‎የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ፋሽስት ወያኔ) ጎንደርን የማዳከም ድብቅ ምስጢር – ሰለሞን ይመኑ

ሪፖርተር ጋዜጣ ሀሙስ እለት ነሀሴ 13/2009 ባወጣው ሰበር ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በቅማንት ብሔረሰብ የማነት ጥያቄ ላይ ብሔረሰቡ ከአማራ ህዝቦች ጋር ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀብሌዎች ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ መሰረት በዝግጅት ላይ መሆኑ ዘግቧል ይህ የፍሽስት ወያኔ የእፍኝት ልጆች ድኩማን ሃሳብ መግቢያ መውጫ ያሳጣውን የአማራውን ትግል ለማዳከም በተለይም ጎንደር ላይ እየተደረገ ያለው ወያኔን የሚያንቀጠቅጥ ትግል ለማዳከም በዚች ድኩማን ጭንቅላት የተወጠነች የተለመደች የትግል አቅጣጫ የማስቀየሪያ የወያኔ ሰይጣናዊ አስተምህሮ ነው፡፡

 

ከዚህ በፊትም ወያኔ እንደተለመደው በጠላትነት የፈረጀውን የአማራ ህዝብ እንደማዳከሚያ ዘዴ ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ብሔሮችን የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ መገፍፍት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማስፈጸም ፍሽስት ወያኔ አሁን ከተነሳው ህዝባዊ አመጽ ቀደም ብሎ በ 2005 እና 2006 ዓ.ም ጀምሮ የቅማንት ብሔረሰብ የብሔረሰብ ጥያቄ እንዲያነሳ በእነ አባይ ፀሃየ እና በእነ አባይ ወልዱ የተንኮል ፍታውራሪነት ይህን ኮሚቴ አደራጅተው በጣም በሚገርም ሁኔታ የኮሚቴው ዋና ጽፈት ቤት ደግሞ መቀሌ ከተማ እንዲከፈት ተደረገ እና በዚህ መሃልም ኮሚቴው መቀመጫውን መቀሌ አድርጎ በመንግስት ወጭ ፌደሬሽን ምክር ቤት ሲመላለስ እና በቂ በጀት ተመድቦለት ሲመላለስ ወያኔ ያልጠበቀው እንግዳ ነገር ተከሰተ ይህም ወያኔ ለኮሚቴው በሚያፈሰው የህዝብ መቀስቀሻ ገንዘብ የጦር መሳሪያ እንደተገዛበት እና ከግብጽም የመሳሪያ ድጋፍ በማግኘት የተወሰኑ ከወያኔ ጋ የተጣሉ የብሔሩ ተወላጆች በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ አላጥሽ በሚባለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከተወሰኑ ወያኔ ካደራጃቸው ኮሚቴዎች ጋ ተገኙ እና ወያኔም የተወሰኑትን ገሎ ከተማ ውስጥ ያሉትንም ሌሎች ተሳትፎ አድርገዋል የተባሉትንም ከ 200 ሰዎች በላይ በመተማ እስር ቤት ታስረው ከቆዩ በኋላ በበረከት ስመኦን ት እዛዝ መሰረት ምርመራው ተቋርጦ የተወሰኑት ሲፈቱ የተወሰኑት ክሱ ቀጠለ በመቀሌ ያለው ዋናው ጽ/ቤትም አበቃለት፡፡

ክሱ በጎን እየቀጠለ በ 2007 እና 2008 ህዝቡ እንደ አዲስ ኮሚቴዎች ካልተፈቱ በሚል ተደጋጋሚ ረብሻ ሲከፈት ጥያቄውን ባነሱት ሰዎች ላይ በጠራራ ጸሃይ ከ 100 በላይ የብሔሩን ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ተለይተው በፌድራል ፖሊስና በመከላከያ የተፈጸመውን ግድያ በአይኔ ለማይት ችያለሁ፡፡

ደምን በደም ለመመለስ እንደ አንድ ጎረምሳ ድኩማን ሃሳብ የያዘው ፍሽስት ወያኔም ወዲያው ይህን የፈሰሰ ደም በሌላ የደም ካሳ ለማስከፈል የብሔሩን ተወላጆች ሰብስቦ ግድያውን የፈጸሙት አንዳንድ የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸው በማለት በጎንደር ሲኒማ አዳራሽ ሰብስቦ የታወረ አማራ ጠል የዘር መርዙን ወያኔ መዝራት ሲጀምር ተሰብሳቢው የገደለን ራሱ ወያኔ ነው እኛ ተጋብተን ተዋልደን የምንኖር ሰዎች ነን ለማጋጨት ያደረጋችሁት ሴራ ከሽፏል በማለት ስብሰባው ሲበተን ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ እንደገና ሌላ ኮሚቴ አዋቅሮ ከዚህ በፊት በፌደሬሽን ምክር ቤት እና በህገ መንግስቱ መስፈርቶች መሰረት የብሔ ማንነትን አያሟላም በማለት ውድቅ አድርጎት የነበረውን ውሳኔ እንደገና ሽሮ ለብሔሩ ተራራማ አካባቢዎችን መርጦ እውቅና ሰጥቻለሁ አለ ይህ ጉዳይም የይስሙላ በመሆኑ የብሔሩ ተወላጆችም አንዱ ካንዱ ጋር ሳይለያይ እንደድሮው በጋራ ተጋብቶ ተዋልዶ እየኖረ ነው ለወደፊቱም የህብረተሰቡ ህልውና ይህ ነው፡፡

እንግዳ የሆነው ሌላው ወቅታዊው የወያኔ ሴራም ጎንደርን ለማዳከም በሚል በማእከላዊ ኮሚቴው በአባይ ወልዱ አቅራቢነት የቀረበውና በስምምነት ጸድቆ ወደ ተግባር የሚገባው አዲሱ የህውሃት ሴራ ስ/ጎንደርን ዞን ለሁለት መክፈል ሲሆን ይህም ሌላ አዲስ ዞን ደባርቅና አካባቢውን ይዞ መመስረትና አዲስ መዋቅር መፍጠር ሲሆን ይህም ወረዳዎች ተከልለው አስተዳደሩም ተዋቅሮ አልቋል፡፡ ህውሃት ይህን ዘዴም ጎንደርን በቀላሉ ለመቆጣጠር ይቀለኛል ብላ ታስባለች፡፡

ሌላኛው ደግሞ የቅማንት ብሔር ያልጠየቀውን የፌደሬሽን ምክር ቤት በራሱ አነሳሽነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በቅማንት ብሔረሰብ የማነት ጥያቄ ላይ ብሔረሰቡ ከአማራ ህዝቦች ጋር ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀብሌዎች ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የምርጫ ቦርድ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ የቀረበለት መሆኑን እና በጥያቄው መሰረት ምርጫ ቦርድም በዝግጅት ላይ መሆኑ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ይህም ፍሽስት ወያኔ ሌላ የእርስ በእርስ ጦርነት ያመጣልኛል ያለው የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ የተነሳበት ሲሆን ነገር ግን ይህ ህዝብ በፍሽስት ወያኔ ጥላቻ ደሙ ውስጥ የተሳሰረ የማይበጠስ አንድነት እንዳጎለበተ ለፋሽስት ህውሃት ማን በነገረው? ፍሽስት ወያኔ ከሸረበው የመከፋፈል ጥላቻ ይልቅ ህዝቡ ውስጥ ያለው የአንድነት ፍቅር እንደሚበልጥ ወያኔንና ተላላኪዎቹን በድል ያንበረከኩ የአንድነት ክንዶችን ወያኔ ታውቀዋለች ይህ የፍሽስት ወያኔ ፍራቻም ነገም ሌላ ክፍፍል መፍጥሩ ስለማይቀር አስተዋዩ ህዝብ ያለምንም ደም መፋሰስ የወያኔ ሴራ እንደሚያከሽፍ እርግጠኛ መሆን ቢቻልም ውስጥ ለውስጥ የሚላላኩና ለዚህ ርካሽ መንግስት ህዝቡን ለማጋጨት ከወያኔ ጎን የተሰለፉ ከጎናችን ካሉ ባንዳዎች እንድንርቅ ግድ ይላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.