ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያውያን ልብ ላይ የነገሰ የለውጥ ሐዋርያ ነው – ንጉስ ካሌብ

የቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” የሚለው ዘፈኑ የአልበም ምርቃት በጊዮን ሆቴል ዝግጅቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በፀጥታ ኃይሎች ፕሮግራሙ እንዳይካሄድ ታግዷል። “መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ይሆናል” እያለ ከተማዋን በመፈክርና በሙዚቃ የሚያደነቁረን ወያኔ ቴዲ ኢትዮጵያዊነትን ከአፍቃሪዎቹ ጋር ሆኖ ለማወደስ ሲነሳ መከልከል ወያኔ ዛሬም በሲኦል የሚኖር የጥላቻ እስረኛ መሆኑን ያሳያል። ወያኔ በጥላቻ ሸለቆ ውስጥ ሆኖ የኢትዮጵያን ከፍታ ለመተንበይ ሞራልም ሆነ ስነምግባር የለውም፣ አሁንም ፀረ አንድነትና ፀረ ኢትዮጵያዊ ነውና። ይበልጥ ይህን የፍቅር ብላቴና በጠሉት ቁጥር ይበልጥ ቴዲን እንወደዋለን።

ቴዲ አፍሮ ለፍቅር ተወልዶ፣ በፍቅር ያደገ ፍቅርን የሚሰብክ የነፃነት ነብይ ነው። ወያኔ ያረከሳትን አገር በጥበብ የቀደሰ፣ ወያኔ ጨርቅ ያላትን ባንዲራ ከወርቅ በላይ የወደደ፣ ዘረኝነትን የጠላ፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ ፍትህን፣ ነፃነትንና ፍትህን በስራዎቹ ሁሉ የሚሰብክ የለውጥ ሃዋርያ በመሆነ ወያኔ ቴዲን አምርሮ ይጠላዋል። የአንድነት ነብይ የሆነው ቴዲም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ላይ የነገሰ የፍቅር ሐዋርያ ሆኖ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አድርጎ በማወደስ ወደ ፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.