የጎንደር መሬት ለሱዳን አይሰጥም ሲል ወጣት አባይ ዘውዱ በስርዓቱ የማሰቃያ ቶርቸር የምድር ሲኦል ከማዕከላዊ አንስቶ እስከ ቂሊንጦ የግዞት

የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አመራር የአብራጅራ ወጣት አባይ ዘውዱ

ስንታየሁ ቸኮል

በዘረኞች የደረሰብን የግፍ በትር የተከፈለው ዋጋ የምንረሳው አይደለም! የጎንደር መሬት ለሱዳን አይሰጥም ሲል ህዝብን አስተባብሮ የሚያታግል የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አመራር የአብራጅራ ወጣት አባይ ዘውዱ ከስርዓቱ በተሻለ ሞጋች ሐሳብ ይዞ ወደ ትግል አለም ተቀላቀለ በተለይ ዘር ቆጣሪ የሆነ ቡድን አማራ ለሆነ ሰው የሚጠብቀው የበቀል ሰይፍ ሁሉም ያውቀዋል፡፡

አባይ ዘውዱ በስርዓቱ የማሰቃያ ቶርቸር የምድር ሲኦል ከማዕከላዊ አንስቶ እስከ ቂሊንጦ የግዞት ማራገፊያ በህመም እየተሰቃየ ሶስት አመት የእስር ጊዜ አሳለፈ ፡፡ በመጨረሻም በካንጋሮ ችሎት የ4 አመት ከሁለት ወር ፍርድ ከተወሰነበት በኃላ ዝዋይ እስር ቤት ተዘዋውሮ የእስር ጊዜውን በዛ አየጨረሰ ይገኛል፡፡ አባይ ማዕከላዊ የቆየበት ጊዜ እንዲቆጠር ከማዕከላዊ ደብዳቤ ተፅፎ ወደ ዝዋይ ተልኳል፡፡ ይሄ ጀግና በዚህ ወር መጨረሻ ለአዲስ አመት ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ” በአባይ እና መሠል ታጋዮቻችን ለነፃነት ትግል የከፈሉት ዋጋ ሁሌም አንረሳውም!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.