ሰበር መረጃ… በወልቃይት  ጸለምትና ሽሬ  ኣውራጃዎች የኮሌሯ  ወረርሽን  እንደ  እሳት  ሰደድ ተቀጣጥሏል – ከኣስገደ  ገብረስላሴ

መንግስት ግን   በሽታው  ኮሌሯ ብሎ የጠሩ ዜጎች  እንደ ወንጀሎኞች  ይመለከታቸዎል  !!!
———————————————————

የኮሌሯው ወረርሽን  በወልቃይት  ሕሞራ በኣዲ ጎሹ  በመዘጋ  በጸለምት  ቆላማ ወረዳዎች ፣ በባድመ ፣በሸራሮ ፣ በሰዬምት ኣድያቦ ፣ በእስገደ ፣ በጽንብላ ፣ በታሕታይ  ቆራሮ ፣ በዛና ፣ በመደባይ ፣ በሰለክለካ ፣ወረዳዎች እንዲሁም የሽሬ  ኣውራጃ  ኩቷ ገጠም  የሆኑ  የኣክሱም ኣውራጃ  ወረዳዎች  በሽታው  ተስፋፍታል ።

በኮሌራው  የተለከፉ  ወገኖች  በጣም በርከት ያሉ  የሞቱ ሲሆን  ፣ኣብዛኞቹ  ህመምተኞች  ግን  በጤና  ጣቢያውች  የተሰጣቸው  ህቡእ ማረፍያ  ቦታ   የተመቻቸ  ማረፍያ የላቸውም ፣ በሽተኞች  በተሰበሰቡበት  ዝቅተኛ  ነርሶች  ካልሆኑ  ከፍተኛ  ሃኪሞች  ኣታዩም  ።
፡ በዚሁ በወረርሽኑ  የተጠቁ ወረዳዎች  ንጹህ  የሚጠጣ ውሃ  የሚባል  የለም   ። ኣርሶ ኣደሩ ፣ወርቂ ለቃሚው  ከወንዝ ጎርፍ  ያመጣለት  የደፈረሰ ውሃ  ነው  የሚጋተው  ያለው  ። እነዛ በዬመንደሩ  የውሃ  ፓንፕ በመትከል  የህዝብ የንጹህ  የውሃ  ኣገልግሎት  ሰጥተናል  እያሉ  የሚጎረኑባቸው  የውሃ  ጉድጓዶች     ጥቂቶች  ካልሆኑ  በስተቀር፡  ኣብዛኞቹ  ሳይሰሩ  የጠፉ  ናቸው ።
ከላይ  የዘረዘርኩት  መረጃ  የመንግስት ይሁኑ  የህወሓት ኢህኣደግ  ፓርቲዎች ፣ተለብዝን ፣ሬድዮ ጣቢያዎች ፣ ኤፍ  ኤሞች ፣ ጋዜጦች  እስከኣሁን  ትንፍሽ  ኣላሉም ። የግል ፕሬሶቹም  ምንም  የተነፈሱት  የለም  ።
ታድያ  ይህ  ህዝብ  ማን  ይድረስለት ?????
ከኣስገደ  ገብረስላሴ  ሰለክለካ   ፣
29  / 12  / 2009

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.