የአባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን እስኪሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል:- ሸንቁጥ አየለ

  ወያኔ የሸረበዉ የቅማንት-አማራ ግዛት የማካለል ሂደት ሁሉ የተለመደ ወንጀል ነዉ
========================
ወያኔ የሰራዉ ህገ መንግስት ፈራሽ ነዉ::ወያኔ የከለለዉ ክልል ፈራሽ ነዉ::የአማራ: የኦሮሞ: የደቡብ: የትግሬ የእንቶኔ ብሎ ወያኔ የከለለዉ ክልል ሁሉ ፈራሽ ነዉ::ህገወጥ እና ወንጀል ነዉና::አሁንም ወያኔ የቅማንት መሬት ይሄ : የአማራ መሬት ያኛዉ ብሎ የሚከልልለዉ አከላለል ሁሉ ፈራሽ ነዉ::ህገ ወጥ ነዉና::ወያኔ እራሱ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ የዉስጥ ቅኝ ገዥ ወራሪ ሀይል ነዉ::የዉስጥ ወራሪ የሰራዉ ህገወጥ የወንጀል ስራ ሁሉ ይፈርሳል::ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ነች::አራት ነጥብ::

በወያኔ የቅማንት – አማራ የማካ…ለል ምርጫ ዉስጥ ለመግባት ዳር ዳር የምትሉ ሁሉ ጥንቃቄ አድርጉ::ወያኔ ሆን ብሎ አማራዉን እና ቅማንቱን ለማጫረስ ብሎም እርሱ ገላጋይ ሆኖ ለመግባት ተዘጋጅቷል:: ወያኔ የሚያደርገዉ ምንም አይነት ምርጫ ህገወጥ ነዉ::ወያኔ እንደሚታወቀዉ በመቶ ድምጽ ህዝብ የመረጠዉን ነገር ዉድቅ አድርጎ የራሱን ሀሳብ ተመርጧል ብሎ እንደሚያጸድቅ ይታወቃል::ከእንደዚህ አይነቱ አዉሬ ጋር ስለምርጫ ማዉራት ወንጀልም ነዉርም ነዉ::አሁን ወያኔ እና የብአዴን አሽከሮቹ ስለ ቅማት አማራ ግዛት ምርጫ ቢያወሩም ቀድመዉ ግዛቱን ከልለዉታል::በመሆኑም የወያኔን አጀንዳ ለማጽደቅ ወደ ምርጫ መግባት አያስፈልግም::

ወያኔ ዛሬ በቅማንት እና በአማራ መሃከል እየሰራዉ ያለዉን አሰራ ሸኖ ላይ እና ፍቼ ላይ በአማራ እና በኦሮሞ መሃከል ከዛሬ ሀያ ስድስት አመት በፊት ተመሳሳይ ደባ ሰርቶ በከፊል ተሳክቶለታል::ሆኖም የሸዋ ልቡ እስከ ምፅዓት እንኳን ቢሆን የአባቶቹን ሀገር ኢትዮጵያን እጁ ሳያደርግ እንደማይተኛ ወያኔም ያዉቃል::

በመሆኑም ወያኔ የሰራዉ ደባ ሁሉ ከስሩ ተነቅሎ ይጣላል::አንዳች ስር እንኳን የለዉም::ጎንደርም የአባቶቹን ሀገር መላዉ ኢትዮጵያን ከወያኔ ይረከባል እንጅ የወያኔን የቀበሌ አከላለል ተቀብሎ አያጸድቅም::ስለዚህ የወያኔ ጫማ ጠራጊዎች ሁሉ ተስፋችሁን ቁረጡ::የገጠማችሁት ጠላት ለዘመናት የጠላት አከርካሪ ማድቀቅ የሚያዉቅ ህዝብ ነዉ::

ወያኔ በተመሳሳይ በባሌ ዉስጥ በኦሮሞ እና በሶማሌ መሃከል የሚጫወትበት ካርታ ይሄዉ ስልት ማለትም ያኛዉ ቁራጭ መሬት የዚያኛዉ : ይሄኛዉ ቁራጭ መሬት የዚህኛዉ በማለት ነዉ::
የአባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን እስኪሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል::ወያኔ የስራዉ ሁሉ ይናዳን::ከስሩ ተነቅሎም ይጣላል::

እዉነተኛ ተቃዋሚዎች ካላችሁ ግን በወያኔ የቅማንት አማራ የካርታ ጨዋታ ዉስጥ የሚሳተፉትን እና ህዝብን ለማጫረስ የሚንቀሳቀሱትን ቢያንስ አንድ ሁለቱን እንደሚሆን እንደሚሆን ለማድረግ ብሎም አጠቃላይ የወያኔን ደባ ለማክሸፍ ተንቀሳቀሱ:: ከሁሉም በላይ ህዝቡን ለቀጣይ መራራ ትግል የስነልቦና ዝግጅት እንዲያደርግ ቅስቀሳ አድርጉ::ወያኔ የሚወድቀዉ በብዙ ቅንጅታዊ ጥቃት ስር ሲገባ ነዉና የተቀናጀዉን የጥቃት ስልት አስሉት::መፍትሄዉ ህዝባዊ አመጽ ብቻ እንዳልሆነ ሳትረዱት የቀራችሁ አልመሰለኝም::

ሚስጥር ሊያስጠብቃችሁ በሚያስችል መልክ ወደ መሬት ለመዉረድ ተንቀሳቀሱ::ወደ መሬት::

ወያኔን በደንብ ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል:: ወያኔ እንደሚመኘዉ ይሄ ቀበሌ የዚህ ያ ቀበሌ የዚያ በማለት ህዝባችንን ደም በማቃባት የህዝቡን መሰረት ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ መቀመቅ የመክተት ስራዉን የጀመረዉ ዛሬ አይደለም::

ይሄን ስራ ብዙ ቦታ ተግብሮታል::ጊዜዉ ሲደርስ ግን አንድ እንኳን የወያኔ አሻራ እንዳይቀር ተደርጎ ከኢትዮጵያ ምድር ይሻራል::እናም ትልቁን የወያኔን ደባ ሳትረሱ ወያኔን ለመንቀል ህዝቡን በማዘጋጀት ላይ አተኩሩ::ህዝብ እና ህዝብ እንዳይፋጅም የቅማንትና የአማራ ህዝብ ወንድማማችነትን ከማስተማር አትዘናጉ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.