የድምጽ ቆጠራ ዉጤት  ነገ ነው የሚነገረው ተባለ #ግርማ_ካሳ

 

ንጉሱ ጥላሁን

የአማራ ኮሚኒኬንሽን ጽ/ቤት  ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን “ በሰሜን ጎንደር ዞን 8 ቀበሌዎች ዛሬ ሠላማዊነቱን ጠብቆ ከማለዳው12:00 ሰዓት ጀምሮ ሲካሄድ የዋለው የህዝበ ውሳኔ ምርጫ 12:00 ሰዓት ማታ መጠናቀቁ ይፋ ተደርጓል፡፡ ጊዚያዊ የድምጽ ቆጠራው ውጤት ነገ ማለዳ 1:00 ሰዓት በቀበሌ ደረጃ ይገለጻል፡፡ ህብረተሰቡም ውጤቱን በፀጋ ለመቀበል ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡” የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

ለአቶ ንጉሱ የሚከተለውን አስተያየት ለጥፊያለሁ።  ግልጽ የሆኑ የመርህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ነው ያቀረብኩላቸው፡

——————-

አቶ   በሕጉ መሰረት ታዛቢዎች አረጋግጠው የምርጫው ዉጤት በምርጫው ጣቢያ መለጠፍ አልነበረበትም ወይ ?  ዉጤቱ ነገ የሚነገር ከሆነ ምን ማርረጋገጫ አለ ፣ ህዝቡ ከሄደ፣ ታዛቢዎች ከተበተኑ በኋላ የምርጫው ዉጤት ስላለመቀልበሱ ?

በአንዳንድ ቦታዎች ውጤት በይፋ በምርጫ ቦርድ ገና ባይረጋገጥም፣ ሕዝቡ በነቂስ ቅማንቶችም ሳይቀሩ ከሰሜን ጎንደር ጋር መቀጠል እንደፈለጉ ነው እየተዘገበ ያለው። እዚህ ጋር ልብ ይበሉ ብዙ ቅማንቶች ሳይቀሩ የሰሜን ጎንደር አክል ሆነው መቀጠል እንደፈለጉ ነው ለማወቅ የተቻለው። ታዲያ “ቅማንቶች በብዛት የሚኖሩባቸው ነው” በሚል  የቅማንት አስተዳደር እንዲሆኑ በተደረጉ 61 ቀበሌዎች  ያለ ህዝብ ፍላጎት ዴሞክራሲያዊ ባለሆነ መንገድ ዉሳኔ ከመወሰን፣ ለምን ልክ እንደ ስምንቱ ቀበሌዎች ሕዝቡ እንዲወስን አልተደረገም ? ለምን ለዴሞክራሲያዊ አሰራር ፣ ለመርህ ቅድሚያ አልተሰጠም ? ለምን ቅማንቶች የሚኖሩበት አካባቢ ነው በሚል  ብቻ የቅማንቶች የራሳቸው አዎንታና ፍላጎት ሳይታይ፣  ድምጽ ሳይሰጡ  የቅማንት አስተዳደር ይፈጠራል ?  ቅማንቶች በ61 ቀበሌዎች ከሰሜን ጎንደር መለየት ከፈለጉ ያ መብታቸው ነው።፡  ግን ለምን ጥቂቶች ይወስኑላቸዋል ?  ያውም እንደሚባለው ጽ/ቤታቸውን መቀሌ ያደረጉ ራሳቸውን የቅምናት ኮሚቴ ብለው የሚጠሩ ጥቂት ግለሰቦች !!!!!

እዚህ ላይ ምን ይላሉ ? የክልሉ መንግስትስ ለምን ህዝብ ዉሳኔ በሁሉም ቦታዎች እንዲደረግ አላደረገም ? ይህ ጉዳይ ትልቅ ጉዳይ ነው። ቢታሰብበት ጥሩ ነው።፡ በ61 ቀበሌዎች የወሰነዉን ዉሳኔ ሽሮ የክልሉ መንግስት ህዝብ እንዲወስ ማድረግ አለበት።

የአማራው ክልል በስምንቱ ቀበሌዎች የሕዥብ ፍልጎት እንዲታየ ማድረጉ ዴሞርካሲያዊነቱ እንደተጠበቀ፣ ብ፤አዴን እንደ ድርጅት ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ ራሳቸውን አማራ ብለው የሚጠሩ ዜጎች ልክ እንደ ቅማንቶች ራሳቸውን ማስተዳደር ከፈለጉ ለምን ተመሳሳይ እድል አይሰጣቸው ? ለምሳሌ አዳማን ፣ ጂማን ፣ ወልቃይት፣ ቆቦ የመሳሰሉይትን ማየት ይቻላል። እነዚህ አካባቢዎች አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ ቢሆንም የሕዝቡ መብት ተረግጦ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። አሁን በአዳማ ወደ አምሳ በመቶ ራሱን አማራ ብልኦ የሚጠራ ማህበረሰብ ነው። ወደ 75% አማርኛ ተናጋሪ ነው። ግን በአዳማ ጽ/ቤት ሲኬድ፣ በቀበሌዎች የሥራ ቋንቋ በአፋን ኦሮሞ ብቻነው። ለምን ብአዴን ይሄ እንዲስተካከል አይሰራም ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.