ሙስና እና ህወሃት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው-ሰማያዊ ፓርቲ

በሙስና የበሰበሰ ስርዓትና ለችግሮቹ መፍትሄ በሙስና መሰብሰብ ብሎ በማመን የተመሰረተው የህወሃት መራሹ መንግስት የሙስናን ችግር የሚቀርፍበት ምንም ዓይነት ሞራልና ስብእና የለውም ሲል የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ ጉባኤ መግለጫ አወጣ።

የሰሞኑ የጸረ-ሙስና ዘመቻን ተመርኩዞ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ህወሃት ማለት ሙስና -ሙስናም ማለት ህወሃት ናቸው ብሎ ከጠቀሰ በሃላ ሙስና ከሌለ ህወሃት የለም ህወሃትም ከሌለ ሙስና የለም ሲል ፓርቲው የጸረ-ሙስናን ዘመቻ የህዝቡን እይታና ቀልብ መስረቂያ ሲል ተሳልቆበታል።

አቶ ጌታቸው አምባዪ የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ -መንግስት 42 ሰዎችን ያሰረው ከጥልቅ ተሃድሶ የተገኘ ውጤት እንደሆነ በማብራራት ገልጾ ነበር። ሆኖም አቶ ጌታቸው ሚ/ር ፣ ሚኒስትር ደ/ኤታና በሚንስትር ማእረግ ላይ ያለን ሰው ገና ለገና ለስልጣናችን ለሚቃወሙ ሰዎች ደስታ ብለን የምናደርገው አይደለም በማለት የታሳሪዎቹን ማንነት ከወዲሁ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደማይቀላቀሉ በአጽንኦት ገልጸዋል።
ሆኖም ባለፈው ሳምንት የዘመቻው ጅምር እውጃ ወቅት በዶ/ር ነገሪ ሌንጮ 34 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ባለሃብቶችና ደላሎች ታሰሩ በተባልንበት ወቅት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረ ነው የሚለውን የሚቃረን ተግባርና መግለጫ እየታየ እንዳለ ይታወቃል።

ህወሃት ማለት ኢኮኖሚያዊ የበላይነትን በዘረፋ ማምጣት አለብኝ ብሎ የተነሳና በዘረፋ የተደራጀ ሃይል ሆኖ ሳለ ዛሬ ግን ከየት ያመጣ ሆኖ ነው የሙስናው ማስተር ማይንድ ሙስናን እናጥፋ ሊል የቻለው ሲል ሰማያዊ ፖርቲ ይገልጻል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሃት ስርዓት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ከተፈጠረበት የስርቆት ፣ዘረፋና ሙስና ይከላከላል ብሎ ከመማን እና ብሎም ከመጠበቅ እርሰ በርሱ ተባብሮና አምርሮ በመታገል ስርዓቱን ከስሩ መንቅሎ ሲጥል ብቻ ነው ከመዘረፍና ከኢ-ሰብዓዊ አያያዝ ለመዳን የሚቻለው ሲል መግልጫው ያትታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በህወሃት ውስጥ በሙሰኝነታቸው እና በእድሜያቸው አንቱ የተባሉት አቶ ስብሃት ነጋ፣ዓባይ ጸሃዪ፣አዜብ መስፍን፣ሳሞራ የኑስና አርከበ እቁባይ ባደረጋቸው መጠን የለሽ የህዝብና የመንግስት ንብረት ዘረፋዎች መረጃዎችን የሚያሰባስቡ መርማሪዎችን ደብዛ በማጥፋት እራሳቸውን ሲከላከሉ እንዳለ ተጠቆመ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.