የአምባገነን ፍሽስት ወያኔ ምርጫ የማጭበርበር ልምዱን ዛሬም በቅማንትና አማራ ህዝብን ለመለያየት እያዋለው ነው፡፦—ሰሎሞን ይመኑ

የቅማንት የሕዝበ ዉሳኔ እሁድ መስከረም 7 በአማራ ክልል ለቅማንት ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ሕዝበ ዉሳኔ ለማካሄድ የድምፅ ሰጭዎች ምዝገባ ከነሐሴ 29 ቀን 2009 ዓም እስከ መስከረም 3 ቀን 2010 ድረስ የተካሄደ ሲሆን ዋና አላማውም ሁለቱን በጋራ አብሮ የኖረ ህዝብ እርስ በእርሱ በጠላትነት እንዲተያይ የተከዜ ማዶ ፍሽስቶች የሰይጣን መምህሮች የደገሱት ሌላ የዘር ፍጅት እንዲያመጣ የታሰበ እቅድ ነው፡፡ የዚህ አይነት ምርጫ በ1997 ዓ ም በኦሮምያ እና በሶማሊያ ክልል ሆን ብሎ በማድረግ እና በጋራ የሚኖረውን ህዝብ የድንበር አጥር በአንድ ሃገር ውስጥ በማስመር ሰሞኑን ለሞቱት ወንድሞቻችን አይነት ድግስ አሁንም የተከዜ ማዶው ፍሽስት መደገሱን ህዝባችን ሊያውቅ ይገባል፡፡

ማሳያ

********

1.በወያኔ ህገ አራዊት ህገ መንግስት አንቀጽ 62(3)መሰረት የራስን እድል በራስ የመወሰን እና የማስተዳደር «ጥያቄዎች ሲነሱ» በህገ መንግስቱ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል ይላል፡፡ ነገር ግን ይሄ በ 12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግበት ለምርጫ ቦርድ ተእዛዝ የተሰጠው በተንኮል ማእከሉ የፌድሬሽን ምክር ቤት አነሳሽነት እንጅ በህዝቡ ጥያቄ አይደለም፡፡ የበለጠ የዚህ ማረጋገጫም ወያኔ ምርጫ አደርግበታለሁ ካለው 12 ቀበሌ ውስጥ 8 ቀበሌዎች ላይ ብቻ መደረጉ እና 4ቀብሌዎች ላይ ተመዝጋቢ መጥፍቱን የምርጫ ቦርድ ለጀርመን ራዲዮ ትላንት መስከረም 6 የገለጹ ሲሆን ይህ የሚያሳየን ጥያቄው ከሁሉም ቀበሌዎች ከህዝቡ የመጣ ቢሆን ኑሮ አሁን ለምርጫ ተመዝጋቢ ባልጠፋ ነበር፡፡ ከዚህ መረዳት እንደምንችለው ወያኔ የተንኮልመቅዱ በትንሹም ባይሳካለትም በ 8ቱ ቀበሌዎች ግን 23000(ሃያ ሶስት ሽህ መራጮች) እንደተመዘገቡ ለዶቸበሌ ገልጿል፡፡

2.በተሻሻለው የአማራ ክልል ህገ መንግስት አንቀጽ 39(5)ም ሆነ በፌደራሉ ህገ አራዊት ተመሳሳይ አንቀጽ  በራስ የማስተዳደሩ ጥያቄ ወደ ምርጫ የሚቀርበው መጀመሪያ በክልሉ ምክርቤት ሁለት ሶስተኛ ድምጽ ተቀባይነት ማግኘት ሲገባው እንደሆነ ቢገልጽም ይህን የራሱን ህገ አራውት ያለከበረበት ምክንያት ባስቸኳይ ያሰበውን ተንኮል ለማሳካት ያቀደ ነው፡፡

3.ከዚህ በፊት የተከዜ ማዶ ነብሰ በላዎች 42 ቀበሌ በቅማንት አስተዳደር ሲያካሂዱ ለምን ህዝበ ውሳኔ ሳይደረግ አሁን እነዚህን 12 ቀበሌዎች ለማካለል ህዝበ ውሳኔ አስፈለገው የሚሉትን ጥያቄዎች ስናነሳ ዋናው ነገር ይህ ዘዴ ህዝቡን በእያንዳንዱ ሂደት በመከፍፈል እና እርስ በእርሱ በጠላትነት እንዲፈረጅ በማድረግ ግጭት ማድረግና የምርጫውን ውጤትም ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መንገድ መቀልበስ እንደሆነ ውስጥ ውስጡን የክልሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡

በጣም የሚገርመው ደግሞ ፍሽስት ወያኔ ምርጫን በማጭበርበር የተካኑ የወያኔ ቀኝ እጆችን በየክልሉ ያሉትን ይራሱን ታዋቂ ኮሮጆ ገልባጮች ከኦሮሚያ፣ ከቤንሻንጉል፣ ከአድስ አበባና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተወጣጡ ልምድ ያላቸዉ የምርጫ ኮሮጆ ቀያሪዎች በቦታዉ እንደሚገኙ አቶ ተስፋለም አባይ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር  ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይህ የወያኔ ኮሮጆ ቀያሪ የማፊያው ቡድን ስርቆቱ እንዳይታወቅበትም ምርጫዉንም ለመታዘብም ሆነ ተሳትፎ ለማድረግ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ያገባኛል የሚሉ አካላት ጥያቄ ቢያቀርቡም እንደተከለከሉ የመኢአድ አመራሮች ገልጸዋል፡፡

ያም ሆነ ይህ ጀግናው የአማራና የቅማንት ህዝብ የፍሽስት ወያኔን ግባአተ መሬት ለማፍጠን የሚያደርጉትን ትግል ለማኮላሸት የተጠነሰሰ ሴራ መሆኑን አውቆ ምርጫውን እስከመጨረሻው እንዲከታተል እና ከተከዜ ማዶ በብር ተገዝተው የመጡ መራጮችንም በየቦታው በመለየት ህዝቡ የራሱን አማራጭ በመውሰድ የፍሽስት ወያኔን ሴራ እንዲያከሽፍና ነገን ከወያኔ ሴራ በተሻለ መንገድ በማየት የወያኔን ሴራ አፍቃሪ ቅልብ ኮሚቴዎችንም የሚያሳፍር ድል በመምታት ከጥቅም በሽታቸው ልናባንናቸው ይገባል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.