በመንገድና በልማት መቀሌና አዲስ አበባ አንደኛ፣ጎንደርና አማራ መጨረሻ ተባሉ – በወንድወሰን ተክሉ

በኢትዮጵያ ከ2006 እስከ 2016 ለአስር ዓመት በተካሄደ የመንግድ ግንባታ ትግራይና አዲስ አበባ የአንደኝነቱን ደረጃ ሲጋሩ የአማራው ክልል ደግሞ በአንጻራዊነት በመጨረሻ ረድፍ ላይ መሆናቸውን የዓለም ባንክ በአመታዊ የሀገራት መሰረተ ልማት ሪፓርቱ አስታወቀ።

እንደ የዓለም ባንክ ሪፖርት ዘገባ ለሊት የሳተላይት እገዛን በመጠቀም በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ደምቀው የሚታዩትን በደማቅ ቀለም በመለየት ቻርት ላይ ያመላከተ ሲሆን የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ከተሞች ለሊት መንገዶቻ በተንቦገቦገ መብራት መሸፈኑን ገልጾ ከሁሉም ክልሎች የበለጠ ጨለማ ከተማ የሆነችው ጎንደር እንደሆነች አመላክታል።

ከትግራይ ሌላ አዲስ አበባና ተጎራባች የኦሮሚያ ከተሞች የውስጥ ለውስጥ መጋቢ መንገዶች ባለቤት በመሆን ሲከተሉ በትግራይ ግን ከመቀሌ ሌላ ገጠራማው ክልል ከየትኛውም ከተማና መንደር ጋር የሚያገናኝ መጋቢ መንገዶች በጥራትና በብዛት በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ መያዛን ሪፖርቱ ይገልጻል።

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት አወቃቀር ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሀብት፣የስልጣን፣የትምህርትና የጤና ክፍፍል እየተካሄደ ነው በማለት ዜጎች ለዓመታት ጥያቄ ቢያቀርቡም ገዢው ፓርቲ ሃሳቡን ባለመቀበልና ፍትሃዊ ክፍፍል ነው የማደርገው በማለት በአድሎዓዊ አሰራሩ እንደገፋበት ይታወቃል።

እንደ የዓለም ባንክ ሪፖርት ላለፉት አስር ዓመታት በኢኮኖሚያዊ እድገት ታላቅ እምረታ ያመጡትን የትግራይ ክልል፣የአዲስ አበባን እና የኦሮሚያን ክልሎች በቅደም ተከተላቸው ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት የተካሄደባቸው ሲል ከገለጸ በሃላ ሁለገብ የሆነ የውስጥ ለውስጥ አገናኝ መጋቢ መንገዶች ባለቤት ለመሆን የቻሉት ከዚህ አንጻር ነው ሲል ገልጾ ከሁሉ ክልሎች ደግሞ የአማራው ክልል በመጨረሻነቱ የመጀመሪያውን የያዘ ክልል ነው ሲል ገልጾታል።
ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ላለፉት አስር ዓመታት ውስጥ በአማራው ክልል 57ግዙፍ ኢንደስትሪዎች ግንባታ መሰረተ ድንጋያቸው ተተክሎ ለመጠናቀቅ ሳይበቁ ሳር እንደበቀለባቸው የተገለጸ ሲሆን በአንጻሩም በትግራይ ክልል በተገነቡ 45 ግዙፍ ኢንደስትሪዎች ከግማሽ ሚሊዮን በለይ ለሆኑ ለክልሉ ተወላጆች ብቻ የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ታውቃል።

የአማራው ክልል ነዋሪዎች አንደበት ተደጋግሞ ሲገለጽ የተሰማው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ክልሉን ክፉኛ መጨቆኑን እና የክልሉንም የተፈጥሮ ሀብት መሬት፣ቅርስና ታሪካዊ ስፍራዎችን ያለህዝብ ፍቃድ ወደ ትግራይ የማካለል ተግባራትን ሲያጋልጥ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን የዓለም ባንክ ሪፖርትም ይህንኑ የህዝቡን አቤቱታ እውነትነት የሚያረጋግጥ ሆኖ መገኘቱን ተወላጆቹ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል በኢትዮጵያ ካሉት 11 ክልላዊ መስተዳድሮች ውስጥ በተፈጥሮ ሀብቱና በህዝብ ብዛቱ ከኦሮሚያ ቀጥሎ በሁለተኛነት ደረጃ ሆኖ ሳለ በመሰረተ ልማት፣በሀብት ክምችትና በመሰል ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከሁሉም አንሶ በመጨረሻ ረድፍ ላይ መገኘቱ ብዙዎቹን የክልሉን ተወላጆች እንዳስቆጣ መረዳት ተችላል።

የዓለም ባንክ በሪፖርቱ የሀገሪቱን መንገድ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ፍሰት/ኢንቨስትመንት/ የስራ እድል፣የመብራት አቅርቦት፣ህክምና፣የት/ት ስርጭት ሽፋን እና ወዘተ ያካተተ ሪፓርት ሲሆን ትግራይና መቀሌ በሁሉም መስክ ከአፍሪካ መዲና ከተባለችዋ ዋና ከተማችን አዲስ አበባ ጋር አንደኝነትን ተጋርታ ተገኝታለች።

በባለፈው ሀምሌ 28ቀን 2010 የተነሳው የአስቸካይ ግዜ አዋጅ ስር የአማራው ክልል ፖሊስ ቢሮ በክልሉ ውስጥ ከ66ሺህ በላይ እስረኞችን የክልሉ መስተዳድር መመገብ አቅቶታል ብሎ መግለጹ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.