የ፪ሺህ፲ ዓመተ ምሕረት አዲስ ዘመን ቃለ ምዕዳን! (ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ። አሜን ።
በሀገራችን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምትገኙ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ፥ ማኅበረ ካህናት ፥ ምእመናንና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ! እግዚአብሔር በቸርነቱ እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ ፪ሺህ፲ ዓመተ ምሕረት አደረሳችሁ ።

«ለታሰሩትም መፈታትን ፥ ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ ፣ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ ፥ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል» (ሉቃ 4 ፥ 19) ።

ዓመተ ምሕረት ማለት የይቅርታ ፣ የምሕረትና የትድግና ዓመት ፥ ዘመን ፥ ወቅት ማለት ነው ። ዓመተ ምሕረት የዓመተ ፍዳ ፥ የዓመተ ኩነኔ ተቃራኒ ነው ። በቤተ ክርስቲያናችን ከክርስቶስ ልደት በፊት ያለው ዘመን ዓመተ ኩነኔ ዓመተ ፍዳ እየተባለ ይጠራል ። ምክንያቱም ሰው የፈጣሪውን ትእዛዝ ተላልፎ ከፈጣሪው ጋር በጣላቱ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ ተፈርዶበት ስለ ነበር ነው ። በርደተ መቃብር ላይም ርደተ ሲኦል ተወስኖበት ነበር ። በመሆኑም ይህ ከባድ ዘመን ሰው በሥጋውም በነፍሱም የተቀጣበት ዘመን ስለ ሆነ ዓመተ ኩነኔ ይባላል ። የእግዚአብሔር ፍርድም ለዲያብሎስ ባርነት ስለ ዳረገው ሥጋውን በመቃብር ተቆራኝቶ ፣ ነፍሱን በሲኦል ረግጦ ይገዛው ፣ ያሰቃየውም ስለ ነበር «ዓመተ ፍዳ» ይባላል ።

[ሙሉውን  በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ]

 

[gview file=”https://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/09/HH-Patriarch-Ethiopian-new-year-2010-message.pdf”]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.