የፋሽስት ወያኔ ስም ከሒዝቦላ ጋር መነሳቱ ይበዛበታል! (አቻምየለህ ታምሩ)

በዛሬው እለት በተካሄደው የአሜሪካ የሕግ መመሪያ የውጭ ጉዳይ ኮምቴ ጉባኤ የወያኔዋ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ የአገዛዙ ባህሪ ተገምግሞ የፋሽስት ወያኔ ስም አሜሪካ በአሸባሪነት ከፈረጀችው ከሊባኖሱ የሺዓ ቡድን ከሒዝቦላ ጋር አብሮ ሲያነሳ ውሏል። እኔ ግን የፋሽስት ወያኔ ስም ከሒዝቦላ ጋር ብቻ መጠራቱ ይበዛበታል ባይ ነኝ። ፋሽስት ወያኔ የአይሲስን ጭካኔ ካወገዘው ከሒዝቦላይ ጋር መወዳደር የለበትም።

በኔ እምነት ፋሽስት ወያኔ ስሙን ቄስ ይጥራውና ስሙ አብሮ መጠራት ያለበት ከሂትለሩ የናዚ አገዛዝና ከአቡባክር አል ባግዳዲው የአይሲሱ ቡድን ጋር ነው። ወያኔንና ሒዝቦላህን ባንድ ረድፍ ወይም ባንድ መደብ ማስቀመጥ ወያኔን በጣም እንደ ማግዘፍ ይቆጠራል። የወያኔ ምድብ በሒዝቦላህም ሳይቀር የተወገዘው አይሲስ ነው።

አይሲስ ያደረገው ወያኔ ያላደረገው ምን ነገር አለና ነው ፋሽስት ወያኔ አይሲስን ካወገዘው ከሒዝቦላህ ጋር አብሮ ስሙ ሊጠራ የሚችለው? ወያኔ አንገት አልቀላም? የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር በግፍ አልረሸነም? ወላጅ እናትን በሞተ ልጇ አስከሬን እንድትቀመጥ አላደረገም? ወያኔ ቤት ዘግቶ ንጹሀንን በእሳት አላጋየም? የአማራን እናት እንግዴ ልጇን ከቀበረችበት አውጥቶ አገርሽ ውሰጅና ቅበሪው አላለም? ባዕዳን ድንጋይ ምሰው ሲቀብሩን ለምን ተናገራችሁ ብሎ አስፓልት ላይ አስተኝቶ ህፃናትና ሴቶችን በጭካኔ አልረሸነም? ግራዚያኒን ለምን ተቃወማችሁ ብሎ ደማችንን በአስፋልት ላይ አላፈሰሰውም? እስክንድር ነጋን በእምቦቆቅላ ልጁ ፊት ህፃኑ የደም እንባ እያለቀሰ በካቴና አላሰረውም? አይሲስ ከዚህ የከፋ ምን ሰራ? በእውኑ አይሲስ የሰራው ወያኔ ያልሰራው ጭካኔ ይኖራልን? እስቲ ንገሩኝ?!

ናዚዎች ከሁሉም በላይ በእስላምና በአይሁዶች ላይ የነበራቸው ጥላቻ ወደር አልነበረውም። በዚህም የተነሳ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ አይሁድና እስላም ጨፍጭፈዋል። የትግራይ ናዚዎችም እንደ አማራ የሚጠሉት ነገር እንደሌለ የራሳቸው ሰው አለም ሰገድ አባይ ያጠናውን ማንም ሊያነብ ይችላል። ስለሆነም ናዚዎች በእስላምና በአይሁድ ላይ የፈጸሙትን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ወያኔዎች በአማራ ላይ ፈጽሞታል። በሀያ አመት ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን በላይ አማራ አጥፍተዋል።

የትግራይ ናዚዎች ያላስለቀሱት፤ ሜዳ ላይ ለጅብ ያልበተኑት፤ በየ ኬላውና በየጥሻው የየብስና የባህር ሲሳይ ያላደረጉት ቤተሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራልን? እነዚህን ጨካኞች ይህንን ሁሉ ግፍ በኛ ላይ ፈጽመው ባደባባይ ሲውሉ ንጹህ ያስመሰላቸው ያሰለፉት ወታደርና በእጃቸው ያለው የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ በእውነተኛ ሕግ ፊት የትግራይ ናዚዎች አለም የህዝብ ጠላቶች እና የሰላማዊ ሕይወት ጠንቆች እያለ ከሚፈርጃቸው ከሒዝቦላና ከሰሜን ኮርያው አገዛዝ የባሱ አረመኔዎች ናቸው። ግን ምን ያደርጋል ተወልደን ያደግንባት አገራችንን ምድራዊ ሲኤል ያደረገ የትግሬዎች የአፓርታይድ አገዛዝ ዛሬ እንደምናየው ከአይሲስ ምድብ ሊቆጠር ያልቻለው አለም መስሚያዋ በገንዘብ ተደፍኖ ለእግዜርም የሚያደርስ አባት ስላጣን ብቻ ነው።

የሆነው ሆኖ ወያኔ ከሰሜን ኮርያና ከሒዝቦላ ጋር ስሙ የተነሳበት የሕግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.