የህወሃት መራሹ መንግስት ዘር ተኮር ዓላማ ጎንደር ላይ ተሸነፈ – በወንድወሰን ተክሉ

የህወሃት መራሹ መንግስት ዘር ተኮር ዓላማ ጎንደር ላይ ተሸነፈ - በወንድወሰን ተክሉ 1በሰሜን ጎንደር የቅማንት የማንነት ጥያቄ የሚመልስ ነው የተባለለት ሕዝበ ውሳኔ መስከረም 07ቀን 2010 በሰጠው ድምጽ ጎንደር አማራነታቸውን በመምረጥ የታሰበውን ሴራ ማክሸፋቸው ምርጫው ከተካሄደባቸው ቀበሌዎች ካገኘነው መረጃ መረዳት ተችላል።

እሁድ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ አጠቃላይ ምርጫውና እጤቱ የታወቀ መሆኑን በምርጫው በታዛቢነት ተሳታፊ ከሆኑት ማወቅ የተቻለ ሆኖ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ እውጃው በይደር ለሰኞ እንዲቆይ መደረጉን ድምጽ ሰጪው ህዝብ እንዳልወደደው መረዳት ተችላል።

በፌዴራሉ መንግስት በ12 የሰሜን ምእራብ ጎንደር ቀበሌዎች እንዲካሄድ የተወሰነው እና በህዝቡ የጎንደርን አንድ ህዝብ ለመከፋፈል ዓላማ ያለው የተባለው ህዝበ ውሳኔ ገና ከመነሻው በ4ቱ ቀበሌ እንደማይካሄድ ህዝቡ በማገዱ በስምንት ቀበሌዎች ብቻ እሁድ ህዝቡ ድምጽ እንዲሰጥ በመደረጉ አብሮነትን በመምረጥ የስርዓቱን ዓላማ ለማፍረስ ተችላል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የምርጫው ውጤት በህዝብ አሸናፊነት ተደምድሞ ይፋዊ ውጤቱን ሰኞ ይገለጻል የሚለውን የመንግስት መግለጫ ማንም በቅንነት እንዳልተቀበለው ከስፍራው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክት ሲሆን ህዝቡ ድምጹን ለመጠበቅ በንቃት ወጥሮ መያዙንም ማወቅ ተችላል።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ ግብረ ሃይል በህወሃት ፓርቲ መቀመጫውን በመቀሌ አድርጎ የጎንደርን እና አማራውን ከፋፍሎ በማዳካም መሬቱን እንደ ወልቃይትና ጸገዴ ወደ ትግራይ ለማጠቃለል ታስቦ የተመሰረተ ሴራ ነው ሲል የጎንደር ሕዝብ ደጋግሞ ሲናገር እንደነበር ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.