የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ድግስ በኃላ ቀር ክልል – ከአካደር ኢብራሂም አኩ

በኢትዮጲያ ውስጥ ካሉት ክልሎች ሁሉ ኃላ ቀር ክልል እየተባለ የሚጠራው የአፋር ክልል በመጪው አመት ኅዳር ወር የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ዝግጅቱ ለወያኔ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማገኘት ቢሆንም ለብዙዎች ግን መቋቋም ከሚችሉት በላይ ከባድ እየሆነባቸው እንደሆነ ይነገራል።
የፌደራል መንግስት ለዚህ ድግስ የሚወጣው ወጪ ሙሉ በሙሉ  መመደቡን ቢያስታውቅም አብዛኛው የክልሉ መንግስት ስራተኞች እንደሚሉት ከሆነ በክልሉ መንግስት ከአንድ አመት በፊት የተጀመረው የደሞዝ ቆረጣ መቋቋም እንዳልቻሉና በዚህ በዓል መማረራቸውን ይናገራሉ።
 
የአፋር ክልል የሚባለው ክልል ከተመሰረተ ጀምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በሦስት ይከፈላሉ።
ጠግቦ አደር፣ቀምሶ አደር እና ሰምቶ አደር።
ጠግቦ አደሮች የሚባሉት በክልል መንግስትነት ስም የወያኔ እምነት የተጣለባቸውና ከክልል እስከ ወረዳ በስመ ልማት የሚመደበውን ገንዘብ ከነቤተሰቦቻቸው የሚዘርፉ ሲሆኑ፤
ቀምሶ አደሮቹ ደግሞ እንደ መምህራኖች፣ ተረ የቢሮ ስራተኞች፣ ፖሊሶችና ጡረተኞች ናቸው።
ሰምቶ አደሮች የሚንላቸው መላው የአፋር ህዝብ ሲሆን ላለፉት 26 አመታት ከመስማት ውጪ ማየትም ሆነ መጨበጥ ባልቻሉት ዕድገትና ብልጽግና ኑሮዋቸው የሚገፉ ናቸው።
አሁን ታዲያ የሚገርመው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ለማክበር ጠግቦ አደርና ቀምሶ አደር ብቻ ሳይሆን ሚስኪኑ ሰምቶ አደርም ጭምር ፊየሎቹንና ከብቶቹን በግደታ አዋጡ ተብለው በየቀበሌው ይህን ያህል ከብት ወይም ፊየል አምጡ ተብለው ደሃውን ህዝብ እያማረሩ መሆኑን በተለያዩ መንገድ አርጋግጫለሁ።
 
በጣም የሚያሳዝነው ግን ተረጂዎች እንኳን ሳይቀሩ ከሚሰጣቸው ዕርዳታ ተቀንሶ ለዚህ ድግስ እንዲውል እየተደረገ መሆኑን ይነገራል።
 
ለመሆኑ ይሄ ሁሉ መዋጮ ለአንድ ቀን ዝግጅት ለምን አስፈለገ ?
ለዛውም የፌደራል መንግስት የመደበው በጀት እያለ።
 
አንደኛ በአፋር ክልል ከሚመደበው አመታዊ በጀት አብዛኛው ምንም ልማት ሳይሰራበት የሚወራረድ መሆኑን  ላስታውስችሁና፣
አሁንም ሌላው የክልሉ ወረዳዎችና ከተሞች በክፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ሰለማይጎበኙ እንደዚሁ የሚቀጥሉ ሲሆን፤ የክልሉ ዋና ከተማ ሰመራን ጨምሮ ለዝግጅቱ መዳራሻ የሆኑ ከተሞችን ለግዜው ማሳመርና ማስመሰል ይጠብቅባቸዋል።
ሰለዚህ ይህን ሁሉ አመታት ሰርተናል እያሉ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር የዘረፉበት መንገደች፣ የመንግድ ዳር መብራቶች፣ የተለያዩ የመንግስት አደራሾች፣ ወዘተ ማደስ አለባቸው።
ለዚህ ነው ሚስኪኑ አርብቶ አደር ሳይቀር ፆፆሙን እያደረ እንዲያዋጣ የተፈረደበት።
 
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ያው እንደተለመደው አጋጣሚውን በመጠቀም ማዋጮውን ለራሳቸው ኪስ ማደለቢያ የሚያውሉ አንዳንድ ኃላፊዎች በመኖራቸው ነው።
 
ለምሳሌ፤ ከወራት በፊት የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት ለተከታታይ ወራት ሙሉ ደሞዝ እንዲያዋጡ ታዘው ሲቆረጥባቸው ለምን እንደሆነ ኢንኳን እንዳልተነገርቸው ይገልፃሉ።
ቁምነገሩ ግን የልዩ ሃይል አዛዦች ለህክምና ታይላንድ የሚሄዱበት፣ ለዑምራና ሓጅ ወደ ሳዑዲ አራቢያ የሚሄዱት ከእኛ በሚቆርጠው ደሞዝ መሆኑን አይተናል ብለው ነበረ።
ይሄ ሁሉ ግን አንዳንዴ ሳስበው ይገርመኛል።
ምንም እንኳን የለለ ውሸት ቢሆንም ወያኔ አንድ ትልቁ የሚመካበትና ደጋግሞ የሚቀሰቀስበት የብሔር ብህረሰቦች መብት አመጣሁበት የሚለው ቀንን ማክበር ይህን ያህል ተቃውሞ ካሰነሳበት ያውም የራሱ ስራተኞች ሳይቀሩ ታዲያ ወያኔ ምን ቀረው ?
ለማንኛውም የብሔር መብትን በተመለከተ አንድ የአፋር ተወላጅ የሆኑ ገጣሚ  የአሊገረብ ጥቁር ነብር በሚል የብዕር ስም በ 2015 የላኩልኝ ግጥም በጊዜው ላላያችሁና እንዲሁም ደግማችሁ እንድታነቡ እየጋበዝኩዋችህ ልሰናበት።
ቸር ያሰማን።
 
ጥቂት ሆዳሞች።።።።
 
ጥቂት ሆዳሞች ህዝብን ሲያታልሉ
በሲመ ልማት ኪሳቸው እየሞሉ
አገር አደገች ብለው ድርቅ ብለው ይዋሻሉ
እባካቹሁ ሰዎች አንድ ነገር በሉ
አፋር አፋር የኢትዮጲያ አይን የኢትዮጲያ ክብር
የሰው ዘር መገኛ ታሪካዊ ምድር
ሉሲ እኮ አለች የቅርብ ጊዜ ምስክር
ተፅፎ አያልቅም ስንት ብየ ሊዘርዝር
ከዳሉል ጀምሮ፣ ባራሕሌ፣ ኮናባ፣
ኤረብቲ ፣ማጋሌ፣ አበኣላ፣ ስትገባ
ከርስ መሬቶቹዋ በማዕድን ተውባ
አገሬ ተሰቃየች በድህነት ተርባ
ጨው፣ ፖታሹ፣ ወርቅ፣ የተከበረ ድንጋይ፣
በውስጧ ተቀብረው ይሄ ሁሉ ስቃይ
የት ያለ እድገት ነው በአይን የማይታይ
እነ ሲሮ የሚጮሁት የወያነ አገልጋይ
ዞን አራት ካሉዋን፣ ያሎ፣ ቴሩ
የማዕድን ሀብታችን ተጠንተው ብመረመሩ
ማእቀብ ተደርጎበት እንዳይቆፈሩ
የአብዴፓ መሪዎች ለሆዳቸው ያደሩ
አንዱ የሄ ነው ከድብቅ አጀንዳቸው፣ ከሚስጥሩ
ዞን አምስትም እንደዚሁ፣ ዞን ሶስት ጋቢ ራሱ፣
ዞን አንድም እደዚሁ አውሲ ራሱ፣
ህዝብን እያጋጩ እርስ በርሱ
አገር እንዳይለማ በህብረት እንዳያርሱ
በላሌ፣ በሰዳዓ፣በሆራ፣በኬኬ እየዘለሉ ማጫወት
በቴልቪዢን መስኮት ደጋግሞ ማሳየት
በዚሁ ከሆነ የተጠበቀው መብት
ዶሮን ሊያታልሏት በማጫኛ አሰረዋት
ቋንቋችን ባህላችን ከጥንት የቆየ ነው
ህጋችን ደንባችን የአፋር ማድዓ ነው
አዲስ ነገር የለም አሁን ያገኘነው
አዲስ ነገር ቢኖር የቀኝ አገዛዝ ነው
የህዝብ ጥያቄ አንድና አንድ ብቻ ነው
ፊትህ፣ ዴሞክራሲ፣ሰፍኖ በልማት ማደግ ነው
መሪያችን ሲሆን እኛ የመረጥነው
በቋንቋቸው፣ በስማቸው አፋሮች
በእጅ አዙር የሌላ አገልጋዮች
አቅም የሌላቸው ድንቆሮ መሀይሞች
ህዝበባችን አጠፉት የአብዴፓ መሪዎች
ሐጂ ሱዩም፣ አንበጣ እስማዕል ሲሮ
ሌላ መሪ አላቸው በድብቅ በሰተጓሮ
ትእዛዝ የሚያስተላልፍ አጀንዳን ዘርዝሮ
ገብረፂዮን ወያኔ ከፈደራል ቢሮ
የተማረ አልወጣም ከዚህ ሁሉ ወጣት ?
ወራሽ ሰለታጣ ነው እንዴ፧ ሲሮን የሚያምኑት ?
ህዝባችን እያየ አይናቸውን የጨፈኑት
ዝም ብለን አናይም እየጠፋ አገራችን
 
ገጣሚ
፨ የአሊገረብ ጥቁር ነብር፨

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.