ኮማንድ ፖስቱ አቡነ ጴጥሮስ እንዳይዘከሩ ከለከለ ። ክልሉ የፈቀደውን ፈቃድ አልቀበልም ፣ አያገባኝም አለ

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ሰንበት ተማሪዎች ከአዳራሹ እንዳይወጡ ተከልክለዋል ። በአሁኑ ወቅት በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እየዘነበ ነውም ተብሏል ። ከሩቅ ጭምር በዓሉን ለማክበር የመጣው ህዝብም ወደ ቤቱ እንዲመለስ የደብሩ ሰንበት ተማሪዎች እያግባቡ ነውም ተብሏል ።

ሰንበት ተማሪዎቹ በድርጊቱ ቢያዝኑም በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ ዝግጅታቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል ። ገሚሶቹም ወደየቤታቸው እየሄዱ ነው ተብሏል ።

ለጊዜው ኢትዮጵያዊውን ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን በአደባባይ ለማዘከር ፈቃድ አግኝቶ የነበረው መርሐ ግብር በኮማንድ ፖስቱ ታግዷል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.