ግልጽ ደብዳቤ! – ለ-ብአዴን አባላትና ደጋፊዎች፣ ለ -አቶ ደመቀ መኮንን «ኢፌዴሪ ም/ጠ/ሚኒስቴር»፣ ለ -አቶ ደጉ አንዳርጋቸው «የዐማራ ክልል» ፕሬዚዳንት፣

ቅጽ ፩ ቁጥር ፱ ሰኞ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፪ሺ፱ዓ.ም.

ለ -ብአዴን አባላትና ደጋፊዎች፣l

ለ -አቶ ደመቀ መኮንን «ኢፌዴሪ ም/ጠ/ሚኒስቴር»፣

ለ -አቶ ደጉ አንዳርጋቸው «የዐማራ ክልል» ፕሬዚዳንት፣

ጉዳዩ፦የቅማንትን ከጎንደር ዐማራ የመገንጠል እንቅስቃሴ በጎንደር በአጠቃላዩም በዐማራው ሕዝብ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ማሳየት ይመለከታል፣

ይህን ጦማር የምንልክላችሁ፣ በራሳችሁ ነፃ ፍላጎት መንቀሳቀስ የማትችሉ መሆኑን ጠፍቶን ወይም አጥተነው አይደለም። «ምንም ብቀጥን ጠጅ ነኝ»፣ እንደሚሉት አባቶቻችን፣ የአባቶቻችን ልጆች ናችሁና! « ዳመናው ሲዳምን ይወረዛል ገደል፣ ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል፤» የሚለው የቆየ አባባል በእሳቤአችሁ ውስጥ ይኖራል ብለን ስለገመትን ነው። የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ወገናችን ላይ እያደረሰ ያለው ሁለገብ የዘር ጥቃት ገደቡን አልፎ እየፈሰሰ መሆኑን፣ ከእኛ ይልቅ፣ እናንተ በቅርበት መገኘት ብቻ ሳይሆን፣ የግፉ አስተናጋጆች ስለሆናችሁ ለእናንተ እንዲህ ነው ብሎ ማለት «ለቀባሪ ማርዳት» ይሆንብናል። በዘመነ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ፣ በዐማራው ላይ፣ታሪክና ትውልድ ይቅር የማይሉት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ድርጊት ተፈጽሟል። ባለፉት 26 ዓመታት የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከአምስት ሚሊዮን(5,000,000) በላይ ዐማራ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ አድርጓል። ይህን ግፍ የታዘቡ የብአዴን አባላት «ብአዴን ከወያኔ ሞግዚትነት ራሱን ነፃ ያውጣ፤ የአመራሩን ቁልፍ ቦታዎች የያዙት ትግሬዎቹ ሕላዊ ዮሴፍ፣ ካሣ ተክለብርሃን፣ ታደሰ ጥንቅሹ፣ ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ከብአዴን ይነጠሉ» የሚሉ ድምፆችን በተለያዩ ጊዚያቶችና አጋጣሚዎች ማሰማታቸውን ሰምተናል። ይህ ድምፅ ተደጋግሞ ከመነገር ባሻገር፣ አሻፈረኝ፣ እኛ የጀግኖቹና የአርበኞቹ ልጆች ለፈሪዎቹና ለባንዳዎቹ ልጆች ለአገርና ለወገን ጠላቶች አንገዛም ወደሚል መሸጋገር እንዳለበት ልናሳስባችሁ እንወዳለን።

ከሁሉም በላይ የዘራችን ጠላት ሆኖ የቆመው የትግሬ-ወያኔ ፍጡሮችና የእርሱ ዓላማ አስፈጻሚ ሆነው ፣ ኩሩውንና ጀግናውን የቅማንት ነገድ ከባሕሩ ከጎንደር ሕዝብ ነጥለው ሊያደርቁት፣ የጎንደርን ሕዝብ ነጣጥለው የትግሬ ወያኔ ጥቃት ተጋላጭ ለማድረግ እየሠሩ ያሉትን የቅማንት ተወላጆችና የእነርሱም ተባባሪ የሆኑ የዐማራ ልጆች እያደረጉ ያለው ሕዝብን የመነጣጠል ተግባር፣ በእናንተ ቀጥተኛ ተሳትፎ በጊዜ እንዲቆም ካላደረጋችሁ፣ ዛሬም ሆነ ነገ የጥፋቱ ግንባር ቀደም ተጠቃሾችና ተጠያቂዎች እናንተ እንደሆናችሁ ትዘነጉታላችሁ አንልም። ይህን የጥፋት ጉዞ ለማስቆምም ኃይሉም ብቃቱም አላችሁ ብለን እናምናለን። ከእናንተ የሚፈለገው ቁርጠኝነቱና ለወገናችሁ የተቆርቋሪነት ስሜት በግልጽ መውጣት ብቻ ነው። «ምን ብጠላው ከወንድሜ ግንባር ደም አልይበት ነውና» ሕዝባችን በዘር ጠላቱ ሲፈጅ ዝም ብላችሁ ለማዬት ኅሊናችሁ የሚፈቅድላችሁ አይመስለንም።

«ጅል ዳኛ የፈረደው፣ ዓመት ያሟግታል» ነውና፣ ለመስከረም 7 ቀን 2010 ዓም በ12 የሰሜን ጎንደር ዞን የቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ይካሄዳል የተባለው ቅማንትን ከጎንደር ዐማራ የመነጠል «ምርጫ» እንደምትገነዘቡት፣ ጥያቄው የቅማንት ሕዝብ ያለመሆኑን ያህል፣ ውሳኔውም የቅማንት እንደማይሆን ግልጽ ነው። ይህ እየታወቀ ሂደቱን እንዲቆም አለማድረግ፣ የጅሉ ዳኛ ፍርድ ሥራ ላይ እንዲውል ወዶ መፍቀድ ነውና፣ ሕዝበ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት፣ የብአዴን አባላት ከሕዝቡ ጎን በመቆም ሂደቱን መቃወም ይጠበቅባችኋዋል። ለዚህ አመራር መስጠት ደግሞ ፣ይህ ጦማር የተጻፈላቸው የድርጅቱ ከፍተኛ መሪዎች መሆን የሚጠበቅ ነው። እነርሱ ግን ይህን ያደርጉታል ተብሎ አይጠበቅም። ካደረጉ ከወያኔ መፋታትን፣ ከሕዝብ ጋር መጋባትን ያስከትላል። ይህ ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል። ዋጋው ውድና ሕይዎትን የሚጠይቅ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህን ውድ ዋጋ የሚከፍል የብአዴን አመራር ካለ «ቴዎድሮስን» ሆነ ማለት ነው። በእስካሁኑ ጉዞ እንደታዘብነው ግን፣ያደርጉታል የሚባሉ አይደሉም። እናም ጀግናን የሚወልደው ወቅት ነውና፣ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ይህን ኃላፊነት ካልወሰዱ፣ በየደረጃ ያላችሁት የድርጅቱ አካላትና አባላት ሕዝባዊና ወገናዊ የሆነ ቆራጥ ውሣኔ በመወሰን፣ የጀግንነት አክሊል በመቀዳጀት፣የታለመው ቅማንትንና የጎንደርን ዐማራ የማለያየቱ ተግባር፣ በሕዝብ ድምፅ ስም ዕውን እንዳይሆን ከሕዝቡ ጎን በመቆም ፣ጎንደርን የማጥፋቱን ዓላማ ማምከን ይጠበቅባችኋል። ይህን ስታደርጉ በውስጥም በውጭም ያለው የዐማራ ትውልድ ከጎናችሁ ይቆማል። ለእናንተም ራሳችሁን በንስኃ ፀበል ከበደል መታጠብ ይሆንላችኋል።

የብአዴን አባላት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሕዝብ ጎን ቆማችሁ የወያኔን አገርና ሕዝብ የመከፋፈልና ከሁሉም በላይ የታላቋ ትግራይ ሪፓብሊክ ምሥረታን ሂደት ካላስቆማችሁ፣ከኅሊና፣ ከታሪክና ከትውልድ ወቀሳ የማታመልጡ መሆኑ ግልጽ ነው። ከዚህ አሳፋሪ ወቀሳ ማምለጥ የሚቻለው፣ ከሕዝብ ጎን በመቆም ብቻ ነው። የሕዝቡ ጥያቄ ምግብ፣ ጤና፣ ልብስ ፤ሕክምና፣ ሰላም፣ ሥራ፣ አንድነትና መቻቻል እንጂ፣ መነጣጠልና ወደ እማያባራ የርስ በርስ ብጥብጥና ጦርነት መግባት አይደለም።

ይህን ሁሉ የምንለው፣ ከእኛ አይቅር፣ አውቀውና ሰምተው ያመኑበትን ያድርጉ፣ ከዚያ ሕዝብ ለሚወስደው ነፃ ውሣኔ ኅሊናው አይጨነቅም፣ እንዲህ ሳልልና ሳላደርግ ይህን ማድረግ አልነበረብኝም ብሎ እንዳይጸጸት የተላከላችሁ ጦማር ነው። በጦማሩ መጠቀምም ሆነ አለመጠቀም የናንተ ውሣኔ ነው።

የጦማራችን አንኳር ሀሳብ፣ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደሞከርነው፣ ለመስከረም 7 ቀን 2010 ዓም የተያዘው የቅማንትን ነገድ ከጎንደር ዐማራ ነጥሎ ለመከለል የተያዘው በሕዝብ ውሳኔ ተብየ ውጤቱ፣ ካለፉት የምርጫ ውጤቶች የማይለይ፣ የሕዝቡን ፍላጎት ሳይሆን፣ የወያኔን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ የሚደመደም መሆኑ ለእናንተ ላለፉት 26 ዓመታት ጉዳይ አስፈጻሚ ሆናችሁ ለተሰለፋችሁ ታጡታላችሁ አንልም። እናም ውጤቱ አስቀድሞ የሚታወቅ አገርና ሕዝብ አጥፊ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ፣ዐማራ ነን የምትሉ የብአዴን አባሎች፣ ዐማራ መሆናችሁን በግልጽ የምታሳዩበት ፈታኝ ወቅት ላይ ያላችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ፣ ከሕዝቡ ጎን እንድትቆሙ ትጠየቃላችሁ።

ቅማንትን ከጎንደር ዐማራ ለመነጠል፣ ወያኔ ባቀደው መልኩ ከቀጠለና የቅማንት ክልል ተከለለ ማለት፣ የቅማናቱን ክልል ከወልቃይት ጋር አገናኝቶ፣ ትግሬን በማስፈር ሰሜን ጎንደርን የትግራይ አካል በማድረግ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ጋር በማገናኘት፣ ወያኔ ሲቋምጥለት ለኖረው የታላቋ ትግራይ ረፐብሊክ ሕልሙ ዕውን የሚያደርግበት የመጨረሻው ርምጃው መሆኑን አውቃችሁ፣ ይህ ከመሆኑ በፊት ከሕዝቡ ጎን በመቆም፣ ሲሠፋ የዐማራውን፤ ሲጠብ የጎንደሬውን አንድነት እንዲጠበቅ እንድታደርጉ ታሪካዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል።

ይህ ጦማራችን ከዕውነተኛ የዐማራ ልጆች የብአዴን አባላት አዎንታዊ መልስ እንደሚያገኝ ተስፋ አለን። በአሉታዊ ለሚመልሱት ደግሞ፣ ለትውልድና ለታሪክ አስተማሪና ነጋሪ የሆኑ ትምህርት ሰጪ ተጨባጭ ርምጃዎች ቆራጦቹ የዐማራ ተጋድሎ አርበኞቻችን እንደሚወስዱ አንጠራጠርም!

የትግሬ ወያኔ ጎንደርን የማጥፋት ዓላማ በተባበረ የዐማራው ተጋድሎ እናከሽፋለን!

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የዐማራ ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.