  የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ ውስጥ ያሉት ድርጅቶች ብቻ የኢትዮጵያን ችግር ፈቼዎች ሆነው ሲያቀርቡ አንድም የአገራችንን ችግር በጥልቀት አልተረዱትም አሊያም ህወሀት በፓሪሱ ጉባኤ ላይ የሰራውን ደባ ለመኮረጅ በዝግጅት ላይ ናቸው ማለት ነው::  ህወሀት በደርግ መውደቂያ ሰሞን በተጠራው የፓሪሱ ጉቤኤ ላይ ያደረገውን ደባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለሚያውቀው እዚህ ላይ መግለጹ ፋይዳ የለውም::  እዚህ ጋ ሳልጠቅስ የማላልፈው  ነገር ቢኖር  በሲያትሉ ኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ ጉባኤ ላይ ንግግር ካደረጉት ውስጥ   የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ  እንዲቆቆም  ተገተው ከሰሩት ውስጥ ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው እና ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊ ይገኙበታል እነርሱም  በሲያትሉ ጉባኤ ንግግራቸው “እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው” የሚመስል ውስጠ ወይራ የተላበሰ አባባል ጣል አድርገው አልፈዋል: ይህንን በተመለከት የምለው ይኖረኛል::

አሁን ወደተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ ዶ/ር በያን ልጠይቅ የምፈልገው: የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ መስራቾች (ጠንሳሾች) የደርጅታችሁን መሪዎችና እርሶን ጋብዘው ስለ ንቅናቄው አስፈላጊነትና ንቅናቄውን ስለምትመሰርቱን አራት ድርጅቶች ማብራሪያ ሲያቀርብላችሁ: በእናንተ በኩል ለኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ አስተባባሪዎች ጥያቄዎች አለቀረባችሁም? ለምሳሌ  የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ የሚለው መጠሪያ ስም ትልቅ ተልኮ እንዳለው እና ለዚህ ትልቅ ተልኮ ደሞ በዊጪ አገር ያሉ  የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ተቀዋሚ ድርጅቶችን በወጉ ያላካተተ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ ከመነሻው ችግሮች ይታይበታል ብላችሁ በደፍረት አልጠየቃችሁም: ከተየቃችሁ ምን መልስ አገኛችሁ ካልጠየቃችሁ ለምን? ይህንን ልጠይቆት ያነሳሳኝ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ ከመመስረቱ ቀደም ብሎ እርሶ ዶ/ር በያን ከሌሎች የድርጅቶች አመራሮች ጋር በአዲስ ዽምጽ ራዲዮ ቀርባችሁ አብራችሁ ለመስራት ሃሳብ እንዳላችሁ ሲነገር አድምጫለሁና ነው::  በሌላ በኩል የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ድርጅት እና   የርሶን የፖለቲካ ተመክሮ ተጠቅመው በአገር ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉትን ተቃዋሚዎች በሚያግባባቸው ጉዳይ ላይ ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ በኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ አይችልም ነበር ወይ?  በእኔ እምነት የድርጅቶትን እና   የርሶን የፖለቲካ ተመክሮ በወጉ የተጠቀሙበት አይመስለኝም አሊያም የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ እንዲመሰረት ትልቅ አስተዋጾ ያደረጉት ወንድሞቾት በአንድም በሌላ ጉዳይ ይህ እውን እንዲሆን አልፈለጉትም ማለት ነው::  ይህ ይመስለኛል በእኔም ሆነ በአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያኖች ውስጥ  የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅንቅቄ የተጠነሰሰው  የአገራችንን የኢትዮጵያን ችገር አጥንቶ መፍትሄ ለመስጠት ሳይሆን ግንቦት ሰባትን አውራ ፓሪቲ አድርጎ የመውጣት ዘመኑን ያልዋጀ እንቅስቃሴ ተደርጎ የሚቆጠረው::  በተጨማሪ በኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ላይ ያለኝ ቅሬታ ትንሽም ቢሆን ሳልጠቅስ ማለፍ አልሻም : ይህውም   ኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ሲመሰረት ደስታ ከተሰማቸው ኢትዮጵያኖች ውስጥ አንዱ ነኝ: የተደሰትኩበትም ዋናው ምክንያት:

1 ኛ ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን የሚለውን አመለከታችሁን ሙሉ በሙሉ በመተው “እኛ ኦሮሞዎች የኢትዮጵያ ግንድ ነን ግንድ እንደ ማይገነጠለው ሁሉ እኛም አንገናጠልም በማለታችሁ::”

2ኛ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለረጅም ዘመን የኖረውን እኛ እና እነሱ የሚለውን የዚያ ትውልድ የፖለቲካ አካሄድ እና ያለመደማመጥ ችግር  በተወሰነ ደረጃም ቢሆን  የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ይቀርፈዋል የሚል ምኞት ስለነበረኝ ::

3ኛ የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት በዊጪ ካሉት እና ተመሳሳይ አገራዊ አጀንዳ ያላቸውን ተቃዋሚ ድርጅቶች ላለፉት አርባ አመታት እኛ እና እነሱ የሚሉትን ፖለቲካ ትተው አብረው በመሆን የህወሐትን መንግስት ለማስገደድ ሁኔታዎችን ያመቻቻል የሚል ሃሳብ በቡዙዎች ኢትዮጵያን ልብ ውስጥ የነበር ሲሆን የሆነው ግን ከዛ በተለየ መልኩ ግንቦት ሰባትን አውራ ድርጅት አድርጎ ለማውጣት ደፋ ቀና ስትሉ ከማየት የበለጠ የሚያሳዝን ነገር የለም::

ማን ያው ቃል ግዜው ያልረፈደ በመሆኑ ቡዙ ሰው የተመኘላችሁን ምኞት ማለትም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ያለምንም አግላይነት የሚሰባሰቡበትን መድረክ ፈጥራችሁ እውነተኛ ስሙን የሚወክል አገራዊ ንቅናቄ እንደምትፈጥሩ ትልቅ ተስፋ አለኝ::  በሌላ በኩል  በኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ፈጣን አካሄድ በአጭር ግዜ ውስጥ ግንቦት ሰባት; የሲዳማ ህዝብ; የአፋር ህዝብ እና  የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ውህደት ፈጽማችሁ አገራዊ ንቅናቄውን አንደ አንድ ድርጅት ሆናችሁ  እንደምትቀርቡ ሌላው ተስፋዪ ነው::  እርግጥ እዚህ ላይ አበክሬ ሳልናገር የማላልፈው ነገር የናንተ የአራት ድርጅቶች ውህደት የሚፈጸመው የግንቦት ሰባት በጎ ፍቃደኝነት ሲታከልበት ብቻ ነው:  ምክንያቱም ኢህአዴግ የአራት ድርጅቶች ስብስብ ሆኖ ለሃያ አምስት አመት የቆየው ህወሀት መወሃድን አጥብቆ በመጥላቱ እና አውራ ሆኖ መቆየት በመፈለጉ ነው::

ሌላው ደሞ ዶ/ር በያን ሲናገሩ እውቁ ደራሲ አቶ ሃዲስ አለማየሁ በ1953 ዓ/ም የወቅቱን ችግር ተገንዝበው ለአጼ ሀይለስላሴ ደብዳቤ የጻፉ ሲሆን: የደብዳቤውም ፍሬ ነገር ንጉሱ ማሻሻይ እንዲያደርጉ የሚወተውት ነበር ::  እኔም የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ውስጥ ባላችሁ ድርጅቶች ብቻ የአገራችን ችግር ስለማይፈታ ሳትውሉ ሳታድሩ የአገራችን ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉትን ድርጅቶች እና ግለሰቦች የሚያጠቃልል አገራዊ እና አንድነታዊ ስብሰባ እንድትጠሩ እጠይቃለው::  እርግጥ ነው ይህን ማድረግ የነበረባቸው ሀሳቡን ያፈለቁትና የጠነሰሱት ነበሩ እንደ እኔ እምነት እነዚህ ሙሁራን ወንድሞቻችን ጥንሡን ሲጠነስሱ ካልተሳሳትኩ  በሂሊናቸው የነበረው በተበታተነ መንግድ የሚካሄደውን ትግል ወደ አንድ የማምጣት ሳይሆን ግንቦት ሰባትን አውራ ድርጅት አድርጎ የማውጣት ፍላጎት ውስጥ ነበሩ:  ይህንን ያልኩበት ምክንያት በቭዥን ኢትዮጵያ ስም የተካሄዱትን በሙሉ ስብሰባዎች በጽሞና ስከታተል የታዘብኩት ነገር ቢኖር አንድን ድርጅት አውራ አድርጎ የማውጣት አካሄድ እንጂ የአብሮ መስራትን የሚያበረታታ አልነበረምና ነው::

አንጋፋው ኢትዮጵያዊ ሙህር ፕ/ር መስፍን ወ/ማ በሲያትሉ ንግግራቸው ይህን ሲሉ ተደምጠዋል ” በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጪ አገሮች ብልጭ ድርግም እያለ የሚታየው የኢትዮጵያ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን አላማ በሁለት የተለያዩ ሃይሎች ስር ያለ ነው በአሁኑ ግዜ ሳይታለም የተፋ ነው በአገር ውስጥ ያለውን ወያኔ ይቆጣጠረዋል::  ከአገር ውጪ የሚታዩትን ብልጭ ድርግሞች የምዘውሩት በፍቅረ ነዋይ እና በፍቅረ ስልጣን ነው ብዪ እኔ አምናለው እነርሱ ካልገቡበት የሌላው እንዳይሰምር እያሉ የሚፎክሩ ድርጅቶች ዛሬ አሉ በዛ ላይ በፈረንጅ አገር የኑሮ ጣጣ ጠገብን አያውቅም ስለዚህ በአገር ውስጥ ወያኔ ስልጣኑን ሃፍቱን ለመቆጣጠር እንድ ሚሞክረው በዊጪም አገር ስልጣኑን እና ሃፍቱን ለመቆጣጥር በመሞከር በስደተኛው ላይ ተጽኖ ይደረጋል ስለዚህ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ንቅናቄዎች ብልጭ ድርግም የሚሉት ለዚህ ይመስለኛል;;”  ይህንን የፕ/ር መስፍንን ትንታኔ ስዳምጥ ፕ/ር ስም ጠርተው አይናገሩ እንጂ ከኔም ጋር ሆነ ከቡዙዎችችን ሀሳብ ጋር የሚስማማ የአውራ ድርጅት የማውጣት መፍጨርጨር ጋር የሚመሳሰል ሆኖ አግኝቸዋለሁ ስለሆነም እንዲህ አይነቱ አካሄድ በጥሞና አይቶ እና ተገንዝቦ መነጋገር የሁላችንም ሃላፊነት ነው ምክንያቱም አባቶች “ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በእርጥቡ” ይላሉና::

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.