የአሜሪካ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሚደረገው የሰባዊ መብት ጥሰትን በመኮነን የወያኔ ህወሃት መሩን መንግስት ተጠያቂ የሚልበት የህግ ረቂቅ  ነገ ሃሙስ ቀን ለውይይት ሊቀርብ ነው

ቀን ጁላይ 27, 2017

ሰዓት 10:00 AM

አድራሻ ፡  2172 ካፒቶል ሂል ሬይበርን ህንጻ [ 2172 Rayburn Building]

ውይይቱ ቀደም ብሎ ተረቆ ቀርቦ የነበረው  H. Res. 128 ላይ ይነሳና ይህኑ ህገ ረቂቅ ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ የሚያደርጉት የኒው ጄርሲው ተወካይ ኮንግረማን ሚስተር ክሪስ ስሚዝ ማሻሻያ ወይም ምትክ የሚሆን ረቂቅ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ አገራችን ኢትዮጵያ ሰባዊ መብት በደል፤ያለፍርድ እስራት፤ሰቆቃና ግድያው መስማት ተመረናል የምንል ሁሉ ለመሳተፍ በቦታው እንገኝ።

ይህን ህገ በማርቀቅ እኛ የህዝብ በደል ልናሰማ የምንጥረውን ሁሉ የሚረዱንን ልናመሰግን ልንተባበር አገር መውደዳችን፤መልካም ስነምግባራችን የግድ ይለናል። በአንጻሩ የግፈኛው ህወሃት መር መንግስት ተወካዮች እንዲህ ያለው መጋለጥ እንዳይደርስባችው እጅጉን ይጥራሉ። እኛም በጎራችን ዲፕሎማሲያዊ ድል ለተበዳዩ ወገናችን ልናስገኝ ተነስተናል። ነገ ካፒቶል ሂል እንድንገናኝ ይሁን።

ኢትዮጵያ ስትበደል በውጭ አገራት ተንከራተው የተሟግቱላት ታሪክም ይህን ግዴታ እንዳዲስ አድርጎ ከኛ ላይ ጥሎታልና በቦታው ተገኝተን ድምጻችንን እናሰማ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.