ኢት-ኢኮኖሚ: የጡብና አዳፍኔ ዘመን ዘር አፈራሽ ባንኮች!!! ‹‹ትንሽ ምላጭ፣ አገር ትላጭ›› (ክፍል አንድ) – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ባለፈው 26 ዓመታት፣ በኢትዩጵያ  የፋይናንስ ዘርፍ አደረጃጀትና የባንክ አገልግሎት  አሰጣጥ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደደረሰ የተለያዩ ምሁራን ስለ ባንኮች የሠጡትን ምክረ ሀሳባችና ጥናታዊ ዳሰስ እናቀርባለን፡፡ በኢትዩጵያ 18 የግል ባንኮች ተፈጥረዋል፡፡ ዓባይ ባንክ፣አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ብርሃን ኢንተርኛሽናል ባንክ፣ ቡና ኢንተርናሽናል  ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ እናት ባንክ፣ አንበሳ ኢንተርናሽናል  ባንክ፣ ንብ ኢንተርናሽናል  ባንክ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል  ባንክ፣ ህብረት ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ዘመን ባንክ፣ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዩጵያ ልማት ባንክና የተዋሀደው የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ይጠቀሳሉ፡፡ የዚችን አገር እጣ ፈንታ ወዴት እንደሄደ እነዚህ ወንዝ አፈራሽ፣ ዘር አፈራሽ የጡብና አዳፍኔ ዘመን ባንኮች በብሄር፣ በፓርቲና ሃይማኖት ተኮር ሆነው መመሥረታቸው የሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍና የባንክ ሥራ እውቀት፤ እንዲሁም የባንክ አገልግሎት የድንቁርና ግርዶሽ ያጠላበት ዘመን ለመሆን አስችሎል፡፡ በአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት በ1906 እኤአ የተመሰረተው አቢሲንያ ባንክ በሃገሪቱ ወርቃማ የባንክ ዘመን የመጀመሪያው መሆኑን ያበሰረ፣ከዛን ዘመን ጀምሮ ህብረ-ብሄር የሆኑት የባንክ ሠራተኞች በዕውቀት የተካኑ፣ የባንኩ ደንበኞች በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በመሆኑ፣ባንኮች በሚሰጦቸው አገልግሎቶች የባንኩ ሠራተኞች በደንበኞቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና በህዝቡ ዘንድም ታላቅ እምነት ያሳደሩ ነበር፡፡

አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የዘመኑን ባንክ ሲገልፁት፣‘’በሃገራችን የፋይናንስ ዘርፍ ላለፍት ሃያ አምስት አመታት በዘርፉ የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎች አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጎል፡፡ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የህብረት ባንክና ኢንሹራንስ መሥራች እንዳሉት ከሆነ፣ በሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ‹‹የተማቱ አፈጣጠር የተለያየ በመሆኑም ለማዋሃድ የሚቻለውም ቀድሞ ሥራ ሲሰራ ነው፡፡ አንዳንዱ በብሄር፣ አንዳንዱ በፓርቲ፣ ሌላውም በሃይማኖት የተቋቋሙ ስለሆነ አሁን ባለው ሁኔታ መቀላቀል ያስቸግራል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለማንኛውም እውነተኛ ውድድር እንዲኖር ለአገር በቀል ገበያ እኩል ሜዳ ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ያልተስተካከለ ገበያ ውስጥ ተቀምጠን፣ ከጊዜ በኃላ ኢኮኖሚያችን መከፈቱ ስለማይቀር በሚከፈትበት ጊዜ ደካማ ተማት ሆነን የውጭዎቹ በቀላሉ እንደ አርጀንቲናና ፊሊፒንስ ኩባንያዎች እንዳንበላ ሥራው ቀድሞ መጀመር አለበት፡፡›› ብለዋል፡፡

የጡብና አዳፍኔ ዘመን ዘር አፈራሽ ባንኮች!!! የኢትዩጵያ ባንኮችና ኢንሹራንሶች የማን ኃብት ናቸው???

የባንክ ስም የፎቅ ወለልና የግንባታው ወጪ
1 ዘመን ባንክ፣ 34 ወለል ፎቅ፣1.23 ቢሊዩን ብር
2 ሕብረት ባንክ፣ 32 ወለል ፎቅ፣1.5 ቢሊዩን ብር
3 ወጋገን ባንክ፣ 23 ወለል ፎቅ፣1.0 ቢሊዩን ብር
4 የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ 46 ወለል ፎቅ፣6 ቢሊዩን 129 ሚሊዩን 500 ሽህ  ብር
5 አዋሽ ባንክ 18 ወለል ፎቅ፣1.23 ቢሊዩን ብር
6 አቢሲንያ ባንክ — ወለል ፎቅ፣350 ሚሊዩን ብር
7 አንበሳ ባንክ 30 ወለል ፎቅ፣ – ቢሊዩን ብር
8 ዳሽን ባንክ  –  ወለል ፎቅ፣1.088 ቢሊዩን ብር
9 ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 30 ወለል ፎቅ፣1.0 ቢሊዩን ብር
10 ጠቅላላ የባንኮች ወጪ 15 ቢሊዩን 733 ሚሊዩን ብር

{1} ዘመን ባንክ፣ ባለ 34 ወለል ፎቅ የግንባታው ወጪ 1.23 ቢሊዩን ብር ኮንትራክተር፤ ውዩ ኩባንያ የቻይና ካንፓኒ የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

{2} ሕብረት ባንክ፣ ባለ 32 ፎቅ ወለል ያለውን የግንባታው ወጪ 1.5 ቢሊዩን ብር ኮንትራክተር፤የቻይና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

{3} ወጋገን ባንክ፣ ባለ 23 ፎቅ የግንባታው ወጪ 1.0 ቢሊዩን ብር ኮንትራክተር፤የቻይና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

{4} የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዋና ቢሮ ባለ 46 ወለል ያለው ፎቅ የግንባታው ወጪ በ266.5 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም 6 ቢሊዩን 129 ሚሊዩን 500 ሽህ  ብር ኮንትራክተር፤ የቻይና መንግስት የኢንጅነሪንግ ግንባታ ኮርፖሬሽን China State Construction engineering Corporation (CSCEC)፤ በአዲስ አበባ ከተማ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

{5} አዋሽ ባንክ ባለ 18 ፎቅ የግንባታው ወጪ 1.23 ቢሊዩን ብር ኮንትራክተር፣የጣልያኑ ቫርኔሮ የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ሌሎች ቅርንጫፍ ባንኮች በአዲስ አበባ ባለ16 እና ባለ11 ፎቆች፣ ደዴሳ ባለ2 ፎቅ፣ጅማ ባለ 6ፎቅ፣ ቢሾፍቱ ባለ 4 ፎቅና፣ ሌላ 10 የባንክ ህንፃዎች፤

{6} አቢሲንያ ባንክ ባለ  ፎቅ የግንባታው ወጪ 350 ሚሊዩን ብር ኮንትራክተር ቫርኔሮ የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቋራጮች ሲሰራ፣ በአዲስ አበባ፣ ቦሌ፣ጨፌ፣ሜክሲኮ የግንባታው ወጪ 110 ሚሊዩንና ለመሬት ግዥ 24.5 ሚሊዩን ብር አውጥተዋል እንዲሁም ሃዋሳና ጅማ ቅርንጫፍ ይሰራል

{7} አንበሳ ባንክ በአዲስ አበባ ባለ 30 ወለል ፎቅ እንዲሁም ትግራይ ውስጥ ባለ 10 ወለል ፎቅ  የግንባታው ወጪ እና የኮንትራክተር ስም አልተገለጸም፡፡

{8} አባይ ባንክ በአዲስ አበባ ባለ   ወለል ፎቅ የግንባታው ወጪ  800 000 000 ሚሊዩን ብር ሲሆን እንዲሁም ባህር ዳር ባለ 10 ወለል ፎቅ የግንባታው ወጪ 4000 ሚሊዩን ብር የኮንትራክተር ስም አልተገለጸም፡፡

{9} ዳሽን ባንክ አዲስ አበባ ባለ  ወለል ፎቅ የግንባታው ወጪ 1.088 ቢሊዩን ብር ኮንትራክተር አልታወቀም፡፡

{10} ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለዋና መስሪያ ቤትነት እያስገነባ የሚገኘው ከ30 ወለል ፎቅ በላይ የሆነ ህንፃ 1 ቢሊዩን ብር ይገመታል፡፡ ንብ ባንክ ከዚህ በተጨማሪ ባለ ሰባት ወለል ሕንፃ በ680 ሚሊዩን ብር የጨረታ ዋጋ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል አጠገብ ለቢሮ የሚሆን ህንፃ ገዝቶል፡፡ ጠቅላላ በኢትዩጵያ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ባንኮች ለዋና መስሪያ ቤትነት እያስገነቡ የሚገኘው አጠቃላይ የግንባታው ወጪ 15 ቢሊዩን 733 ሚሊዩን ብር ይገመታል፡፡

በኢትዩጵያ ለባንኮች ኮንስትራክሽን ጠቅላል ወጪ 15,733 ቢሊዩን ብር እንደሆነ ከገላጭ ሠንጠረዡ ማየት ይቻላል፡፡ የኢትዩጵያ ህዝብ ከ10 እሰከ 20 በመቶ ብቻ ከባንክ ጋር ግንኙነት በሚያደርጉበት አገር 15 ቢሊዩን 733 ሚሊዩን ብር ለህንፃ ግንባታ ከማዋል ለሰው ኃይል ልማት ማለትም ህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል እንዲያዳብር፣ የባንክ ጥቅምን፣የመድህን ዋስትና ጥቅምን በማስተማር የሰውን ህሊና አስቀድሞ መቀየር ያስፈልጋል፣ ሰማይ ጠቀስ የባንክ ፎቆች ከመገንባት ይልቅ በሃገሪቱ ውስጥ ትንንሽ ቅርንጫፍ ባንኮችን ማስፋፋት የባንክ ተደራሽነትን ለማብዛት የተሸለ ይሆናል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ሰማይ ጠቀስ ፎቆች እንዲገነቡ ባለፀጋዎቹን ይገፋፋል፣ የፎቅ ግንባታ ለቢሮና ለመኖሪያ ኪራይ ከመሆን በስተቀር ግዜያዊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ጠቀሜታው ዝቅተኛ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በየቦታው የሚከራይ ቢሮ ወዘተ ተለጥፎ ማየት አሥር ዓመታት በላይ አሳልፎል፡፡ ማለትም የፎቅ ግንባታው አቅርቦት ከፍላጎቱ ስለበለጠ የፎቅ ግንባታ ገቢ በማሽቆልቆል ላይ ይገኛል፡፡

መንግሥት የከተማ ነዋሪዎችን ንብረት ለመንጠቅ ከአራት እስከ አስር ፎቅ ካልሰራችሁ ተነሱ በማለት በመሬት ነጠቃና ሽያጭ ንግድ ተጠምዶል፡፡ እንደ መንግሥት ባለኃብቶቹን በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፎች መዋለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ፣ኢንቨስት እንዲያደርጉ አያማክርም፡፡ የወያኔ መንግሥት የተንሸዋረረ ኢንቨስትመንት ፖሊሲ ምክንያት፣ ኢንቨስትመንቱ አዲስ ምርትና እሴት የማይፈጥር፣ የሥራ ዕድል የማይከፍት፣ የውጭ ምንዛሪ የማያስገኝ፣ በከተማና ገጠር ነዋሪዎች ማኃል የኃብት ክፍፍልን የሚያሰፋ ለመሆን በቅቶል፡፡ በትግራይ ከተማ ነዋሪዎች የሦስተኛው ዓለምና የአፓርታይድ መንደሮች ብለው የሰየሞቸው ከተሞች አሉ፡፡ በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በሃዋሳ፣ ህዝቡ የሰየማቸው፣ የሙስና መንደሮች፣ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ደሃ ማቆር፣ ቆሼ መንደር፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሠፈር ወዘተ የሚባሉ በህብረተሰቡ ላይ የሃብታምና ደሃ መንደሮች በሰዎች ህሊና የስነ-ልቦና ቀውስ እየፈጠረ መሆኑን ምሁራን በጥናት አረጋግጠዋል፡፡ በከተማውና ገጠሩ ህዝብ የህይወት ትስስር ድርና ማግ የነበሩ የማህበራዊ ኑሮ እሴቶች እድር፣ እቁብ፣ ማህበር፣ ፅዋ መጠጣት፣ወዘተ የደስታና የሃዘን ጊዜት መገናኛ የነበሩ እሴቶች በሙሉ በማጥፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ወያኔ ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝቡ በማፈናቀልና በተለያዩ ቦታ ህዝቡን በማስፈር ምህበራዊ ኑሮን አናግቶል፡፡

በ2003 ዓ/ም 680 የቅርንጫፎች ባንኮች ቁጥር የነበረ ሲሆን፣ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይ 2800 ደርሶል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወደ 3900 ደርሶል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትም 1600 ቅርንጫፎች መድረስ ችለዋል፡፡ ከባንክ ቅርንጫፎች ከ3900 ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የግል ባንኮች ናቸው፡፡ 18 ሽህ የነበረው የባንክ ሠራተኛ አሁን ከ20 ሽህ በላይ ሆኖል፡፡

በ2013 እኤአ የግል ዘርፍ ባንኮች ቅርንጫፎች በኢትዩጵያ (868)ና የኢትዩጵያ መንግስት ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች (832) በአጠቃላይ የቅርንጫፎች ባንኮች ድምር (1700) የኢትዩጵያ ህዝብ ብዛት (93.8 ሚሊዩን) ጋር ሲነፃፀር 1 ቅርንጫፎች ባንክ 55,176 ሽህ የኢትዩጵያ ህዝብ ይደርሳል፡፡ የኢትዩጵያ ህዝብ ብዛት በ2013 እኤአ (93.8 ሚሊዩን) ውስጥ 10 ሚሊዩን ህዝብ የባንክ ተጠቃሚ ሲሆን ማለትም  10.7 እጅ ከመቶ የባንክ ተጠቃሚ ሲሆን የቀረው 89.3 እጅ ከመቶ የባንክ አገልግሎት እንደማያገኝ በጥናት ተረጋግጦል፡፡

Microfinance institutions (MFIs) and Savings and Credit Cooperatives (SACCOs) should increase their reach to the poor. In 1996, the National Bank of Ethiopia (NBE) developed a prudential regulatory framework for microfinance to supply financial services to the poor. The Microfinance Proclamation 40/1996 opened the possibility for the establishment of deposit-taking MFIs.20 Despite these efforts, in March 2015, there were only 24 MFIs providing financial services. Their penetration ratio is still low, with less than 4 percent of the population being served. Similarly, SACCOs, which are voluntary associations with a purpose to save and lend money to its members, remain small by international standards. Although they are growing in number, their coverage is insignificant relative to the size of the unbanked population.

2015 እኤአ በአገሪቱ አሁን ያሉት ሦስት ሽህ የባንክ ቅርንጫፎች ተደራሽነታቸው ምን ያህል ነው ቢባል አነስተኛ ነው፡፡ በኢትዩጵያ የሥነህዝብ  ቁጥር  99,465,819 ሚሊዩን ሲሆን  33,155 ሽህ ህዝብ አንድ የባንክ ቅርንጫፍ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሰማይ ጠቀስ የባንክ ህንፃዎች ግንባታ ይልቅ የቅርንጫፍ ባንኮች ማስፋፋትና የባንክ ተደራሽነትን ማብዛት የተሸለ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ህብረተሰቡን ስለ ባንክ ቁጠባ ባህል እንዲያዳብር  የባንክ ሂሳብ ደብተር እንዲይዝ ትምህርት ማስረፅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሌላው የሚገርመው ነገር ከ99 ሚሊዩን ህዝብ ውስጥ 950 ሽህ ሰዎች ወይም 1 በመቶ ባለኃብቶች ብቻ ከባንኮች የመበደር መብት አላቸው፡፡ ሰፊው ህዝብ ከባንኮች ውስጥ ገንዘቡን የማስቀመጥ መብት ሲኖረው የመበደር መብት ማስያዣ (collateral) ቤት፣ ቪላ፣ ፎቅ፣ መኪና፣ ፋብሪካ፣ እርሻ፣ ሆቴል፣ ወዘተ የሚያሲዘው ንብረት ስለሌለው የመበደር መብት የለውም፡፡

Financial development in Ethiopia should focus particularly on rural areas where the majority of the population resides. In Ethiopia, access to finance is primarily through the banking sector and microfinance institutions (MFIs). There are 18 commercial banks and one state-owned development institution (Development Bank of Ethiopia). The sector is highly concentrated, with the

largest, state-owned commercial bank comprising about 70 percent of total assets. Banks have been rapidly expanding their branches, which have increased four-fold since 2010. However, as more than a third of branches is located in Addis Ababa, the rural areas (with almost 80 percent of population) still lack good access to financial services. Despite rapid growth, compared to other countries in the region, the population per bank branch remains high (35,957 as of March 2015).

‹‹የአገር ውስጥ ባንኮች  ለህዝብ ተደራሽነታቸውን ከማስፋት አካFüያ ውስንነት ስላለባቸው በቢሊዩን ብር የሚገነባ አንድ ባንክ ከመገንባት ይልቅ ብዙ ትንንሽ ባንኮች በየክልሎቹ በማነጽ ለህዝብ ተደራሽ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ የከተማውና የገጠሩ ህዝብ ዛሬም ገንዘብ በእጁ ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው፣ገንዘቡን ከቤት ውስጥ ነው የሚያስቀምጠው፡፡ ባንኮቹ ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፡፡ ባንኮቹ ከህዝብ ተቀማጭ ገንዘብ 5 በመቶ የተቀማጭ ወለድ በመስጠትና ገንዘብ ሲያበድሩ 17 በመቶ የብድር ወለድ በመቀበል እንዲሁም ለሠራተኞች ደሞዝ 3 በመቶ በመክፈል ባንኮች ያገኙትን ትርፍ 9 በመቶ ከመከፋፈል ውጭ ረጅም ራዕይ ሰንቀው መስራት አቅማቸው ደካማ ነው፡፡ ህዝቡ በሚያስቀምጠው ተቀማጭ ገንዘብ የሚያገኘው የተቀማጭ ወለድ አነሰተኛ ነው፡፡ በአንጻሩ ባንኮች የሚያበድሩት ገንዘብ የብድር ወለዱ ከፍተኛ ነው፡፡  ከዚህ ሰፊ ልዩነት ተጠቃሚ የሆኑት ባንኮች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው አንድ ባንክ በተቋቋመ በሁለተኛ ዓመቱ ብዙ አተረፍኩ ሲል የምንሰማው፡፡›› በአዳፍኔ ተኩስ የማይፈርሱ ባንኮች ከመገንባት ህዝቡን የቁጠባ ገንዘብ የማስቀመጥ ባህል እንዲያዳብር ማስተማር ማለትም የባንክ ህንጻ ከመገንባት ይልቅ የሰዎች ህሊናን መገንባት ለሥልጣኔ እድገት በር ከፋች ነው፡፡

የቻይና ኮንትራክተሮች የኢትዩጵያን የፋይናንስ ተቋማት የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃዎቸ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ በዲጂታል ኢኮኖሚ/በኢንተርኔት ኢኮኖሚ/ድረ ገፅ ኢኮኖሚ ዘመን በአዳፍኔ ተኩስ የማይፈርሱ ባንኮችና፣ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች መገንባት ማህይምነት ነው፡፡ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መረጃ ዘመን  የጥሬ ገንዘብ ዝውውር  በመስመር የለሽ ስልኮች ወይም ሞባይሎች፣ኢቲኤም፣ከቤት ሆኖ ገንዘብ በቀበል፣ማስቀመጥ፣ዕቃ መግዛትና መሸጥ ወዘተ የስልጣኔ ዘመን አዳፍኔ የማይደረምሰው የባንክ ህንፃ ግንባታ አላዋቂነት ነው፡፡ በዓለማችን የባንክ ቅርንጫፎች ቁጥር ቀንሶል፣ ቅርንጫፍ አልባ ባንኮች እየተስፋፉ ይገኛሉ፡፡ ‹‹Internet banking has increased, certain banks have closed many branch facilitiesm estimated at 1,487 closures within the year 2014. Certain banks assert that additional branches are underperforming, likely due to the increase in online banking options, but will likely remain.››

ባንኮች ተደራሽነት ከ100 ሚሊዩን ህዝብ ውስጥ 22 ሚሊዩን ህዝብ ብቻ ያገለግላሉ፣ ባንኮች ህብረተሰቡን ስለ ባንክ ጥቅም ስለ ገንዘቡ ቁጠባ ባህል እንዲኖረና የባንክ የቁጠባ ደብተር በነፃ እንዲያወጣ በማድረግ ገንዘብ ማስቀመጥ ልምድ እንዲያዳብር የማድረግ አስፈላጊው ቅስቀሳና የባንክ እውቀት ለህዝብ ሳያስገነዝቡ ፎቅ በመገንባት ግዜቸውን ያጠፋሉ፡፡

በ2008 ዓ/ም የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በኢትዩጵያ የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር ሲሆን በአንጻሩ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ በሌላ በኩል የመንግሥትና የግል ባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር አካባቢ ነው ያላቸው፡፡ ከህዝብ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብን ከባንኮች ተቀማጭ ካፒታል ስናቀናንሰው (670 ሲቀነስ 30 ቢሊዩን ብር) 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነው፡፡

ፕሮፊሰር ዶክተር ፍቅረማርቆስ መርሶ እንዳሉት ‹‹በኢትዩጵያ የባንክ ሴክተር፣ ከዓለም አቀፍ የባንኮች ውድድር መንግሥት ስለጠበቃቸው ብቻ  ነው ብዙ ትርፍ እያገኙ ያሉት፣ መንግስት በተዘዋዋሪ አቅማቸውን እንዲገነቡና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጊዜ እየሰጣቸው ቢሆንም 20 ዓመት ሆኖቸዋል፡፡ ግን በቂ ለውጥ አላመጡም፡፡ ባንኮቹ ዕድሉን ካልተጠቀሙበት መንግስት እስከመቼ ከውጭ ውድድር ይከላከልልንና ትርፉን እየተከፍፈልን እንኑር የሚለው ነገር ምን ያህል ያስኬዳል የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ አሁን ባለው አቅም ከውጭ ባንክ ኩባንዎች ጋር በፍፁም ሊወዳደሩ አይችሉም፡፡ አሁን ያለው የውጭ ባንክ አገልግሎት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ነው፡፡ የእኛው ደግሞ በአንፃሩ ደካማ ስለሆነ የመወዳደር አቅም አይኖራቸውም፡፡ ባንኮቹ ቴክኖሎጅን በመሳብ፣ አዳዲስ አሰራሮችን በመፍጠር ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን አቅም ማጎልበትና መተግበር አለባቸው፡፡ መንግስት ካፒታላቸውንም እንዲያሳድጉና የተሸለ አሰራር እንዲተገብሩ እየገፋቸው ነው፡፤ ምክንያቱም የሽንኩርት ንግድ ይመስል በመቶ ሚሊዩን ብር ባንክ ልትመሰርት አትችልም፡፡ ስለዚህ ትንንሽ ባንኮችን ከማብዛት ይልቅ ትልልቅ ሆነው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅማቸውን በማጎልበት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን ለግሰዋል፡፡››

በ2009 ዓ/ም የመንግስት ባንኮች፣የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ የሚከታተላቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትጵያ ልማት ባንክና የኢትዩጵያ መድን ድርጅት የ2009 ዓ/ም የዕቅድና አፈፃፀም ጠቅላላ ሀብት፤በሶስቱ የመንግሥት የፋይናንስ ተቆማት የ2009 ሂሳብ ዓመት ክንውን መሠረት የ523 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት መመዝገቡን ሲገለፅ፣ ከታቀደው የ517 ቢሊዩን ብር አኮያ ከ100 በመቶ በላይ ጭማሪ መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም ከነበረው የ440.4 ቢሊዩን ብርጠቅላላ ሀብት አኮያ የ82.6 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቦል፡፡ ከጠቅላላው ሀብት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ የተመዘገበው 60 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱም ታውቆል፡፡ ከዚህ ውስጥ በብድር መልክ የተመዘገበው ሃብት 184 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በኢንቨስትመንት መልክ ከ269 ቢሊዩን ብር በላይ ነው፡፡ አጠቃላይ የዕዳ መጠን፤ በሦስቱ ተቋማት በ2009ዓ/ም ያስመዘገበት አጠቃላይ የዕዳ መጠን 490 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በ2008ዓ/ም የነበራቸው የእዳ መጠን 415 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ተቋማቱ ካፒታል መጠባበቂያ ክምችታቸውን ጨምሮ 33 ቢሊዩን ብር መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡ በብድር ሥርጭት፤በሦስቱ ተቋማት  በብድር ሥርጭት ረገድ ድርጅቶቹ 124 ቢሊዩን ብር ብድር (የብድር ቦንድ ኩፖን ታክሎበት) ማሠራጨታቸው ሲገለፅ፣አብዛኛው ድርሻ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ ተመልክቶል፡፡ባንኩ 94.5 ቢሊዩን ብር ብድር መሰጠቱ፣54 ቢሊዩን ብር ገደማ ብድር መሰብሰቡንና የብድር ክምችቱም በቦንድ የሰጠውን ጨምሮ 420 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱ ታውቆል፡፡ የተበላሸ የብድር፤ በሦስቱ ተቋማት የተበላሸ የብድር መጠኑ ከጠቅላላው ብድር ውስጥ 2.8 በመቶ መሆኑ ሲገለፅ፣የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የአምስት በመቶ የተበላሹ ብድሮች ጣሪያ አኮያ ዝቅተኛ ሆኖል፡፡ ከዚህም በላይ 14.6 ቢሊዩን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን፣ ከ2008ዓ/ም መጠንም የ5.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቆል፡፡

ዶክተር ጌትነት በጋሻው ‹‹በባንኮች እያደግን ነው የሚሉት ውሃ አይቆጥርም፡፡ የአገር ውስጥ ባንኮች የካፒታል ዕድገት የተሸለ እንደሆነ ቢጠቀስም ለህዝብ ተደራሽነታቸውን ከማስፋት አካüያ ውስንነት እንዳለባቸው ይሰተዋላል፡፡ ህብረተሰቡም አሁንም ገንዘብ በእጁ ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ ባንኮቹ ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፡፡ ባንኮቹ ያገኙትን ትርፍ ከመከፋፈል ውጭ ረጅም ራዕይ ሰንቀው መስራት አቅማቸው ደካማ ነው እንዲያውም ‹‹ዶሮ ብታልም ጥሬዋን›› ዓይነት ነው ከዓለም አቀፍ የባንኮች ውድድር አንጻር ሲታይ ወደ ኃላ የቀሩ ናቸው፡፡ የኢትጵያ ባንኮች ከዓለም አቀፍ የባንኮች ውድድር አንጻር በጭራሽ ተወዳዳሪ አይደሉም፡፡ እንካüን ከውጭው ባንኮች ጋር እርስ በእርሳቸው እንካü አልተወዳደሩም፡፡ ደንበኛው በአነስተኛ ዋጋ ብድር ማግኘት አለበት፡፡ የብድር ወለዱ ከፍተኛ ነው፡፡ በአንፃሩ የተቀማጭ ወለድ ደግሞ አነሰተኛ ነው፡፡ ከዚህ ሰፊ ልዩነት ተጠቃሚ የሆኑት ባንኮች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው አንድ ባንክ  በተቋቋመ በሁለተኛ ዓመቱ ብዙ አተረፍኩ ሲል የምንሰማው፡፡ የሁሉም ባንኮች የተጣራ ሀብት ቢደመር እንካüን አንድ ትልቅ የውጭ ባንክ ላይሆን ይችላል፡፡ ባንኮች  ራሳቸው ይበልጥ ደንበኛውን በሚያረካ መልኩ ማሳደግ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን የውጭዎቹ ባንኮች በዚህ ሁኔታ ወደ  ሃገር ውስጥ ቢገቡ ገብያቸውን ይወስዱባቸዋል፡፡ አሁን በእኛ ባንኮች የማይሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶችን በውጭ አገር እናያለን፡፡ በአንፃሩ ባንኮች አሁን በአላቸው የአገልግሎት አሰጣጥም ሆነ አደረጃጀት የውጭውን ዓይነት አገልግሎት ሊያመጡ ስለማይችሉ የውጭዎቹ ካላቸው ዓለም አቀፍ ልምድና አቅም አንፃር የደንበኛውን ቀልብ በአንድ ጊዜ ነው የሚማርኩት፡፡ ስለዚህ የእኛዎቹ መጀመሪያ በራሳቸው መጠንከር አለባቸው፡፡ በአገሪቱ አሁን ያሉት ሦስት ሽህ የባንክ ቅርንጫፎች ተደራሽነታቸው ምን ያህል ነው ቢባል አነስተኛ ነው፡፡ የውጭ ባንኮች ቢገቡ ግን ይህን ሁሉ ጠቅልለው የእኛዎቹን ያንኮታኩቶቸዋል፡፡ የኢትዩጵያ ባንኮች ረጅም ጊዜ ዕይታ የሌለው አካሄድ አያዋጣቸውም፡፡ እናም ረጅም ጊዜ ራዕይ ኖሮቸው ተደራሽነታቸውን ማስፋትና ለለውጥ መትጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኢትዩጵያ ባንኮች የዓለም አቀፍ የባንኮች ልምድ አይተው መተግበር ከቻሉ የውጭ ባንኮች እንካüን ቢመጡ ተወዳዳሪና አሸናፊ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን ይሰጣሉ፡፡››ዶክተር ጌትነት በጋሻው፡፡

ከደንበኞች ከተሠበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ላይ የሚከፈለው ወለድ ከዋጋ ንረት በላይ መሆን አለበት!!!

የካቲት 22 ቀን 2009 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ‹‹ በኢትዩጵያ ባንኮች የሚከፍሉት የወለድ ምጣኔ ከዋጋ ግሽበት መጠን አነስተኛ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ የወለድ መጠን አምስት በመቶ ሲሆን የዋጋ ግሽበት መጠኑ በአማካይ 7 እስከ 9 በመቶ ደርሶል፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ የባንክ ደንበኛ ገንዘቡን በባንክ ሲያስቀምጥ ወለዱ ከግሽበቱ ያነሰ በመሆኑ የሚያገኘው ወለድ በግሽቱ ይወሰድበታል ማለት ነው፡፡  በዚህ የተነሳ አንድ ሰው ገንዘቡን ባንክ የሚያስቀምጠው ወለድ አገኛለሁ ብሎ ሳይሆን ሌባ እንዳይሰርቅብኝ ብሎ በመስጋቱ ነው ወደሚል ድምዳሜ እንደሚያደርስ የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ምሁራኑ የወለድ ምጣኔ ከግሽበት ማነስ የለበትም ባይ ናቸው፡፡ በተለይ የቁጠባ መጠንን ለማሳዳግ የባንኮች የወለድ መጠን ከግሽበቱ በላይ መሆን አለበት የሚለው የኢኮኖሚ ምሁራን ምክረ ሃሳብ ነው፡፡››

አቶ ክብሩ ገና ‹‹በአገራችን ግሽበቱ በአማካይ ከ8 እሰከ 10 በመቶ መካከል ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የወለድ ምጣኔው አምስት በመቶ ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ልዩነት በመኖሩ ሰው ገንዘቡን ባንክ ከማስቀመት ይልቅ የተለያዩ ንብረቶችን (መሬት፣ ቤት፣ መኪና) ግዥ ላይ ሲያውለው ይታያል፡፡ ምክንቱም የቤትና መሰል ንብረቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ስለሆነ በእነዚህ ንብረቶች ላይ ገንዘቡን ማፍሰሱ ግሽበቱን ይከላከልለታል፤ብሩም የመግዛት አቅም ዋጋ እንዳያጣ ያደርግለታል፡፡… ወለድ ከግሽበት በታች መሆኑ ቁጠባን አይጎዳም የሚለው በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚታይ አይደለም፡፡ ሌሎች ጉዳዩችም አሉት፡፡ ለምሳሌ በኢትዩጵያ ትልቅ ግሽበት ያለው ንብረት ላይ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የቤት ዋጋ በየግዜው እያሻቀበ  ነው፡፡ ስለዚህ ባለገንዘቡ ብዙ ጊዜ ገንዘቡን ግሽበቱን ሊያሸንፍ በሚችልበት መልኩ ሊያውለው ይችላል፡፡ ይህም በዓይነት የተደረገ ቁጠባ ነው፡፡…. በአንጻሩ ከባንክ ብድር የሚወስድ ሰው ይጠቀማል፡፡ ምክንያቱም ንብረት ላይ በማዋል የገንዘቡን የመግዛት ዋጋ ከፍ ማድረግ ይችላልና፡፡ ለምሳሌ ቤት ገዝቶ የሚያከራይ ሰው የቤት ኪራዩን ከፍ በማድረግ ሊጠቀም ይችልል፡፡ ንብረት የሚሸጡ ሰዎችም ከግሽበቱ እኩል ወይም በላይ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን ይችልሉ፡፡…. ገበያው ግሽበት በሚያመጣ ፖሊሲ ላይ የተቀመጠ ከሆነ ግሽበቱ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ የመንግሥት ኃላፊነት ግሽበቱ መስመር እንዲይዝና ወደ ታች እንዲወርድ ማድረግ ይሆናል፡፡›› ይላሉ አቶ ክብሩ ገና፡፡ እንደ ኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ መረጃ መሠረት፣ በቀላሉ ለማስረዳት በ2007 እኤአ የዋጋ ግሽበት 16.9  የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 11.9 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ያሰቀመጠ ደንበኛ 11.9 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡ በ2008 እኤአ የዋጋ ግሽበት 30.0  የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 25.0 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ያሰቀመጠ ደንበኛ 25 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡  በ2009 እኤአ የዋጋ ግሽበት 23.0  የተቀማጪ ገንዘብ ምጣኔ 5 በመቶ ሲሆን ልዩነቱ 18.0 ነው ይህ ማለት ከእያንዳንዱ 100 ብር ያሰቀመጠ ደንበኛ 18.0 ብር ከተቀማጭ ገንዘቡ ያጣል ማለት ነው፡፡

የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን፣በ1985 ዓ/ም 41.4 በመቶ ወደ በ2009 ዓ/ም 94 በመቶ እያሽቋለቋለ መሆኑን ከሠንጠረዡ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ የወለድ መጠንና የተቀማጭ ገንዘቡ ላይ የሚገኘውን የወለድ ምጣኔ እንዳማይሰላ እንገምት፡፡

በ1984 ዓ/ም 100,000 ብር በባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ያስቀመጠ ግለሰብ በዛ ዓመተምህረት ባለ የውጭ ምንዛሪ ተመን 48,309 የአሜሪካን ዶለር ነበር፡፡ በ2009 ዓ/ም መቶው ሽህ ብር በውጭ ምንዛሪ 4,305 ዶላር መሆኑ  ፍንትው ብሎ ይታያል፡፡ ከ1984ዓ/ም እስከ 2009ዓ/ም የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን እንዴት እየረከሠ እንደመጣ ያሳያል፡፡ የብር ዋጋ በየግዜው እየወደቀ እንደመጣና የብር የመግዛት አቅም ከዓመት ዓመት እየተሸመደመደ መሄዱን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በባንክ ተቀማጭ ገንዘብ የሚያስቀምጡ ግለሠቦች በአንድ በኩል በውጭ ምንዛሪ ተመን መቀነስና በዋጋ ግሽበት የተነሳ ባንክ ያስቀመጡት ገንዘብ እየወረደና እየቀነሰ መምጣቱን መገንዘቡ ይቻላል፡፡በተመሳሳይ የባንክ ኢንቨስተሮች ማለትም የኢትዩጵያ ባንኮች ባለአክሲዩኞች የገንዘብ ኃብታቸው እየቀነሰ መምጣቱን አስተውለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በኢትዩጵያ የሚገኙ ባንኮች በሙሉ ገንዘባቸውን ሰማይ ጠቀስ ፎቅ በመገንባት ሥራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ የፎቆችና ቪላ ቤቶች መገንባትና መሥራት ማለትም ተቀማጭ ገንዘብን ወደ ተለያዩ ንብረቶች መቀየር በአሁኑ ጊዜ ባለው የንብረቶች ዋጋ ከፍተኛ በመሆኑ የዋጋ ግሸበቱን ለመከላከልና ባንክ ተቀማጭ የሆነውን ብር የመግዛት አቅም ዋጋ እንዳያጣ ያደርግላቸዋል፡፡

ዓመት

ኢትዩ

  ዩኤስ  ኢትዩ

ዶላር = ብር

የውጭ መንዛሪ

በመቶኛ

ተቀማጭ ገንዘብ

በብር

ተቀማጭ ገንዘብ

በዶላር

1984 2.07 100,000 48,309
1985 5.00 41.4 100,000 20,000
1988 5.88 85.0 100,000 17,007
1993 8.15 72.1 100,000 12,270
1998 8.65 94.2 100,000 11,561
1999 8.39 103.0 100,000 11,919
2000 8.93 94.0 100,000 11,198
2001 9.67 92.3 100,000 10,341
2002 12.39 78.0 100,000 8,071
2003 13.33 93.0 100,000 7,501
2004 14.06 95.0 100,000 7,112
2005 18.65 75.4 100,000 5,362
2006 19.65 95.0 100,000 5,089
2007 19.85 99.0 100,000 5,038
2008 21.83 90.9 100,000 4,380
2009 23.23 94.0 100,000 4,305

በአጠቃላይ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን፣ያሽቆለቆለው በዘጠና አራት በመቶ ነው፣እንዲሁ እየቀነሰ ከመጣ በሃገሪቱ የፎቆችና የቪላ ቤቶች ዋጋም መውደቁ ብሎም የመሬት ዋጋ ጥንቡን መጣሉ የማይቀር ክስተት ይሆናል፡፡ በሃገሪቱ መሬት የመንግስት ነው፣ህዝብ ባልመከረበት የተጫነበት የወያኔ መንግሥት የመሬት ፖሊሲ ምክንያት የመሬት አቅርቦቱን የያዘው መንግሥት በዪዜው ትንሽ መሬት በጨረታ አቅርቦ እየሸጠ ለመጠቀም ችሎል፡፡ ይህ አርቴፊሻል የመሬት እጥረት በመፍጠር መሬት ፈላጊውን ኢንቨስተር ሻሞ የሚያጫውተው የወያኔ መንግሥት ከትንሽ ግዜ በኃላ የመሬት ጫረታ በኢንቨስተሮች አለመሳተፍና መቀነስ ወያኔ የሚሸጠው መሬት ፈላጊ ያጣል፡፡  በአዲስአበባ ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት 355 ሽህ ብር የሊዝ መጫረቻ ዋጋ መቅረቡ አመላካች፣ የኢኮኖሚ ውድቀት መሆኑንና የብራችን እሴት  ወደ ወረቀትነት  መቀየርን እንደሚያሳይ የምጣኔ ኃብት ጠበብት ይገልፃሉ፡፡ ወያኔ የህዝብ መሬትን እየሸጠ ለመቀጠል ቢያልምም ህዝቡ በሚያደርገው ህዝባዊ እንቢተኛነትና ተጋድሎ ንብረታቸውን ያጡ ኢንቨስተሮች መሬት በጨረታ ለመግዛት ቀርቶ በነፃ ቢሠጣቸው ዋስትና ስለሌላቸው መዋለ-ንዋያቸውን አያፈሱም፡፡ በ2010 ዓ/ም እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር የመሬት አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም መንግሥት ሰራሽ የመሬት ፖሊሲ፣ በውጭ ምንዛሪ ተመን መቀነስና በዋጋ ግሽበት የተነሳ የፎቆች፣ የቤቶችና የመሬት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆላቸው አይቀርም፡፡ ሃገሪቱ ያላት ሃብት ከግዜ ወደ ግዜ እየመነመነ፣ ወደ ባህር ማዶ  የውጭ ምንዛሪያችን እየኮበለለ፣የገንዘባችን የመግዛት አቅም እየቀነሰ መምጣትን ያሳያል፡፡

 

እንደ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት በ2009 ዓ/ም በኢትዩጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር 9.4 በመቶ የነበረው፣ በነሀሴ ወር የዋጋ ግሽበቱ 10.4 በመቶ በምግብ ነክ ፍጆታዎች ላይ መሆኑ ተገልጾል፡፡ እንዲሁም ምግብ ነክ ባልሆኑ ፍጆታዎች ላይ የ7.1 በመቶ ጭማሪ ተከስቶል፡፡ በዚህም ምክንያት በአገራችን ግሽበቱ በአማካይ ከ8 እሰከ 10 በመቶ መካከል ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የወለድ ምጣኔው አምስት በመቶ ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ልዩነት በመኖሩ ሰው ገንዘቡን ባንክ ከማስቀመት ይልቅ የተለያዩ ንብረቶችን (መሬት፣ ቤት፣ መኪና) ግዥ ላይ ሲያውለው ይታያል፡፡ ለዚህ ነው ባለኃብቶችና በሃገሪቱ የሚገኙ ባንኮች የዋና ቢሮ የፎቅ ግንባታና የቅርንጫፍ ባንኮች ሥራ ላይ ተጠምደው የሚገኙት፡፡

 

ዶክተር ሰዒድ ኑሩ ‹‹ አሁን ያለውን የዕርዳታና የብድር አሰጣጥ አዝማሚያ ብዙም ተስፋ ባናደርግበት መልካም ነው›› በሚል ርዕስ ግንቦት 27 ቀን 2009 ዓ/ም ዶክተር ሰዒድ ኑሩ የኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማሕበር የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ በኢትዩጵያ የተመደበው በጀት የመግዛት አቅሙ ምን ያህል ነው፣ ምን ያህል የማስፈፀም አቅም አለው ለሚለው የሰጡት ምላሽ እንዲህ ነበር፡፡ ‹‹የዛሬውን በጀት በሚሊኒየም ከነበረው ዋጋ ጋር ብታሰላው ትልቅ አይደለም፡፡ የሚሊኒየሙ በጀት በ2000ዓ/ም  43.9 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ በ2010ዓ/ም  የአሁኑ በጀት 320.8 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ አሁን የተያዘው 320.8 ቢሊዩን ብር በጀት በ2000ዓ/ም በነበረው ዋጋ 110 ቢሊዩን ብር ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያለው በዋጋ ንረት የመጣ ነው፡፡ በአማካይ ዋጋ በሦስት እጥፍ አድጎል፡፡ በዚህ ወቅት በመቶ ብር ትገዛ የነበረው እቃ አሁን ሦስት መቶ ብር ነው እንደ ማለት ነው፡፡ ከመፈጸም አንፃር ፣ሥራ ከመስራት አንፃር የምታየው የገበያ ዋጋን የሚያንፀባርቅ አይደለም፡፡ መነሻችን ይሄ ነው፡፡በ2000ዓ/ም በሚሊኒየም ወቅት 43.9 ቢሊዩን ብር በጀት ሲቀርብ ጉድ ተብሎል፡፡ አሁን 320.8 ቢሊዩን ብር ደርሶል አሁን ይሄም ትልቅ ይመስላል፡፡ ነገር ግን በ650 በመቶ ዕድገት አለው፤ነገር ግን በትክክለኛው ዋጋ ብታሰላው 155 በመቶ ብቻ ነው ሥራ የመፈፀም አቅሙ፡፡ ሌላው የተቀረው የዋጋ ንረት ነው፡፡›› ዶክተር ሰዒድ ኑሩ::

 

 

የቻይና ድራጎኖች የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ዘርፎች ተቆጣጥረዋል!!!

የቻይና ኮምኒስት ፓርቲና ህወኃት ፓርቲ አንባገነናዊ አገዛዝ ይወገድ!!!

ቻይና ድራጎኖች ሳይወቁ ወያኔ አይወድቅም!!!

ቻይና ያበድራል! ወያኔ ይሰርቃል!! ህዝብ ዕዳውን ይከፍላል!!!

‹‹በኢትዩጵያ መንግሥታዊና የግል ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ በ2010ዓ/ም ይከሰታል!!!››

2010 ዓ/ም መልካም አዲስ አመት ይሁንልን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.