ህዝቡን በስናይፐር የገደለ ብቸኛው የአለማችን ገዳይ የትግራዩ ፍሽስት መንግስት እና ነሀሴ ፩ ሲታሰብ(ዋ-ባህር ዳር) – ሰለሞን ይመኑ

በአማራ የማንነት ጥያቄ ዙሪይ ወያኔን ፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ በመክተት በተከፈተበት የማንነትና የህልውና ጥያቄ ለህዝባቸው በመጠየቃቸው በአደባባይ በጥይት አሩር መስዋእት የሆኑ ጀግኖቻችን የምናስብበት ቀን ነው። በዚህ ቀንም የእኛ ጀግኖች ገለው የሞቱ በመሆናቸው የልባችን ኩራት፤የርስታችን ወራሽ፤በርስታችን ተራራ ከፍ አድርገን የምንተክላቸው፤በክብር ከፍ ከፍ የምናደርጋቸው፤ ህያው የሆነ የማይነጥፍ የህልውና እና ከህልም የመባነን የመለከት ድምፅ የለፈፉ፤የጨለማውን ዘመን የብርሃን ወጋገን ፈንጣቂ፤በወያኔ ላይ የደም እዳቸውን ያልከፈልንላቸው፤ ምድራችን ባድማ እንዳትሆን የወያኔ የምድር አራዊትም ብዝበዛቸው እንዲበቃው የማንቂያ ዲወል ደዋዮች፤ የህልውናን ድንቅ ጽላት በልባችን አትመውት ያለፉ፤ የአማራው ህዝብ ለአመታት የተሸከመውን የወያኔ የጭቆና ቀንበር ፈንቅለው በመውጣት የተስፋ ብርሃን የሆኑ፤ ለአመታት የነገሰውን የእኔ ምን አገባኝ የለዘብተኛ አቋም የሰበሩ፤ የማይጠፍ የማንነታችን ነበልባል እሳት በልባችን ውስጥ የለኮሱ፤ የጠላቶቻችን መንጋጋ በመምታት የወያኔ ቅጥረኛ ክፉ ሰሪዎችን ጥርስ ያረገፉ፤ የህዝባቸውን መከራና ሸክም እንዲሁም ጫና ከልባቸው በሚነደው የእኔነት ስሜት ጠላትን በቁጣቸው የቀሰፉ፤ ለማንነታቸው ሲሉ ሰይፍን የሳሉ ቀስትን የገተሩ ለሞት የማይሰስቱ ፤ጀግኖች የሚዘከሩበት የአማራ ተጋድሎ ሰማእታት ቀን ነሐሴ ፩። ሃውልት የሆነው ስራቸውን በብረት በትር ጠብቀን የምንይዝበት የእኛ ሙሴዋቻችን ቀን ነሐሴ ፩፡፡ አሁንም በሞት ጣር እና በስቃይ ድምጽ ሁነው በወያኔ ወታደራዊ ማሰቃያዎች ያሉ ጀግኖቻችን የበለጠ የምናስብበትና መፍትሔ የምንፈልግበትና የምንመካከርበት ቀን እንዲሁም የወገኖቻችን የሰባዊ አያያዝ ሁኔታ የምናውቀውን ሁሉ መረጃ በመያዝ ወደ መፍትሔ የምንጓዝበት ድል አብሳሪ ቀን ነሐሴ ፩።

በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)የእስር ትእዛዝ የተቆረጠላቸው የአፍሪካ አምባገነኖች 

** የሱዳኑ የፍትህና እኩልነት ንቅናቄ የጦር መሪ የሆነው ባህር አቡ ጋርዳ ከሌሎች ሃይሎች ጋ በመሆን በሱዳኑ የዳርፉር ጦርነት ወቅት በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ሳይቀር ጉዳት በማድረሱ

** የኬንያው ሙሃመድ አሊ በወቅቱ የኬንያ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረ እና ከኬንያው ፐሬዚዳንት ምዋዊ ኪባኪ አማካሪ ከነበረው ከ ፍራንሲስ ሙታራ ጋር በመመሳጠር የፐሬዝዳንቱ ተቀናቃኝ የሆነው Orange Democratic Movement ጥቃት ሲፈጽም ኮሚሽነሩ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን ባለማክሸፉ ብዙ ንጹሃን በመሞታቸው እና ብዙ ግድያዎች ፤ አስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀሙ

**የሱዳኑ ኦማር አልበሽር በዳርፉሩ ግጭት ወቅት ስልጣኑን ተጠቅሞ ወታደሩን፤ፖሊስን ፤የደህንነት ሃይሉን፤ እና ጃንጃ ሚኒሻዎችን በመያዝ ፉር፤ማሳሊትና ዛጋዋ ጎሳ ህዝቦችን አማጽያን ናቸው በማለት እንዲገደሉና እንዲደፈሩ ወሲባዊ ጥቃት እንዲደርስባቸውና ጅምላ ጭፍጨፋ እንዲደረግና ጎሳዎችንም የማጥፋት ስራ ሰርቷል፡፡

** የኮቲዲቫሩ ቻርለስ ብሌ ጎዴ በሰባዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን በወቅቱ የኮንግረስ ፓም አፍሪካ የተባለ የወጣቶችን ድርጅት የፐሬዝዳንት ሎረንት ባግቦ ደጋፊ የነበረ ድርጅት መሪ በነበረበት ወቅት አቢጃን አካባቢ በፐሬዝዳንቱ የምርጫ ተፎካካሪ በነበሩት በአላሳኔ ኦታራ(2010 ላይ)ንጹሃን ደጋፊዎች ላይ ከሎረንት ባግቦ ጋር ሁነው ባወጡት እቅድ መሰረት ብዙ ንጹሃን ተገለዋል፤ተደፍረዋል፤ተቀልተዋል እንዲሁም ኢ-ሰባዊ የሆነ አያያዝ በመያዛቸው ከሎረንት ባግቦ ጋር  እና ከልጁ ሲሞን ባግቦ ጋር ለፍርድ ቀርበዋል፡፡

** የሊቢያው ጋዳፊ፤ልጁ ሳፊ አል እስላም ጋዳፊ ሊቢያ ላይ በተከናወነው ረጅም ግጭት

** የኬንያው ሁሩ ኬንያታ በፐሬዝዳንት ምዋእ ኪባኪ የምርጭ ወቅት እሱን በመደገፍ በተቃዋሚ ተፎካካሪ ደጋፊዎች ላይ ባደረሱት የብዙ ንጹሃ ግድያ

**ከዚህም ሌላ የኮንጎው ጀርሜን ካታንጋ፤የሊቢያው ቶሃሚ ካሊድ፤የኡጋንዳው ጆሴፍ ኮኔ፤ እንዲሁም በጣም ብዙ ተዘርዝረው የማያልቁ የአፍሪካ አምባገነኖች በህዝባቸው ላይ መሳሪያ ያነሱት እና ህዝባቸውን የጨፈጨፉት ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ አንዴ ወጥተው በማይወርዱበት የአፍሪካ የእድሜ ልክ የስልጣን መንበር ላይ ሊያወርዳቸው የሚታገል ካፉ እስከ ገደፉ የጦር መሳሪያ የታጠቀ አማጺሃይል በመኖሩ ነው፡፡ ይህ ማለት አምባገነኖቹ ልክ ናቸው ማለቴ ሳይሆን እንቁ እና ብርቅ የሆነውን የአፍሪካ ስልጣን ለማስለቀቅ የሚችል ተፎካካሪ የትጥቅ አቅም ያለው አማጺ በመኖሩ ነው፡፡

ታዲያ ነብሰ በላውን የፍሽስቱን የወያኔ መንግስት በንጹሃን የባህርዳር ወጣቶች ላይ የተጠቀመው ስናይፐር የጦር መሳሪያ ከምንም በላይ ለፍትህና ዲሞክራሲ ሲሉ ባዶጃቸውን በወጡ ንፁሃን ዜጎች ላይ ሲሆን ይህም ግድያ በፓርላማ በሎሌው ሃይለማሪያም ግልፅ ትእዛዝ የተላለፈ የሞት አዋጅ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ወያኔ የፈጸመው ግድያ፤ድብደባ፤ከልክ ያለፈ በቀልና ሰባዊ መብት ረገጣ ባዶ እጁን ከወጣና መብቱን ከጠየቀ ህዝብ ጋ የተደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከላይ ከጠቀስኳቸው የአፍሪካ ጭራቆች በላይ በአማራው ላይ የወያኔ ፍሽስት መንግስት ብዙ ስቃይ ፈጽሟል፡፡ ይህም ምናልባት ለሰልፍ የወጣን ህዝብ በስናይፐር የገደለ የአለማችን ስር የሰደደ መንግስት ያደርገዋል፡፡

ዋ-ባሕር ዳር

*******

   ልጆችሽን እንዳትረሽ ከጉያሽ የጠፉትም በአማራ ጠሉ ቅልብ የትግራዩ አጋዚና በአንዳንድ የአማራ ጠል የትግራይ ተወላጅ ባንዳዎች ሲቸገሩ ቤት ለእንግዳ ብለሽ የሰጠሻቸውን መጠለያ ለታማኙ ደም ለሚጠጣው መንግስታቸው በሩን ከፍተው የልጆችሽን የሞት ድግስ ደገሱበት እንዲሁም ለሆዱ ባደረ ጥቂት የስልጣን ጥመኛ የራስሽ እስትንፋስ ጭምር ለልጆችሽ ሞት ተባበሩ፡፡ 

     ዛሬም ቢሆን ከጉያሽ ተደብቀው ጠረንሽን ሲማጉ የነበሩ ባንዳዎች ቀሪ ልጆችሽን ሊያስበሉ ተልኳቸውን ይዘው ተንኮልና ሼር ወደሚከወንበት የደም መሬት ተመልሰዋል ነገም በየዋህነት ትቀበያለሽ፡፡

ዋ- ባሕርዳር

      «እናጽዳው ስላችሁ ግዴለም ስትሉ

        አንበጣ አወደመው አገሩን በሙሉ

        ዳመናው ሲዳምን ይወረዛል ገደል

        ይዘገያል እንጅ መች ይረሳል በደል»

ይህ ስንኝ ከፌስቡክ ገጽ ወዳጀ የተዋስኩት ነው፡፡ ግን ገላጭ ስለሆነ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ መስዋእት የሆኑትን ወንድሞቻችን ስናስብ የበለጠ እንድንተጋና የደማቸውን ዋጋ የምንከፍል እንሁን፡፡

 ነሐሴ 1/2008 በባህርዳር የነፃነትና የፍትህ የፍና ወጊ ድምጽ ከፍ ብሎ ሲሰማ ብዙ ጀግና ወንድምና እህቶቻችን በወያኔ ነብሰ በላው ገዳይ መንግስት ያጣንበት ቀን በመሆኑ እችን ቀን ለኛ ለወገኖቻቸው ሲሉ በከፈሉት መስዋእትነት ፈጣሪ ነብሳቸውን በመልካም ስፍራ እንዲጎበኝልን የሁላችንም ፀሎት በመሆኑ ነብስ ይማርልን።

#ሰለሞን ይመኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.