የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ በደ/ አፍሪካ የቀዶ ጥገናውን በተሳካ መልኩ አደረገ!

” በጣም ደህና ነኝ፤ ጌታነህ ከበደ አመሰግናለው”
-ተመስገን ተክሌ

የቀድሞ የደደቢት ፊት አውራሪ በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአገሪቱ ሪከርድ 65,000 ብር ሁለተኛው ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ፤ የአዋሳ ከነማው ተመስገን ተክሌ የጉልበት ላይ ቀዶ ጥገናውን ትላንት በደቡብ አፍሪካ በተሳካ መልኩ አከናውናል።

ኢትዮ ኪክ ከደቡብ አፍሪካ ከተጨዋቹ ጋር ዛሬ በስልክ ቆይታ አድርጋለች ። እንድታነቡት በአክብሮት እጋብዛለው።

ኢትዮኪክ:- እንዴት ነበር የትላንቱ ኦፕራስዮን ? በአሁኑ ሰአት ተመስገን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ተመስገን:- እግዚሐብሔር የተመሰገነ ይሁን። ትላንት እክምናዪ በጥሩ አልፋል፤ ሁለት ሰአት ተኩል የፈጀ ነበር። እመሙ ግራ ጉልበቴ ላይ ስጫወት በጣም ስሜት ነበረው። እዚህ ስፔሻሊስት ዶክተሮች በተሳካ መልኩ ኦፕራሲዎኑን አድርገውልኛል። ዶክተሩ እንዳለኝ ጉልበቴ ካለው ጉዳት በተጨማሪም ሀምስትሪግም ተያይዞ እመሙ ትንሽ ስሜቱን አጠንክሮታል ብሎኛል። በአሁን ሰአት በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ እግዚሐብር ይመስገን ከሆስፒታል ወጥቼ እዚህ ዘመዶቼ እና ጓደኞቼ ጋር ነው ያለሁት።

ኢትዮኪክ:- የጉልበት ጉዳቱ ብዙ ጊዜ የቆየ ነበር?

ተመስገን:- ደደቢት እያለው ተጎድቼ ነበር ነገር ግን አሳክመውኝ 2 አመት ለደደቢት ተጫውቻለው። አዋሳ ከገባሁ በኃላ ባለፈው ዓመት ላለመውረድ ባደረግነው ጥረት በጣም እያመመኝ እጫወት ነበር። በተለይ ወደ መጨረሻ አካባቢ እና በጥሎ ማለፉ ከቡና ጋር ስንጫወት አሞኝ እመሜን ችዪው ነው ጎል ያስቆጠርኩት።

ኢትዮኪክ:- ከዚህ በኃላስ ምን አይነት እክምና ነው ዶክተሮቹ የሚያደርጉልህ?

ተመስገን:- እዚህ ደቡብ አፍሪካ ምናልባት ለሁለት ወር እቆያለው ። ከሰኞ ጀምሮ ለ6 ሳምንታት ፊዚዮ-ቴራፒ በሳምንት ሁለት ቀን/ ሰኞ እና ሀሙስ ታዞልኛል። ይህም ጄሶው እንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው። ከዛ በኃላ የዶክተር ቀጠሮ አለኝ ሂደቱን የሚቌጨው ወይም ቼክአፕ ይኖረኛል። ዶክተሮቹ የግል አካላዊ እንቅስቃሴም እንዳደርግ ተነግሮኛል ስለዚህ የጂምናዝየም እንቅስቃሴም በሂደቱ ውስጥ አደርጋለው ማለት ነው።

ኢትዮኪክ:- ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ትርቃለህ ማለት ነው?

ተመስገን:- እንግዲህ አሁን ባለው ሁኔታ እክምናው በጥሩ ሁኔታ ተጀምሯል። ከዚህ በኃላ የማገገሚያ ጊዜ ምናልባት ከ3- 4 ወር ባነሰ ጊዜ እግዚሐብሔር ተጨምሮ ወደ ምወደው እግርኳስ እመለሳለው።

ኢትዮ ኪክ:- ክለብህ አዋሳ ከነማ ምን አሉህ?

ተመስገን:- ከአሰልጣኜ ውበቱ አባተ ጋር ዛሬ በመልዕክት አውርተናል። ጤንነቴ ተሽሎኝ በሳላም እንድመለስ ተመኝቶልኛል።

ኢትዮኪክ:- ምንም እንኳ የሀገሪቱ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋች ብትሆንም የእክምና ወጪውን የሸፈነልህ ይኖራል?

ተመስገን:- በርግጥ ከከፍተኛ ደሞዝተኛ ተጨዋቾች አንዱ ብሆንም የእክምና ወጪዬን እራሴው ነው የሸፈንኩት። ከዚህ እክምናዪን ጨርሼ ስመለስ ክለቤ ወጪዬን የሚመልስልኝ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው። የእክምናው ወጪ የሚያሳዪ ደረሰኞች አሉኝ።

ኢትዮኪክ:- እክምናው ምን ያህል ብር ፈጀ ?

ተመስገን:- በአጠቃላይ የአውሮፕላን ትኬቱን ጨምሮ 200 ሺ ብር አካባቢ።

ኢትዮኪክ:- በዚህ አጋጣሚ ማለት የምፈልገው ነገር ካለ?

ተመስገን:- ጌታነህ ከበደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች በጣም በጣም አመሰግነዋለው ፤ እሱ ወረቀት ልኮልኝ እክምናዪ የተሳካ አድርጎልኛል። ቤተሰቦቼን አመሰግናለው። በተጨማሪም አዳነ እና ይገረም ስላደረጉልኝ ነገር እግዚሐብሔር ይስጥልኝ።

Source – Ethio-Kickoff

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.