የፋሲል ደሞዝ ዘፈን እና አስቂኙ ክስ – ሰለሞን ይመኑ

የሃገራችን የፍትህ ስርዓት እንዴት በፖለቲካው(በአስፈፃሚው)እጅ ሙሉ በሙሉ እንደወደቀና የህግ የበላይነት ሳይሆን የፖለቲካው የበላይነት እንደሚያሸንፍ በዚህ ክስ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ በአማራና የኦሮሚያ ክልሎች የሚቀርቡ የሽብር የሃሰት የክስ ድርሰቶች በግልፅ ብናይም የአሁኑ የፍሲል ደሞዝን አዲሱን ሙዚቃ በስልካቸው ሲያዳምጡ ተገኙ የሚለው ክስ ግን በጣም የሚያስቅም እንዲሁም የህዝቡ የጭቆና አገዛዝ ምን ያህል ደረጃ እንደደረሰ መረዳት ይቻላል፡፡
  በጣም የሚገርመው ክስ የመሰረተችው/ው አቃቢ ህግ ነገር ይገርማል እስኪ እንዴው በዚህ ክስ ላይ የታየው የወንጀል ድርጊት ምንድን ነው? እንዴው ክስ ለመመስረት መሰረታዊ የሆነው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 23 መሰረት አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፤ ግዙፍዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው፡፡ ወንጀል ሁኖ የሚያስቀጣ ነገርም ህገ ወጥነቱ እና አስቀጭነቱ በህግ የተደነገገውን ድርጊት ፈፅሞ መገኘት ነው፡፡ በዚህ ክስ ላይ ግን እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች እንዳልተሟሉና የፍሲል ደሞዝ አዲሱ ዘፈን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወንጀል ባለመሆኑ ሰዎቹ የተከሰሱት ወንጀልነቱ በህግ ባልተደነገገ ህግ ነው ማለት ነው፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ ዘፈኑ በወንጀልነት የተደነገገ ቢሆንም እንኳን ዘፈኑን በስልክ ማዳመጥ ለሌላ ሶስተኛ ወገን እንዲያዳምጠው በማድረግ ለአመፅ እስካላስነሳ ድረስ ወንጀል አይሆንም፡፡ ዋናው ነገር ግን የሙያተኛው እንዲህ  ሙያውን እስኪረሳ ድረስ በፖለቲካ አይን መታወር የስራቱን መክሰርና እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን እንደዋነኛ የፖለቲካ መሳሪያ በማድረግ የትግራዩ ፍሽስት መንግስት እንዴት ህዝቡን አንድ በአንድ እየለቀመ ወደ ማጎሪያ ካምፕ እያስገባ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን በፍትህ ስራቱ ዙሪያ ያለን የክልሉ ሙያተኞችም ከፖለቲካ መሳሪያነቱ ወጥተን ሙያዊ ግዴታችን ካላሳየን በቀር አሁንም ቢሆን የህዝቡን የመከራና የስቃይ ዘመን በማራዘም በኩል እኛም ከፍሽስቱ የወያኔ መንግስት ጋር ተሳትፎ እያደረግን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በዚህ መንግስት ከሚደረገው አፈና ጎን ለህሊናው ሳይሆ ለጥቅምና ለሆዱ የሚያድር ሙያተኛ እስካለ ድረስ የስቃይና የመክራ ዘመን ይቀጥላል፡፡
 ወይ ደግሞ የምናዳምጠውን የሙዚቃ ዝርዝር ልማታዊው መንግስት በልማታዊ ሚዲያው በየቀኑ ይዘርዝርልን፡፡
# ፍትህ ለሁሉም#

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.