ሲያትል: በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው የሦስቱ ኢትዮጵያን ህጻናት የፍትሃተ ፀሎትና የቀብር መርሃ ግብር

ካልጋሪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ተመስግነዋል

በሲያትልና አካባቢው ለምትገኙ በሙሉ፦

እጅግ አሳዛኝ በሆነ የመኪና አደጋ በለጋነታቸው ህይወታቸው የተቀጠፈው ሶስት ህፃናት ስርአተ ቀብራሸው Saturday August 26 2017 ስለሆነ በሃዘን ልባቸው የተሰበረውን ቤተሰብ ለማፅናናትና በፍትሃተ ፀሎታቸው እንዲሁም በግብአተ ቀብራቸው እንድትገኙ የሚቀጥለውን መርሃ ግብር ተገንዘቡት።

ይህ አሰቃቂ አደጋ በደረሰበት የካናዳ ካልጋሪ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራዊያንና የሃገሬው ኗሪወች እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት ላደረጉት እጅግ ልብ የሚነካ ፈርጀ ብዙ ድጋፍ ሃዘንተኛ ቤተሰቦች ጥልቅ ምስጋና አቅርበዋል። በሲያትልና አካባቢው የሚገኘው ወገንም ስራየ ብሎ ከሳምንት በላይ አብሮ ሲያዝን ሲተባበርና ሲያፅናና በመሰንበቱ እግዚአብሔር በበጎ ይክልላቹህ ብለዋል። በሃገርቤትም ሆነ በአለም ዙርያ ያለው ወገን በሙሉ ጉዳዩን ሰምቶ ሁለገብ እርብርቦሽ በማድረግ የሃዘናችን ተካፋይ እንዲሆን የዜና እረፍቱን ላሰራጩት የመደበኛና ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ጥልቅ ምስጋና አቅርበዋል። በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ ድጋፋቹህን በሰፊው ላበረከታቹህ በሙሉ እጅግ እናመሰግናለን ብለዋል።

የስርአተ ፍትሃትና ቀብር መርሃግብር፦

1) ፀሎተ ፍትሃቱ 9Am በሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን/ገዳም
940 26th Ave S. Seattle
2) እኩለ ቀን(Noon) ጉዞ ወደ መቃብር ስፍራ ይጀመራል
3)1PM ላይ ስርአተ ቀብር የሚደረግበት

Washington Memorial Park
16445 International Blvd.SeaTac wa

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.