በኦሮሚያ የታወጀው የአምስት ቀን የስራ አድማ-በሻሸመኔና አምቦ መኪኖች እየተቃጠሉ ነው ተባለ – በወንድወሰን ተክሉ

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አከባቢ በሻሸመኔ እና በአምቦ ከፍተኛ የንበረት ቃጠሎ መከሰቱን ከስፍራው ከደረሰን የስልክ መረጃ መረዳት የተቻለ ሲሆን የተቃጠለውም ንብረት የስራ ማቆም አድማ የጣሱ ተሽከርካሪዎች ናቸው ብለዋል።

በመላ ኦሮሚያ ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ የሚዘለቅ ጠቅላል የስራ ማቆም አድማ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ዛሬ ሲሆን በዚህ ዙሪያ የተጠናቀረው ዘገባ እንደሚከተለው ቀርባል።

**ትግሉ ከአቅማችን በላይ በመሆን በህዝብ እጅ ገብታል-ተቃዋሚ ፓርቲዎች።

በመላ ኦሮሚያ ለ5 ቀናት የታወጀው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተግባራዊ በሆነበት የመጀመሪያው ቀን አጠቃላይ የንግድ ተቃሞች እና የትራንስፖርት አገልግት ሙሉበሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ከተሞቹን በጸጥታ አጥለቅልቆ እንደዋለ መረዳት ተችላል።

በምስራቅ ኦሮሚያ ጨለንቆ፣ደደር፣አሰቦት፣በዴሳ፣አወዳይ፣ገለምሶ፣ጨርጨር ከተሞች በሙሉ ነዋሪው ቤቱን ዘግቶ እቤት መዋሉን የጀርመን ድምጽና የቪ.ኦ.ኤ ጋዜጠኞች እየደወሉ አረጋግጠዋል።የንግድ ተቃሞች፣የትራንስፖርት አገልግሎት እና እንዲሁም የግል ትላላቅ ድርጅቶችም ሳይቀሩ ተዘግተው እንደዋሉ ለማወቅ ተችላል።

እንደ የቪ.ኦ.ኤ ዘገባ በምስራቅ ኦሮሚያ ካለ ሰው ጋር በስልክ ንግግር ዘገባ ከሆነ በአምስቱ ቀን የስራ አድማ ጥያቄዎቻቸው ካልተመለሰ የመታገያ ስልታቸውን ቀይረው እስከመጨረሻ እንደሚታገሉ ገልጸዋል።

የአምስቱን ቀን የስራ አድማ ያስተባበሩ ሃይሎች አገላለጽ የስራ አድማው ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በእስር እየተሰቃዩ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱልን፣ኢ-ፍትሃዊ የሆነው የግብር ተመን ይነሳልን እና ያለአግባብ እየተዘረፈና ለሱማሌ ክልልም እየተሰጠ ያለው መሬት በአስቸካይ ይቁም የሚል ጥያቄ ሲሆን ስርዓቱ ግን አንድም የፖለቲካም ሆነ የህሊና እስረኛ የለኝም በሚለው አቃሙ ይታወቃል።

የቪ.ኦ.ኤ ጋዜጠኛ ካነጋገራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦ.ፌ.ኮ ም/ል ሊቀመንበር “እኛ ይህ እንዳይመጣ መንግስትን በሰላም ተለማመጥን ለመንን ግን የሰማን አልሆነም። አሁን ጉዳይ ከፖለቲካ ድርጅቶች እጅ ወጥቶ በህዝቡ እጅ ገብታል።ከእኛ በላይ የሆነ ነው “ሲሉ ተናግረዋል።

የስራ ማቆም አድማው በሰሜን ፍቼ መስመር በምእራብ ከአስኮ ጀምሮ እስከ ደንቢ ዶሎ ድረስ በተዘረጋው አውራ መንገድ ላይ አንዳችም ትራንስፖርት እንዳልታየ ማወቅ ተችላል። ከአዲስ አበባ ቡራዪ የታክሲ አግልግሎት የሌለ ሲሆን በደቡብ ወሊሶ፣ሻሸመኔ፣አሩሲና በጅማ በስራ ማቆም አድማው ጸጥ እረጭ ብለዋል።

በመንግስት በኩል አድማውን ለማክሸፍ ሰራዎቱን በማሰማራት ነጋዴዎችን በግድ እንዲከፍቱ ሲያስገድድ የታየባቸው ከተሞች ቁጥር ትንሽ እንዳልሆነ መረዳት የተቻለ ሲሆን የማሸግ ተግባር መፈጸሙንም መረዳት ተችላል።

በአምቦ፣በሻሸመኔ፣በወሊሶ፣በነቀምት፣በምስራቅ ኦሮሚያ ወታደሮች በግድ ለማስከፈት የሞከሩባቸውና የማሸግ ተግባር የፈጸሙባቸው ከተሞች ናቸው።በሻሸመኔ የተሰማሩት የስርዓቱ ታጣቂዎች ህዝቡን እቤት መቀመጥ አይቻልም እያሉ ደግሞም ሁለት ሶስት ሆናችሁ መሄድ አይችልም በማለት እስርሰበርሱ የሚቃረን ህግ እንደሚያዙ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

የኦሮሚያ ግዛት በኢ-ፍትሃዊነቱ የታወቀውን እና በጠ/ ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በሌቦች የተተመነና 40%ትክክል ያልሆነ በተባለው ግብር ተመን እንደ አቻው የአማራ ግዛት ያለአግባብ የተጫነበት ሲሆን መሬቱን ለሱማሌ ክልል እየተሰጠበት በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ልጆቹ በእስር ቤት እየማቀቈበት ያለ ግዛትና ህዝብ እንደሆነ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.