ህዋህት መሬታችንን ለመቀማት፣ ለምድ ደረበች የቅማንትነት – ልያ ፋንታ

የኢትዮጵያን እንደ ሀገር የነበራትን ገናናነት ለማዳከም በክልል፣በዞን በመከፋፈል አንዱ ከአንዱ ጋር እንዳይግባባ በቆንቋ በመለያየት ነገር ግን ታላቋን ትግራይ በስፋት ለመገንባት ፣ ኩናማውንም ፣አማራውንም ፣ኢሮቡን የግድ ትግርኛ ብቻ ተናገር እያሉ መደፈቅ የህዋህት በአደባባይ የወጣ ጽሀይ የሞቀው ሀገርን የማፍረሰ የክህደት ስራ ነው።

ተወልጄ ባደረግኩበት በርካታ የቅማንት ማህበረሰብ ባለበት አካባቢ ቅማንትኛን ለመግባቢያ ሲጠቀሙበት አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ቅማንቱም አማራውም በአማርኛ ይግባባሉ፣ በትዳር የተሳሰራሉ አብረው መከራ እና ደስታን በጋራ ያለ ልዩነት ይካፈላሉ።

በአሁኑ ወቅቀት መቀሌ እና ሽሬ ጽ/ ቤቶች ከፍቶ ህዋህት ትግራይ ከአማራ ህዝብ ይልቅ የትግራይ ህዝብ ቅማንትን የወዳል፣ በእናንተ ናፍቆት ከስቶ መንምኗል የሚል ወይም ጎንደርን ትክሻዋ ላይ በልቷታል እና እኔ እጄ ረዥሟ ትግራይ ጎረቤቷ ልከክላት እንደምታ ያለው ልብ ወለድ የፈጠራ ድረሰት ደርሶ በማህበረሰቡ ዘንድ በምግባራቼው የተጠሉ እንደ ነጋ ጌጡ፣ እንደ ዶክተር ሲሳይ ይፍሩ አይነት ሆዳሞችን ቀጥሮ ሁለቱን በፍቅር የኖሩ ማህበረሰብ አባላት ለማጨፋጨፍ ህዋህት ዝግጂቱን አጠናቅቋል። በርካታ አስተዋይ የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጆች እኛ ለብቻችን በዞን መከለል አንፈልግም በማለት ላይ ናቼው።የሚቀጥለው እርምጃ እንደ ወልቃይት ወገኖቻችን ሁሉ እጂ እና እግራቼው በንሰለት እየታሰረ በግፍ መገደል ነው። ጎንደርን በሶስት ዞን የመክፈል አላማ ህዋህት ክፍለ ሀገሩን አንዴ ዘግኖ ከመጉረስ ሶስት ጊዜ መጥኖ ለመጉረስ ያዘጋጄው ስልት ነው።

በመጭው መስከረም ወር የሚካሄደው ሪፍረንደም አስፈጻሚ 170 ካድሬዎች በሙሉ የህዋህት ምልምሎች ናቼው።
ህዋህት ሆይ! ጎንደርን ለመጉረስ የቅማንትነት በርኖስ መልበሰሽን መላው ጎንደሬ አውቋል። አማራ ከቅማንት ጋር አይጋጭም በከንቱ አትድከሚ እልሻለሁ።
ልያ ፋንታ
ከጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ( ጎህ) ዲሲ ቻፕተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.