የድንበር አጥር ሰፋሪው የተከዜ ማዶው ፍሽስት ቡድን የማያቆም የመሬት ዘረፍ–(ሰሎሞን ይመኑ)

#ጠገዴ ወ #ፀገዴ
#ሌላኛው ወልቃይት ሌላ ግጭት ሌላ እልቂት
 በወያኔ ህገ አራዊት አንቀጽ 46(2) መሰረት ክልሎች የሚዋቀሩት በህዝብ አሰፋፈር፤ቋንቋ፤ ማንነትና ፈቃድ ላይ በመመስረት እንደሆነ ያስረዳል ነገር ግን የንጹሃንን ደም በማፍሰስ ለምትመሰረተዋ የደም መሬት አሁንም ሌላ ችግር ሌላ ስጋት የያዘ አነጋጋሪ የሆን የመሬት ወረራ በአማራ ህዝብ ላይ መፈጸሙን ጭራሽ ሳያፍሩ በግልጽ ስለስምምነቱ በይፋ ነገሩን፡፡
 አንቀጽ 46 እንደሚያወራው ከሆነ ጠገዴ በሰሜን ጎንደር አስተዳደር ስር የቆየ ወረዳ ሲሆን የሚተዳደረውም በአማራ ክልል ነው፡፡ በወረዳውም በርሃ ብ ምክንያት ተሰደው የመጡ በጣም ትንሽ የትግራይ ተወላጆች በሰፈራ ምክንያት ሲመጡ የአካባቢው ህብረተሰብ ቤት ለእንግዳ ብሎ ሲቀበላቸው ትንሽ ቆይተው ጠገዴን ፀገዴ አሉትና በትግረኛ በትግራይ ክልል ሊጠቃለል ይገባል የሚል የወያኔ ሴራ ተጀመረ፡፡ ክልሎች የሚዋቀሩት በህዝብ አሰፋፈር፤ቋንቋ፤ ማንነትና ፈቃድ ላይ በመመስረት ከሆነ የወረዳው የስራ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን የህዝቡ አሰፋፈርም ከሌሎች አማራ ወገኖቹ ጋር ነው ማንነቱም እንደዛው የህዝቡም ፍላጎት 100 ፐርሰንት ከአማራዊ ማንነት የወጣ አደለም፡፡ በሰፈራ የመጡ የትግረኛ ተናጋሪ ጥቂት ሰዎች ያላቸው መብትም ሁለት ነው፡፡ አንደኛው የራሳቸው ቋንቋና ባህል ተከብሮላቸው እስካሁን ሲኖሩ እንደነበረው ከህዝቡ ጋር ተግባብቶ መኖር ሲሆን አይ አይሆንም ካሉ ደግሞ ያፈሩትን ሃብት ይዘው ወደ መጡበት መመለስ ነበር ሁለተኛው አማራጭ ነገር ግን ቅልብ የአማራ ሆድ አደሮች የብ አዴን ሰዎች ምን ተስማሙ ወረዳዋን ግማሹን ለም መሬት ለትግራይ ክልል መስጠት በሚል ሲሆን ይህም ከ አንቀጽ 46 ሃሳብና ዓላማ ውጭ ለትግራይ ክልል ሌላ ገጸ በረከት ቀርቦለታል፡፡
 በጣም የሚገርመው በደግነት የተራበን የተቀበለው አብዛኛው የአማራ ህዝብ በደግነት ከርስቱ እንዲነቀል ዛሬም ተስማሙበት ያውም ህውሃት ከ ህውሃት ጋር የአማራን ለም መሬቶች ለመንጠቅ፡፡
የክልሎችን ወሰን በተመለከተም በሁለቱ ክልሎች ስምምነት መፈጸም እንዳለበትና የሚመለከታቸው ክልሎችም መስማማት ካልቻሉ የፌድሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት አመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ በህገ አራዊቱ አንቀጽ 48(1 እና2) ላይ በግልጽ ያለ ሲሆን በወቅቱም ህገ አራዊቱ ሲጸድቅ ሁለቱም ክልሎች ተስማምተው ክለላውም አልቆ በሚኖረው ህዝብ ላይ ዛሬ የተከዜው ማዶ ተስፋፊ ማፌያ ቡድን የመሬት ዘረፍውን ሲገፍበት አዲስ ድንበር መመስረት ጀመረ፡፡ ይህ ማለት ችግር ቢኖር ኑሮ ህገ አራዊቱ ከጸደቀ ከ 1987 ጀምሮ ባሉት 2 አመታት ውስጥ ስለ ክልሎች ድምበር አለመስማማት የፌድሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ይሰጥ ነበር፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ምንም የድንበር ጥያቄ ስላልነበረ በሰላም ካለቀ ያሁኑ አዲስ ስምምነት ለምን ተፈጠረ ብለን ብንጠይቅ መልሱ አንድና አንድ ነው ያም አማራውን ከርስቱ ከቀየው የመንቀል ስልታዊ ሴራ ነው፡፡
የአማራ ክልል ለም የእርሻ መሬቶችን በመንጠቅ የደም መሬቷን የተከዜ ማዶ ማፌያዎችን ምድር ለማስፍፍት በሚደረገው እሽቅድድም የአማራው የህውሃት ቡድን ከትግራዩ የህውሃት ቡድን ጋር ተስማማሁ ይለናል፡፡ ይህ ማለት ለም የእርሻ መሬቶችን ከአማራ ክልል ለመንጠቅ ህዋሃት ከህዋሃት ጋር አዲስ የድምበር ልገሳ ለትግራዩ ክልል በቅልብ የብአዴን ወኪሎች ሌላ ገጽ በረከት ቀርቦላቸዋል ይህም ሌላኛው ወልቃይት ሌላኛው የደም ድንበር ነው፡፡ ወያኔም ገና ቀበሌ ከቀበሌ ድንበር ሊሰራልን ይችላልና በቃህ ልንለው ይገባል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.