የማለዳ ወግ… የሮሂንጋ ሰቆቃና የጋዜጠኛው ምስክርነት ! – ነቢዩ ሲራክ 

* ከአል ቃኢዳና ከ ISIS የማይተናነስ እርምጃ ነው
* ቡዲስቶች በፖሊስ እገዛ መንደሮችን አቃጠላቸው

የበርማ /ሚያንማር ራካን ግዛት አናሳ ሮሂንጋ ሙስሊሞች ከሁለት ክፍለ ዘመን ቡዲስት ግፍ ሲፈጸምባቸው የኖሩና እየኖሩ ያሉ ሀገር አልባ ዜጎች ናቸው ። ሮሂንጋ ሙስሊሞች ጭቆናውን ለመመከት ራሳቸው የሚያስተዳድሯት ሀገር በመሻት ከቀድሞዋ ቡርማና ከአሁኗ ሚያንማር ለመገንጠል ቢደራጁም ለውጥ ሊያመጡ ግን አልቻሉም ። ይልቁንም መደራጀታቸ ውና ለመገንጠል የመትጋታቸው ጦስ ዛሬ ድረስ ለሰላማዊው አናሳ ሙስሊም ማህበረሰብ በጀምላ በጭካኔ ግፍ ማለቅ ምክንያት ሆኖ ዘመን ተሻግሯል።

ያለፈውን ትተን ነሐሴ 19 ቀን 2009 ዓም ወይም እአአ ከ August 25, 2017 ከሁለት ሳምንት ወዲህ የሆነውን መመልከት የጉዳዩን አሳሳቢነት ያሳየናል ። ትናንት ጅዳ ላይ በሚያንማር ሮሂንጋ ሙስሊሞች መከራና ሰቆቃ ዙሪያ በመከረ ው የአለም እስላሞች ጉባኤ የሚንማርን መንግስት የሚያወግዝ መግለጫ አውጥቷል።መግለጫው” የሚያን ማር መንግስት እርምጃ ከአል ቃኢዳና ከ አይ ሲ ኤስ ISIS የማይተናነስ እርምጃ ነው” ይላል የወጣው መግለጫ። መግለጫው እየሆነ ካለው እውነት ጋር አገናኝቸው ትኩረቴን ባይስበውም በመግለጫው የተካተተው በሮሂንጋ ተፈመ ተብሎ የቀረበ ግፍ ያማል

በሚያንማር ሮሂንጋ ግጭት ካገረሸ ወዲህ 6,334 አናሳ ሙስሊሞች በግፍ መገደላቸው ተጠቅሷል። 8,349 መቁሰላቸው ፣ 500 ሴቶች መደፈራቸው ፣ 103 መንደሮች መውደማቸው ፣ 23,250 ቤቶች መቃጠላቸውና 335 ,000 ሮሂንጋ ሙስሊም ነዋሪዎች ቤት አልባ መሆናቸውን ላይ ልብ ሰባሪ መረጃ ሆኖ እናገኘዋለን ። ይህ ሁሉ ሲሆን የተመለከተው አለም ዝምታን መርጦ በመግለጫ ጋጋታ እያጨናነቀን ነው ። በመግለጫው ከውግዘት ያለፈ እርምጃ የማያሳየው የተባበሩት መንግስታትን ድርጅት በሁለት ሳምንቱ ግጭት ብቻ 150.000 የሚደርሱ የሚያንማር ሮሂንጋ ሙስሊሞች ወደ ጎረቤት ባንግላዲሽ መሰደዳቸውን ያስረዳል። በቃ ! የመንግስታቱ ድርጅት ይህ የስደተኛ ሰቆቃ
መከራ ከመሆን ባለፈ ግፉን ማስቆም ያልቻለ የመንግስታት ጥርቅም ሆኖ አርፏል  ያስዝናል …

የሰሞኑ የሚንማር መንግስትና የቡዲስት እምነት ተከታዮች እርምጃ የአለም መገናኛና ማህበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ እንደሆነ ቀጥሏል። የመንግስታት ዝምታ የቆጨው ሰብአዊ ሰው አናሳ ሙስሊማኑ በሚደርስባቸው የለየለት ግፍ ፍትህ ያገኙ ዘንድ በፊርማና በሰላማዊ ሰልፍ ሳይቀር ግፊት እየተደረገ እየተጠየቀ ነው። ሰሞነኛ ግጭቱን ተከትሎ የቀደሙ ረባሽና አሰቃቂ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎች እየተሰራጩ ፣ የሆነውን ትቶ ያልሆነ ግነት የታከለበት ታሪክ መጻፉ በስፋት ይስተዋላል። ይህም እውነተኛው መረጃ እንዲደበዝዝ ምክንያት እንዳይሆን ስጋት ይመስለኛል። ይህ መሰሉ አካሄድ በእኛም በሀበሾቹ መንደር እየተስተዋለ መጥቷልና የቆዩ መረጃዎች ላይ አለማተኮሩ ጠቃሚ መሆኑን መጥቀሱ ይበጅ ይመስለኛል !

የሰሞኑ ግጭትና የጋዜጠኛው ምስክርነት …
=========================== በዚህ ሁሉ መካከል ትክክለኛ መረጃዎችን የሚንማር ሮሂንጋ አናሳ ሙስሊማን በሚኖሩበት አካባቢ የተገኘ በሚያንማር መንግስ ት ከተመራ የጋዜጠኞች ቡድን ጋር ያቀናው የቢቢሲ ጋዜጠ ኛ ጆናታን ሄድ ስለ ግጭቱ ነዋራዊ ሁኔታ የተመለከተውን ምስክርነት ሰጥቷል። ጋዜጠኛ ጆናታን ሄድ ግጭት ተቀሰቀሰባቸው የተባሉ መንደሮችን ከጎበኘ በኋላ ባወጣው ሪፖርት የሚያንማር ራካሂን ቡዲሂስቶችና በሚያንማር ፖሊሶች እርዳታ ቤት ማቃጠላቸውን አጋልጧል።

ጋዜጠኛ ጆናታን ሄድ ባሰራጨው የጉዞ ሪፖርት ምስክርነቱን ሲሰጥ የግጭቱን ማገርሸት ተከትሎ የሚንማር መንግስት ግጭቱ አለ ወደተባለበት ራካን መንደሮች ቢወስዳቸውም በነጻነት እንዲንቀሳቀሱና መረጃ እንዳይሰበስቡ ” አማጽያኑ የመንደሩ ነዋሪዎች ግጭቱ አለም አቀፍ ትኩረት እንዲሰጠ ው ቤቶቻቸውን ያጠቃጥላሉ ” በማለት አማጽያኑ ጋዜጠኞች ን ሊያጠቁ እንደሚችሉ ምክንያት በመስጠት ተጓዥ ጋዜጠ ኞች በቂ መረጃ ከነዋሪው ምስክርነት ሊሰበስቡ እንደታገዱ ተናግሯል ።

ጋዜጠኛ ጆናታን በአንጻሩ በራካን ጋዱ ዛራ በተባለ መንደር ቤት ሲያቃጥሉ የተመለከታቸው አማጽያኑ ሳይሆኑ ነዋሪውና የሚንማር ወታደሮች መሆናቸውን በሰጠው ምስክርነት እንዲህ ብሏል…

” እኔ ሰሞነኛ ግጭቱን ተከትሎ የሚንማር መንግስት ባደረገው ግብዣ መሰረት ከተጋበዙትና ወደ ግቱ ቦታ ከተጓዘው የጋዜጠኛ ቡድን መካከል አንዱ ነኝ ። በጉዟችን በነጻነት መረጃ የምብሰበስብነት ሁኔታ አልነበረም ። የምንጓዘው የሚንማር መንግስት ወደ መረጠውና ቦታ ብቻ ነበር ። ወደምንፈልገው ቦታም ሆነ ወደ አቅራቢያው መሄድ አይፈቀድልንም ነበር።

” ከደቡብ ሞንግዳው አል ሊ ታን ኪያው Al Le Than Kyaw, south of Maungdaw ስንመለስ ትኩስ ጭስ የሚወጣባቸው ቤቶችን ተመለከትን ። አብሮን ያለው ፖሊስ ባሳለፍነው 25 August 2017 አማጽያንና ነዋሪዎች ሆን ብለው ያቀጣጠሉት ቤቶች ናቸው አሉን። እኛ የተመለከትነው ግን በመደዳው ባሉ ሶስት የቤት ግድግዳዎች ያልጠፋ እሳት የፈጠረው ትኩስ ጭስ ነው ። በቅርብ ርቀት ደግሞ የአውቶማቲክ መሳሪያ ጩኸት ይሰማል ። እየተመለስን እያለም ሌሎች በ20 እና በ30 ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ የተቃጠሉ ቤቶችን ፣ የተቃጠሉ ዛፎችንና የሩዝ ሰብል ጭስ ተመልክተናል ። ይህም በዚያ መንደር ምን እንደተፈጠረ ምልክት ነበር ።

“በእግራችን ስንዘዋወር አንድ ጦር ፣ ጎራዴና ሌላም መሳሪያ የያዘ ፈርጣማ ጎልማሶች ተመለከትን ። ለማነጋገር ሞክረን ፈቃደኛ አልሆኑም ። ወፈ ኋላ ላይ አንድ ሚንማራዊ ወዳጄ ካሜራ ሳያቀርብ ጠየቋቸው የራካቡ ቡዲስት እምነት ተከታዮች መሆናቸውን ገልጸውለታል ። ከመካከላቸው አንዱ እሳት ለማያያዙ ከሚንማር ፖሊሶች እርዳታ ማግኘቱን ተናግ ሯል። በጉብኝታችን ወቅት የእስልምና ትምህርት የሚሰጥ ባቸው መድረሳዎች ጣራቸው ብቻ ቀርቶ ተመልክ ተናል። ከአጠገቡ ያለ ቤት በእሳት መያያዙንም አይቻለሁ። ከዚህ ቀደም ካየናቸው ጎልማሳ ስለት የታጠቁ ቡዲስቶች ውጭ በመንደሩ ሰው የለም ። የቤት እቃ ፣ የልጆች መጫዎቻዎች ፣ የሴት ልብሶች እዚህ እዚያ ወዳድቀው ተመልክቻለሁ ። ባዶና ትርፍራፊ የነዳጅ መያዣ ቆርቆሮዎችም ወዳድቀው ነበሩ… ” በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል…

ፍትህ ለሀገር አልባ ዜጎች !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ጳግሜ 3 ቀን 2009 ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.