ኢት-ኢኮኖሚ (ህወኃት ቤት ጥይት፣ህዝብ ቤት ክብሪት አይጠፋም!!!) – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

(ክፍል አንድ)                                            

የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይማር ያስተማራቸውን ህዝቡ ጥያቄ መሠረት በማድረግ በቀ.ኃ.ሥ ዘመን በ1953፣ በደርግ ዘመን በ1981 እና በወያኔ ዘመን በ2002 ዓ/ም የአገዛዝ ሥርዓት ላይ ተቃውመው መንግሥት ለመቀየር ተንቀሳቅሰው የነበረበት ወርቃማ ታሪክ ያፃፉበት ዘመን ነበር፡፡ በዚህም የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት  ትግል ህብረ-ብሄር የሚወክሉ ብዙ ጀነራል መኮንኖች ክብር ህይወታቸውን ለኢትዩጵያ ህዝብ ሠውተዋል፡፡ ክብርና ሞገስ ለተሠው ህብረ-ብሄር የኢትዩጵያ ሠራዊት አባላት ይሁን፡፡ ለሃገር ሉዓላዊነትና ለወገን ፍቅር ብለው ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ምርጥ ጀግኖች ለዘላለም ሲዘከሩ ይኖራሉ፡፡

በ1953 ዓ/ም የቀ.ኃ.ሥ መንግስት ከስልጣን ለማውረድ በተደረገው ሙከራ የተሠው ህብረ-ብሄር (ከአማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ) የኢትጵያ ልጆች እናስታውስ፡-

1 ሜጀር ጄነራል መንግሥቱ ንዋይ 2 ሜጀር ጄነራል ፅጌ ዲቡ 3 ሜጀር ጄነራል ወርቅነህ ገበየሁ
4 ግርማሜ ንዋይ ወዘተ    

በ1981 ዓ/ም ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያምን ከስልጣን ለማውረድ በተደረገው ሙከራ የተሠው ህብረ-ብሄር (ከአማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ) የኢትጵያ ልጆች እናስታውስ፡-

በአዲስ አበባ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፈው ከተሰውት መኃል
1 ሜጀር ጄነራል መርድ ንጉሴ 2 ሜጀር ጄነራል ፋንታ በላይ 3 ሜጀር ጄነራል ኃይሉ ገ/ሚካኤል
4 ሜጀር ጄነራል ወርቁ ዘውዴ 5 ሜጀር ጄነራል አምሃ ደስታ 6 ሜጀር ጄነራል አለማየሁ ደስታ
7 ሜጀር ጄነራል ዘውዴ ገብረየስ 8 ብ/ጀነራል ደሣለኝ አበበ 9 ብ/ጀነራል  ሰለሞን በጋሻው
10 ብ/ጀነራል ተስፋ ደስታ 11 ብ/ጀነራል እንግዳ ወ/ አምላክ 12 ብ/ጀነራል እርቅይሁን ባይሣ
13 ብ/ጀነራል ነጋሽ ወልደየስ 14 ብ/ጀነራል ገናናው መንግሥቴ 15 ብ/ጀነራል ተስፋዬ ትርፌ
በአስመራ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፈው ከተሰውት መኃል ሜጀር ጄነራል ደምሴ ቡልቱ
16 ብ/ጀነራል አፈወርቅ ወ/ሚካኤል         17 ብ/ጀነራል ታዬ ባላኪር      18 ብ/ጀነራል ታደሰ ተሰማ
19 ብ/ጀነራል ወርቁ ቸርነት 20 ብ/ጀነራል ንጉሴ ዘርጋው 21 ብ/ጀነራል ከበደ መሀሪ
22 ብ/ጀነራል ተገኔ በቀለ 23 ብ/ጀነራል ከተማ አይተንፍሱ 24 ብ/ጀነራል ከበደ ወ/ጻዲቅ
25 ብ/ጀነራል ሰለሞን ደሣለኝ 26 ዶ/ር ኮሎኔል ጌታቸው አወቀ 27 ኮሎኔል መስፍን አሰፋ
28 ኮሎኔል ፋቃደ እንግዳ 29 ሌ/ኮ ዘርአይ እቁባአብ 30 ሌ/ኮ ዩሃንስ ገብረማርያም
31 ሻለቃ ካሳ ፈረደ 32 ሻለቃ ሚካኤል ማርቦ 33 ሻምበል ጌታሁን ግርማ

ምንጭ፡- ሳተናው፡- ኢዩብ ዘለቀ፡-የታሪክ ዓምድ፣የአየር ወለዱ መሃንዲስ …የግንባት ስምንቱ መፈንቅለ መንግሥት ስናስታውስ (እንደ ደረጀ ደምሴ ‹‹አባቴ ያቺን ሰዓት››ታሪካችሁ ይፃፋል! አትረሱም! )

ህዝባዊ ዴሞክራቲክ ጋርድ፡-የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት፣ቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. ድርጅቶች ለህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍን ውስጥ በመሰለልና የሃገሪቱን ምስጢርና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስለላ መረብ በማስገባት ከፍተኛ ጥቃት አድርሰዋል፡፡

በ2002 ዓ/ም መለስ ዜናዊ ለማውረድ በተደረገው ሙከራ የታሰሩ ጀነራል መኮንኖች የኢትዩጵያ ልጆች እናስታውስ፡-

  1 ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ጨርቆስ         2 ብ/ጄ አሣምነው ፅጌ ተበጀ      3 ሌ/ኮ ደምሰው አንተነህ ደመላሽ
4 ሻለቃ መኮንን ወርቁ አለሙ        5 ሌ/ኮ አለሁበል አማረ ዋሴ      6 ሌ/ኮ አበረ አሰፋ አበራ
7 ሌ/ኮ አለሙ ጌትነት አባተ       8 ሌ/ኮ ሰለሞን አሻግሬ አምበርብር 9 ሌ/ኮ ጌታቸው ብርሌ ደሴ
10 ሻ/ል ተመስገን ባይለየኝ ፀጋው  11 ሻለቃ አዱኛ አለማየሁ ገ/ማ እሸቴ 12 ሌ/ኮ ፋንታሁን መሃባ መፍቲ
13 ሻለቃ መሠከረ ካሣ ወንድም 14 ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ ተገኝ 15 ሻለቃ ፋናዬ ውቤ ሙጬ
16 መ/አ አባቡ ተፈሪ አለሙ 17 ሻለቃ አደፍርስ አሣምነው ክብረት 18 ያረጋል ይማም ሚኪ           
19 ክፍሌ ስንሻው ታገደ 20 መዘምር የሸዋስ መንገሻ በየነ 21 መንግስቱ አበበ አረጋዊ ሳሚ    
22 እማዋይሽ አለሙ ወ/ሚካኤል 23 ጎሽራድ ፀጋው አጋፋሪ 24 መላኩ ተፈራ ጥላሁን
25 ዳን ያባቱ ስም ያልታወቀ            26 አማኑኤል ያባቱ ስም ያልታወቀ 27 አወቀ አፈወርቅ            
28 ዋና ሣይጅን አመራር ባያብል ካሣ 29 ኢንስፔክተር አራጋው አስፋው ረታ 30 ም/ሣጅን ጎበና በላይ አየለ
31 ረ/ሣጅን ይበልጣል ብርሃኑ ተፈራ 32 ም/ሣጅን የሸዋስ ምትኩ ቸኮል 33 ሣጅን ወድነሽ ተመስገን አለሙ
34 ሣጅን አይተን ካሣ መኮንን   35 ጌቱ ወልዴ አባይ ሆይ      36 ጌቱ ወርቁ ንዳው                   
37 ፅጌ ኃብተማሪያም ጨሚሣ 38 ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር      39 አንዳርጋቸው ፅጌ ኃብተማሪያም
40 ሙሉነህ እዩኤል ፋኔ       41 ኤፍሬም ማዴቦ 42 ዳንኤል አሠፋ
43 ቸኮል ጌታሁን  44 መስፍን አማን 45 ፋሲል የኔአለም
46 ደረጀ ሃብተወልድ                               

 

የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት በ14 ጁላይ 2009 እኤአ የሰዎችን የስልክ ንግግሮች ጠልፎ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ (የወንጀል መዝገብ ቤት) በማስረከብ በተከሳሾቹ ላይ ፍርድ ቤት እንደማስረጃ ተቆጥሮ ባደረጉት የስልክ ንግግር ብቻ ስለምን ጉዳይ እንደተወያዩ ሳይገለፅ በመንግሥት መገልበጥ ወንጀለኛ ተብለው በአሰቃቂ ግርፋትና ድብደባ ተደርጎባቸው እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የጠለፈውን የስልክ ንግግሮች የያዘ የስለላ ሠነድ ከመኃተምና ከፊርማ ጋር ተያይዞ በማስረጃነት (በክፍል ሁለት) ቀርቦል፣ ያንብቡትና የቴሌን ጆሮ ጠቢዎች ጠንቀቅ ይበሉ፡፡ የቻይናውያኑ ዜድቲኢ እና ሀዊ  ካንፓኒዎች ለዚህም ስራቸው ያለ አንዳች ነፃ ውድድርና ጨረታ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ሥራን ሁሉ እንዲሰሩ ተሰጥቶቸዋል፡፡ የቻይናዊያን ሾተላይ ሰላዬች፤ የቻይና መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽንና የኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ኃብት  በመቆጣጠርና የቻይና ኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ ደግሞ ብድር በማመቻቸት  99 በመቶ የኃብቱን ድርሻ በመያዝ ኢትዩቴሌኮም ፕራይቬታይዝ ለማድረግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ኢትዩቴሌኮም ዋናው መ/ቤት የህወሃት ዶ/ር ደብረፂዎንና የደህንነት መስሪያ ቤት ሹም ጌታቸው አሰፋ እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ የስልክ/ የሞባይል/ ኢንተርኔት የተለያዩ ድረ ገፆች፣ኢሜል (የፅሁፍ መልእክቶች)፣ በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ በሚገኙ ኢትዬጵያዊያን ዜጎች ላይ ስለላ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ከነዚህም መኃል በዴሞክራቲክ ጋርድ፣ የኢትዩጵያ የነፃነትና ዴሞክራቲክ ሃይል፣ በግንቦት ሰባት አባላቶች (አንዳርጋቸው ፅጌና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ)፣ጋዜጠኞች (ውጭ የተሰደዱ ሃያ በላይ ጋዜጠኞች)፣ጦማርያን (ዞን 9)ና ምሁራኖች (ዶ/ር ታደሠ ብሩ) የሙስሊም ህብረተሰብ፣ በፅንፈኝነት፣ አክራሪነትና መንግስት ግልበጣ ወዘተ  ፍርጆ በኢትዩጵያ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መጠቀሚያ በማድረግ ዜጎችን በማሰቃየት፣ በማሰር በመግረፍና በመሰወርና በመግደል የፈፀሙት ወንጀል ታሪክ ይቅር የማይለው የስለላ ተግባር በኢትዩጵያ ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤትና የኢትዩቻይና የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በማህተም ያረጋገጡትና  ያቀረቡት የስለላ ማስረጃነት በወህኒ ቤት የሚገኙት የህዝብ ልጆች የመከላከያ ሠራዊት አባላቶች ገሃድ ምስክሮች ናቸው፡፡ የጀነራል መኮንኖቹ (በዴሞክራቲክ ጋርድ) በስብሰባዎች ላይ ባነሱት ጥያቄዎች ውስጥ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የትግራይ የበላይነት ይወገድ፣ በሠራዊቱ ውስጥ በተለይ በሜቴክ የሙስናና ንቅዘት ይቁም፣ በኢትዩጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በአፍሪካ፣ የሙስናና የዝምድና ሥራ ይብቃ፣የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት በወታደራዊ ሣይንስ አመራር ችሎታ ያላቸው መሪዎች ይመራ፣ በሠራዊቱ ውስጥ ያለ የዘር አድሎ፣ የእድገት አድሎ፣የክልላዊነት የቡድን ሥራ ይቁም፣ወዘተ የሚሉ የሰራዊቱ ጥያቄን በመጠየቃቸው የታሰሩ ህብረ ብሄር የሃገራችን ብርቅያ ልጆች ናቸው፡፡  የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ፤የቻይና መንግስትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ምን ዓይነት እንደሆነ ለአመል ታህል እንመልከት፡፡ የቻይና መንግስት በአንድ ሃገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት መርህ አለኝ ቢልም ከኢትዬጵያ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ጋር በቴሌኮምኒኬሽን ዘርፍ በተለይ በኢንተርኔትና  በሞባይል አገልግሎቶች ላይ ስለላ በማድረግ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ነፃ ጋዜጠኞችን፣ዲያስፖራዎችንና ምሁራኑን በመሰለል ትልቅ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ስብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች፣የነፃ ፕሬስ፣የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ (የፓርቲዎች ውድድርና ምርጫ፣የሲቨል ሶሳይቲ የፕሬስ ነፃነት፣ሬዲዩ፣ቲቪ፣ጋዜጣ፣ድረገፅ፣ ኢንተርኔት፤ ወዘተ በቻይና መንግስትና ኮምኒስት ፓርቲ፤ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ መሬት፣ ባንክ ኢንሹራንስ፣ ቴሌኮምኒኬሽን፣ መብራት ኃይል ወዘተ በአጠቃላይ የግብርና፤ኢንደስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች በልማታዊ መንግስት ቁጥጥር ስር ሲሆኑ ስርአቱ በፖለቲከኛ ካድሬዎች ሙስናና ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት ውስጥ እንደሚገኝ እሙን ነው፡፡

የወህኒ ቤቶች ሁኔታ Prison and Detention Center Conditions

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የወህኒ ቤቶች ሁኔታ በተመለከተ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ሦስት የፊዴራል እስር ቤቶችና 120 የክልል መንግስቶች እስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ብዙ ይፋ ያልሆኑ እስር ቤቶች በሃገሪቱ ውስጥ ሲገኙ ከነዚህ መኃከልም በዴዴሳ፣ በብር ሸለቆ፣በጦላይ፣ሆርማት፣ብላቴ፣ታጠቅ፣ጅጅጋ፣ሆለታና ሰንቀሌ የጦር ካንፖች ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የወህኒ ቤቶች ሁኔታ ለእስረኛዎች ህይወት በጣም አስጊና ብዙ ሰዎች ተፋፍገው የታሰሩበትና ለመተኛት አመች ያልሆኑ ቦታዎች ናቸው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ለእስረኞች በቀን ስምንት ብር ወይም ግማሽ ዶላር ለምግብ፣ ለውሃና ለጤና ጥበቃ ወጪ ያወጣል፡፡ ብዙዎቹ እስረኞች ተጨማሪ ምግብ ቤተሰቦቻቸው እየገዙ ያቀርቡላቸዋል፡፡ የእስረኞች ጤና ጥበቃ በተመለከተ በፊዴራል እስር ቤቶች ውስጥ አስተማማኝ ህክምና አያገኑም፤ በክልል እስር ቤቶች ውስጥም የህክምና አገልግሎት የለም፡፡ በሃገሪቱ በሚገኙ ወህኒ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመኖሩ የተነሳ እስረኞች ንፅህናቸውን ለመጠበቅ ባለመቻላቸው ብዙዎቹ በጤና ችግር ይሰቃያሉ፡፡ እስረኞች አነስተኛ የህክምና አገልግሎት ብቻ ያገኛሉ፡፡ በወርሃ የካቲት በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ አንድ የጣልያን ዜጋ በህክምና እጦት የተነሳ ህይወቱ አልፎል፡፡ በአመቱ መገባደጃ ላይ በአጠቃላይ በግምት 86,000 ሽህ እስረኞች ሲገኙ ከዚህ ውስጥ 2,474 ሴት እስረኞች ሲሆኑ፣ 546 ህፃናቶች ከእናታቸው ጋር ታስረው ይገኛሉ፡፡ የወጣት ጥፋተኞች አንዳንድ ግዜ ሞት ከተፈረደባቸው ጎልማሶች ጋር በአንድ ላይ ይታሰራሉ፡፡ በአጠቃላይ ወንድና ሴት እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች ታስረው ይገኛሉ፣ ቤተሰቦቻቸውም ይጠይቆቸዋል፡፡ በሌላ በኩል  ቤተሰቦቻቸው የማይጠይቆቸው የተከለከሉ ጥቂት እስረኞች ይገኛሉ፡፡ The country has three federal and 120 regional prisons. There also are many unofficial detention centers throughout the country, including in Dedessa, Bir Sheleko, Tolay, Hormat, Blate, Tatek, Jijiga, Holeta, and Senkele. Most are located at military camps. Prison and pretrial detention center conditions remained harsh and in some cases life threatening. Severe overcrowding was common, especially in sleeping quarters.  The government provided approximately eight birr ($0.50) per prisoner per day for food, water, and health care. Many prisoners supplemented this with daily food deliveries from family members or by purchasing food from local vendors. Medical care was unreliable in federal prisons and almost nonexistent in regional prisons. Water shortages caused unhygienic conditions, and most prisons lacked appropriate sanitary facilities. Many prisoners had serious health problems in detention but received little treatment.  In April an Italian citizen died after receiving allegedly substandard medical treatment in Kality prison. At year’s end there were an estimated 86,000 persons in prison, of whom 2,474 were women and 546 were children incarcerated with their mothers. Juveniles were sometimes incarcerated with adults who were awaiting execution. Male and female prisoners generally were separated. Authorities generally permitted visitors. In some cases family visits to prisoners were restricted to a few per year.

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን በትግራይ ወህኒ ቤቶች ውስጥ አስረው በድብደባ በማሰቃየት፣ ከወላጆቻቸው እንዳይጠየቁ በመሰወርና በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እንዳይጎበኙ በማድረግ ያለፍርድ እንደረሸኖቸው በአቶ ገብሩ አስራት መፅሃፍ ይፋ ወጥቶል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጸጋዬ ገብረ መድህን(ደብተራው)፣ ይሳቅ ደብረፂዎን፣ ስጦታው ሁሴን፣ በለጠ አምኃ የኢህአፓ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩና ሌሎች አንጋፋ አባሎች ውስጥም ደሳለኝ አምሳሉ፣ ሃጎስ በዛብህ፣ ተክላይ ኃይለ ሥላሴና ከሱዳን ተላልፊ የተሠጠው አዛነው ደምል፣ይገኙበታል፡፡ ከ1993 እኤአ ከአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ጎሞ ጎፋ በህወሓት የተሰወሩና የት እንዳደረሶቸው የማይታወቁት ውስጥ አበራሽ በርታ፣ ለማ መኮንን፣ ተስፋዬ ከበደ፣ ወንዱ ሲራክ ደስታ፣ እዬብ ተካበ፣ ሞት ባይኖር፣ አይነኩሉ፣ ዬሴፍ፣ ጋይምና ጎደኞቹ በቅሎ ቤት አካባቢና ጃታኒ አሊ በናይሮቢ  በህወሓት የጦር አበጋዞች ሲገደሉ ሌሎች የደረሱበት አይታወቅም፡፡ በቅርቡም ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዩጵያ የመጣው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ፣ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተቃዋሚ የህዝብ ልጆችን እያደኑ በመግደል ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔዊ ተግባር ፈፅመዋል፡፡  የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት መሪ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ተወልደ ወልደ ብርሃን፣በረከት ስምኦን፣አባይ ፀሃይዬ፣አለምሰገድና ኃያሎም አርዓያ ለግድያው ተጠያቂ ሲሆኑ ሌሎቹም ግልገል ፋሽስቶች አንድ ቀን ለፍርድ እንደሚቀርቡ ከደርግ መንግስት መማር ይገባቸዋል፡፡ በኢትዩጵያ የህሊና እስረኞች፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች በሽብርተኛነት ስም አስረዋቸዋል፡፡  የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ መሪዎችን እነ ዶክተር መራራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ ሌሎቹም በሽብርተኛነት ስም አስረዋቸዋል፡፡ እነ ብርጌደር ጀነራል ተፈራ ማሞ፤ ብርጌደር ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ እማዋይሽ አለሙ ወ/ሚካኤል፣ሌሎቹንም የፖለቲካ እስረኞች አድርጎል፡፡

የወያኔ ጠቅላይ ጦር ሠፈር የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ጦር ሠራዊት፣ አየር ወለድ፣ ዓየር ኃይል፣ የፖሊስ ሠራዊት ወዘተ፤ ከላይ ከዋናው ኤታማጆር ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ/መሀመድ ዩኑስ ጀምሮ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሬጅመንቶች፣ ሻለቃ፣ ሻምበል ከፍተኛ ማዕረግ በትግራይ የህወኃት ቡድን በትግራይ የዘር ሃረግ ወይም በአንድ የዘር ሃረግ ስልጣኑ የተያዘ ነው፡፡ የኢትዩጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የሠራዊቱ ዋና ጦር ሠፈር በትግራይ ክልል ውሰጥ የጦር መሳሪያው  መከማቸቱ የኢትጵያ ዓየር ኃይል ከደብረዘይት ሠፈሩ ወደ ትግራይ፣ ማይጨው ተራራዎች ተቦርቡረው የጦር አይሮፕላኖቹ ሠፈር መቀየሩ ጉዳዩ የዘረኝነት ስሜት እንጂ በጥናት የተደገፈ አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ በህወኃት የተነደፈ የአናሳ ዘውጌኛነት የስነ-ልቦና ደዌ ወይም በሽታ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዩጵያን ካልገዛና ካልመራ ህዝቡ ይበቀለናል በሚል እብሪትና ፍርሃት የተነሳ፤ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊትና የመሣሪያ ክምችት፣ የታንከኛ ብርጌድ በሙሉ በትግራይ ክልል ውስጥ መገኘቱ በትረ-ሥልጣናቸውን በቀጣይና በዘለቄታ ከደደቢት ዋና ጠቅላይ ጦር ሠፈር ለመቆጣጠር የታቀደ ሴራ ነው፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በሌላው የኢትዩጵያ ክልሎች ውስጥ የህወሃት አባላቶች በሙሉ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ታጣቂዎች ማድረጉ፣  ፀሃይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ያደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ልጆቹ መታጠቃቸውን ይመሰክራል!!! ለምን ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታቸው አይመለሱም የእናንተ ወርድያ ሆነው እስከመቼ ይኖራሉ እያሉ በየስብሰባዎቹ ሲጠይቁ ሁለት እስርት ተቆጥሮል፡፡ ልጆቻችን ለምን ሌላ ክልል ውስጥ ገብተው ደም ያፈሳሉ!!! ለምን አብረን ከኖርናቸው፣ ተጋብተን ተዋልደን ከኖርንበት ህዝብ ጋር ታጋጩናላችሁ በማለት ያላሰለሰ ጥያቄ ማቅረቡን የኢትዩጵያ ህዝብ ያውቃል!!!

ምላስ አጥንት የላትም፣ አጥንት ግን ትሰብራለች!!! የሥነ-ልቦና መላሸቅ(Identity crisis) የጦር አበጋዞቹ ኢትዩጵያዊ ብሄርተኛነትን በማዋረድ የማንነት ጥያቄ በሥነ-ልቦና በማላሸቅ ኢትዩጵያዊ ባህል፣ኢትዩጵያዊ ታሪክ፣ብሄራዊ መዝሙር፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ፣ብሄራዊ ቅርስ፣ ብሄራዊ ቌንቌ ወዘተ ጥላሸት በመቀባት የራሳቸውን ዘውግ በትግራይ ህዝብ ስም በመነገድ ከሌላው ኢትዩጵያዊ ወገኑ ጋር የማጋጨት እኩይ ተግባር ይፈፅማሉ፡፡ ምላስ አጥንት የላትም፣ አጥንት ግን ትሰብራለች!!! ‹‹ባንዲራ ጨርቅ ነው!!!›› ‹‹የዓይን ቀለማቸው ካላማረን እናባርራቸዋለን!!!›› ‹‹የአክሱም ሃውልት፤ ለወላይታው ምኑ ነው!!!›› ‹‹እንኳን ከእናንተ ተወለድኩ!!!›› ‹‹ጣታችሁ ይቆረጣል!!!›› ‹‹የአስቸኳይ ግዜ ታውጆል፤ የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲወስድ አዝዤለሁ!!!›› ወዘተርፈ በማለት መለስ ዜናዊ ውርስና ቅርስ ሆኖ ጥሎልን ያለፈው የታሪክ ጠባሳ፤ የህወኃት ጦር አበጋዞች በኢትዩጵያውያን ዜጎች የመታወቂያ ወረቀት ላይ የማንነት ጥያቄን በማደል clan identification የዘር ሃረግ (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ ወዘተ) በማለት ዘውጌ ብሄርተኛነትን በመፈብረክና ኢትዩጵያዊ ብሄርተኛነትን በማዳከም ታሪክ የማይረሳው በደል ፈፅሞል፡፡

የህፃናት ጦር ሰራዊት (ማንጁስ) (child soldiers) የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄን በመገንባት ረገድና አዲስ የማንነት መታወቂያ የህፃናት ጦር ሰራዊት በመመሥረት አሊያም ጎልማሳ የጦር ሠራዊት በመገንባት ጥንታዊውን የቤተሰብ ምስረታና የቤተሰብ ፍቅር በማጥፋት ለጦር አበጋዞቹ ብቻ ታማኝ፣ታዛዥና ውጤታማ ሠራዊት  ለመገንባት አስችሎቸዋል፡፡ ጥንታዊው የህብረተሰብ ግንኙነቶችና  የቤተሰብ ፍቅር ማጣትና መቆረጥ ውጤት ነው፡፡(ማኪንሌይ፣2007፣ገፅ 58)Warlords can also use identity construction in order to create new identities with warrior names for child soldiers or adult soldiers who are recruited to their networks as if to throw off the ties of family  tradition. This reconstruction of identities is thought to make them less responsible for terrible conducts and more effective fighters, as their traditional social context is cut off (MacKinlay, 2007, p.58).The media has produced several stories about these young soldiers with new warrior names who often dress up in attires like wigs and gowns to further distance themselves from their former social identity and context: የጦር አበጋዞቹ ሕፃናቱን ዋርዲያና ዘበኛ በማድረግ ወርቃማ የትምህርት ቤት ግዜቸውን እንዲያጠፉ ማድረግና ህፃናቱ በጦርነት ሜዳ ውሎ ባዩት የስነልቦና ጠባሳና ለህሊናና አካለ ጎዶሎነት ተዳርገዋል፡፡ የጦር አበጋዞቹ ሕፃናቱንና ጎልማሶቹን ማንጁስ፣ቀይ እንባባ፣ቀይ እንቡጦች፣ ብረቱ ወጣት (The iron youth)፣ በሚል ስም ለአቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ህፃናትን ለወታደርነት መልምለዋል፡፡ ዛሬ በተለያዩ እስር ቤቶች መርማሪዎች ሆነው እስረኞችን በመግረፍና በማሰቃየት የሚገኙ የወያኔ በሽተኞች አገራችን አፍርታለች፡፡

የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ወታደራዊ ትርኢት (Military Parade) በተከታታይ በትግራይ ክልል ውስጥ ለአመታት መታየት በቀሪው የኢትዩጵያ ህዝብ ላይ ያሳደረው ጫና በሠራዊቱ ላይ የእኔነት ስሜት (Sense of Belongingness) አሳጥቶታል፡፡ የወያኔ ሠራዊት እንደ ጥንቱ ከህዝብ ጋር አብሮ ቆርሶ፣ አብሮ ጎርሶ፤ አብሮ አርሶ፣ አብሮ ዘርቶ ይባልለት የነበረ ወርቃማ ዘመንን በዘረኝነት አጨለመው፣ ቀሪውን ዜጋ ሁሉ የሁለተኛ ዜግነትና ብሄር ብሄረሰብ መታወቂያ እየሰጠ ይገዛ ጀመር፡፡ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት፤በወያኔ የጦር አበጋዞች ማለትም የጦር መኮንኖች እዝና ቁጥጥር ስር፣ ተወጥሮና ተጠርንፎ  (Command and Control)  ሲሰቃይ አመታት ተቆጥሮል፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፀበል እየረጨ፣ የልማታዊ መንግስት ቄጤማ እየነሰነሰ፣ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሸማ በየአምስቱ አመት እየቆረጠ ከሰማይ ደመና፣ ከምድር ዉሃ አጠፋ 8.4 ሚሊዩን ህዝብ ለረሃብ ተዳርጎል፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት በህገ-መንግስት ስም፣ በዴሞክራሲ ስም፣ በግለስብና በህዝብ ላይ ፍጹማዊ አገዛዝ (Totalitarian) በመዘርጋት ለሃያ ስድስት አመታት በግፍ ገዝተዋል፡፡ የወያኔን ግፍ ያዩ የትግራይ ወጣቶች ከሌሎች ኢትዩጵያዊ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን ቆመዉ  የህወሃት ዘረኛ የጦር አበጋዞች መንግስት ጠቅላይ ጦር ሠፈር ለማጋየት ታጥቀው ሊነሱ ይገባል፡፡

የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት ከትግል ጎዶቹ በመማር በህቡዕ እንደ ‹‹ዴሞክራቲክ ጋርድ›› በመደራጀት ህዝባዊውን ትግል መቀላቀል ታሪካዊ ሃላፊነት አለባችሁ፡፡ የኢትዩጵያ መከላከያ ሠራዊት ከነፃነት ኃይሎች ጋር መቀላቀልና ህዝባዊውን ትግል በማጎልበት የህወኃት መንግሥት መጣል ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት፡፡የወያኔ የጦር አበጋዞች በዘር ላይ የተመሠረተ አገዛዝ ሃያ ስድስት አመታት አስቆጠረ፤ ጥንት የኢትዩጵያ አርበኞች ጣልያንን የተዋጉት በሸዋ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወለጋ፣ በሐረር፣ በሲዳሞ፣ በአርሲ፣ በትግራይ ወዘተ ተራሮችና ሸንተረሮች፣ ደጋና ቆላ፣ ቆጥኝና አለት፣ ወንዝና ጅረት፣በርሃና አሸዋ የጎበዝ አለቃቸውን እየመረጡ አፈር ቀምሰው፣ባሩድ ልሰው፣ መቅመቆ በልተው ኮሶ ግተው፣ የጠላት ጦርን አንዱን ለአስር!!!፤የጠላት ጦርን አስሩን ለአንድ!!! ገጥመው ነው ሃገርና ህዝብ ነፃ ያወጡት፡፡ የሃገሪቱ ልጆች የጦርነት አካዳሚ ሣይንስ ኮሌጆች ተመርቀው ባሉበት እናት ሃገር ሳይንሳዊ የጦር ስትራቴጂ በመንደፍ በህዝብና በሃገርን ነፃ ማውጣት ይቻላል፡፡ ሃገራችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የግንቦት ሰባት፣ የኦጋዴን ብሔራዊ አርነት ግንባር፣የኦሮሞ፣ የጋምቤላ፣ የቤኒሻንጉል የደፈጣ ተዋጊዎች በህብረት ተጋድሎቸውን በማጠናከር የህወኃት አንባገነነዛዝን መስወገድ ይቻላል፡፡ ‹‹አንዱ ለሁሉም፣ሁሉም ለአንዱ››  የአንዱ ጥቃት የሁሉም ጥቃት፣ ብለን የደፈጣ ተዋጊዎች እንቅስቃሴ በመላ ሃገሪቱ ካቀጣጠልን ነፃነታችን በእጃችን መዳፍ ላይ ናት፡፡ ህዝቡ የሚሻው የመሳሪያ ድጋፍ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ከጦርነት አካዳሚ ሣይንስ ኮሌጆች የተመረቁ ጠበብት ህዝባዊውን የሽምቅ ውጊያ ትክቲክና ስትራቴጂ ለህዝብ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ካለበለዛ በማይሆን የጦር ስትራቴጅ እየተመራን ለወያኔ የጦር አበጋዞች እንቁላል እየሸጥን መኖር ግድ ይለናል፡፡ እንደ ሰው፣ ከሃገር እየተሰደድን፣ከውቅያኖስ እየሰመጥን፣ በሰይፍ እየተቀላን፣ ወንዶቻችንና ሴቶቻችን እየተደፈሩ፣ ከመኖር ዛሬውኑ በክብር መሞት ይመረጣል፡፡ ለሚታገሉት አርበኞች አስፈላጊውን ሽልማትና ቤተሰቦቻቸውን የሚታደግ ህብረ ብሄራዊ ድርጅት በማቆቆም አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነት አለብን፡፡

የወያኔን ኢኮኖሚ ኢምፓየር በስውር የሚያደናቅፍ፡-ሃገር አቀፍ ድርጅት ይቆቆም፡- የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ውጪ በሚኖሩ ኢትዩጵያውያን ወደ ሃገር ቤት የተላከ የሃዋላ ገቢ በ2010/11 (1.4ቢሊዩን ዶላር)፣ 2011/12 (2.4ቢሊዩን ዶላር)፣ 2012/13 (2.9ቢሊዩን ዶላር)፣ 2013/14 (3.0ቢሊዩን ዶላር)፣ 2014/15 (3.7ቢሊዩን ዶላር)፣ 2015/16 (4ቢሊዩን ዶላር)፣ 2016/17 (4.6ቢሊዩን ዶላር) ይገኛል ተብሎ ቢታሰቡም 3.7 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ብቻ ተገኝቶል ብለዋል፡፡ በ2009 ዓ/ም እንደ ዓለም ባንክ ግምት ወደ ኢትዩጵያ የተላከው የገንዘብ መጠን ከ624 ሚሊዩን ዶላር ሲሆን ገቢው ማሽቆልቆሉን ተገልፆል፡፡ ከዲያስፖራው 78 በመቶ ያህሉ መደበኛ ባልሆኑ የሐዋላ መላኪያዎች እንደሚጠቀሙ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ከመንግሥት ጋር ተቀራራቢ የሆነ 3.7 ቢሊዩን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቆል፡፡ በ2009 ዓ/ም ከውጪ ንግድ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ 2.9 ቢሊዩን ዶላር እንደሆነ ሲታወቅ በአንፃሩ ከሐዋላ የተገኘው የውች ምንዛሪ ገቢ ግን 4 ቢሊዩን ዶላር መሆኑ ታውቆል፡፡ ከባህር ማዶ ሃገራት ዜጎቻችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚላክ ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓውንድ ወዘተ በህወኃት ባንኮች እንዳይገባ የማድረግ ዘዴን ማጠናከር የወያኔን የጥይት መግዣ በማገድ ከሥልጣኑ መንቀል አንደኛ ዘዴ በመሆኑ ማስተባበሩ ይቀጥል፡፡ በዚህም የሚያኮራ ሥራችሁ ዘሪሁን ተስፋዬና ፅጉአዝ ብርሃኑ ወደ ሀገርቤት የሚላከውን ዶላር በተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም ዶላሩን ውጪ ላሉ ሰጥቶ የብሩን በተዘዋዋሪ ሃገር ውስጥ ላሉ ዘመዶች በመስጠት ለወያኔ እንዳይደርስ ማድረግ ተችሎል፡፡ በዚህም ምክንያት በሃገሪቱ የጥቁር ገበያ የአንድ የአሜሪካን ዶላር 31 ብር መመንዘር ተጀምሮል፡፡ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ተባብሶል፣ የውጪ ንግድ ተንኮታኩቶል፣የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተባብሶል፣ በህወኃት ሹማምንቶች ከሃገሪቱ ዶላር የማሸሽ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሎል፣ የመልካም አስተዳደርና የሙስና/ የሌብነት ሥርዓት በወያኔ ተንሰራፍቶል፡፡ በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ህዝባዊ የአምስት ቀናት ከሥራና ከቤት ያለመውጣት አድማ የኢኮኖሚ ምርቶች ግብይይትና የሸቀጣ ሸቀጥ ልውውጥ ኪሳራው ገና አልተሰላም ይህንን ተከትሎ የትራንስፖርት መቆረጥና የመኪናዎች መሰባበርና መቃጠል ምጣኔ ኃብቱን አንኮታኩቶታል፡፡ ባንኮች ተዘግተው በመዋላቸው በገንዘብ ዝውውሩ ዝግምተኛ ሆኖል፡፡ በኢትዩጵያ ይህን ህዝባዊ የኢኮኖሚ አሻጥር ለማቀጣጠል፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሞባይል ስልክ ለአንድ ቀን ባለመጠቀም ያሳዩት ፈር ቀዳጅ የትግል ስልት፤ እንደ አረብ ስፕሪንግ ኢንተረ ኔት ድረገፆችና፣ ማህበራዊ ድረ ገፅ ፈር ቀዳጅ የትግል ስልት በመሆን በታሪክ ይታወሳል፡፡ በሁሉም ኢትዬጵያዊያን ይሄ ትግል ለወራቶች ቢቀጥል የገዥው መንግስት ከቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ለሰለላ ተግባሩ በምንከፍለው ገንዘብ ስቃያችንና እስራችንን ስላበዛን በኢትዩቴሌኮምን የምትታለበውን ላም ወተት ለአንድ ወር ለማንጠፍ በስልክ ያለመጠቀምና የሞባይል ካርድ አለመግዛት አድማ እንዲደረግ ለአስተባባሪዎቹ እናሳስባለን፡፡ ኢትዩጵያዊ ድረገፆችና፣ ማህበራዊ ድረ ገፅ የኢኮኖሚ ዐምድ ቢኖራቸው ህብረተሰባችን ስለ ሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ይዞታ የማንበብና በመወያየት ባህሉን ሊያዳብሩ ይችላሉ፡፡  የወያኔን ኢኮኖሚ እስካልደፈጠጥን የፖለቲካውን በትረ-ሥልጣን መጨበጥ የህልም እንጀራ ይሆናል፡፡ ኢኮኖሚውን የተቆጣጠረ ፖለቲካውን ይቆጣጠራል የሚባለው ለዚህ ነው፡፡

ቻይና ኮምኒስት ፓርቲና ከህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ጋር የኢሳት ሳተላይት ቲቪና ሬዲዩ፣ የሱማሌ፣ የጋምቤላ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ ወዘተ  ህዝብ ላይ የደረሰውን እልቂት ዜናን ለኢትዮጵያ ህዝብ  በማጋለጥ የኢሣት መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ያበረከተውን ታላቅ አስተዎፆኦ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል፡፡ ኢሳትን ለመዝጋት የቻይና ህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት በመቃወምና በኢትዩጵያ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እነ ዶክተር መራራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ!!! እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እስክንድር ነጋ፣አንዱአለም አራጌ ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ!!! እነ ብርጌደር ጀነራል ተፈራ ማሞ፤ብርጌደር ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ እማዋይሽ አለሙ ወ/ሚካኤል፣ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ተፅዕኖ ለማድረግ  ኢትዩቴሌኮምን ያለመጠቀም አድማ በተግባር እናሳይ፡፡ በዚህም የኢትዩቴሌኮምን የገንዘብ s~” uመዝጋት የኢትዩጵያን የትግል ሥልት ለዓለም ዐቀፍ ህብረተሰብ ዘንድ በማስመዝገብ የህወኃት ኢኮኖሚ እናንኮታኩት፡፡ ይህንንም የህብረት የትግል ጥሪ የኢትዩጵዊያን ድረ-ገፆች፣የኢትዩጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን (ኢሣት)፣ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ፣ ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች አስተባባሪ፣ የአማራ ወጣቶች አስተባባሪ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር፣ ግንቦት ሰባት፣ በማህበራዊ ድረ,ገፆች አክቲቪስቶች (በፋስቡክ፣ ቲውተር፣ ወዘተ) በልዩ ልዩ መገኛኛ አውታሮች ወዘተ በኢትዩጵያ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱና በህወኃት እስርቤቶች ውስጥ የሚደረጉ ኢሰባዓዊ ግርፋትና የወሲብ ጥቃትን ለዓለም ህብረተሰብ ለማጋለጥ የሚደረግ ህዝባዊ ጥሪ እንዲደረግ የማስተባበርና የአድማውን ቀን የመቁረጥ  አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!

በወያኔ እስር ቤቶች ውስጥ ኢስብዓዊ ግርፋትና ማሰቃየት ይቁም!!!

በወያኔ እስር ቤቶች ውስጥ ኢስብአዊ የወሲብ ጥቃት ይቁም!!!

የወያኔ እስር ቤቶች በዓለም ዓቀፍ ስብአዊ መብት ኮሚሽን ይጎብኙ!!!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.