የኬንያን ድንበር ያለ ህጋዊ ሁኔታ አቋርጠው ገብተዋል የተባሉ 13 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

 እንደ መረጃዎች ገለጻ፣ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በቁጥጥር ስር የዋሉት ረቡዕ ዕለት ሲሆን፣ እስከ አሁን ድረስም በፖሊስ እጅ ይገኛሉ፡፡ በቀጣይ ቀናትም ፍርድ ቤት ቀርበው የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደሚተላለፍባቸው ከወዲሁ ተነግሯል፡፡ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ በመንገድ ላይ ሳሉ ሲሆን፣ ኬንያን እንደ መሸጋገሪያ ለማቋረጥ ሲሞክሩም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ስደተኞቹ በጠቅላላ ወንዶች ሲሆኑ፣ በፖሊስ ሊያዙ የቻሉትም በአንድ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ሳለ ነው፡፡ ከኬንያ ወደ ታንዛንያ ለመሸጋገር በአንድ ቤት ተቀምጠው ሳለ የተያዙት ስደተኞቹ፣ ድንገት በተደረገ ፍተሸ በፖሊስ እጅ ሊወድቁ መቻላቸውም ተነግሯል፡፡ ፖሊስ እንደገለጸው፣ ስደተኞቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ ደላሎችን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ግን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውሉ አልቻሉም፡፡

ስደተኞቹ የሀገሪቱ ቋንቋ የሆነውን ሲዋሂሊ ጨምሮ እንግሊዝኛ መስማትም ሆነ መናገር የማይችሉ በመሆናቸው፣ ከስደተኞቹ ጋር ለመግባባባት አደጋች መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ሆኖም አስተርጓሚ ተፈልጎ በአስተርጓሚ እየተነገጋሩ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ስራ አጥነት እና የፖለቲካ ሁኔታ ሽሽት ሀገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በሚደረገው ጉዞም ብዙዎች መንገድ ላይ የቀሩ ሲሆን፣ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እስር ቤቶች የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥርም ከፍተኛ ነው፡፡

ቢቢን ዜና

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.