የመስቀል በላል ሃይማኖታዊ ነው ። በመስቀል ባኣል መንግስትም የፓርቲዎች መሪወች እጃቸው ከማስገባት እጃቸው ይታቀቡ !!! – ኣስገደ ገብረስላሴ ፣

ባገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ የክርስትና ሃይማኖት ኣማኒያን እንኳን 2010 ዓ/ም

መስቀሉ በኣል ፡በሰላምኣደረሳችሁ ኣደረሰን ።

የመስቀል በኣል በመላው ሃገራች የሚገኙ የክርስትና ኣማኒያን ለዘመናት በድምቀት እያከበሩት ኖረዋል ፣ ኣሁንም እያከበሩም ኣሉ ።
ይህ እንደዚህ እንዳለ በኣለፉ ኣመታት ግን የመስቀል በኣል የኣማኒያን በኣል የሃይማኖት መድረክ መሆኑ ቀርቶ የፓለቲከኞች የፓለቲካቸው ኣመለካከት ማስተላለፍያ ትቦዎች ነበሩ ዘንድሮ በመቀሌ ከተማ ደመቅ ያለ የክርስትና ሃይማኖት ኣማኒያን በኣል እየተከቨረ ነው ። ለዚሁ በኣል ዶምቀት የከተማው ወጣቶች ለረጅም ጊዜ በዚሁ ዘንድሮ በኣሉ በድምቀት የሚከበርበት ያለው ታሪካዊው የጮምዓ ተራራ ነጻ ሆነው እንዳያከብሩ የህወሓት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ጣልቃ እየፈጠሩ ቡዙ መሰናክሎች የፈጠሩባቸው ቢሆንም የመቀሌ ህዝብ ግን የወጣቶች ተነሳሽነት የጥንት ቅርስ ኣዳሾች ብሎ ስላኣበረታታቸው ወጣቶቹ ሳይሸማቀቁ በታሪካዊ ጮምዓ ተራራ 52 ሜትር ርዝመት ያለው ተምሳሌት የጌታችን እዬሱስ ክርስቶሰ ግማደመስቀል በማቆም የነበራቸውን ተጽእኖ በመበጣጠስ መስቀል የሃይማኖት በኣል መሆኑ ዛሬ ቀን የኢትዮጱያ ፓትሪያሪክ ቡጹእ ኣውነ ማትያስና በመቀሌ ዞን ጳጳስና ከፓትሪያሪኩ ጋር የመጡ ጳጳሳት እንዲሁም እጅግ ቡዙ ቀሳውስት እና የቅኔ የድጋ ወዘተ ዘማሪያን ፣ወደ ተራራው ሊወጣ የሚችል ከእህጻን እስከ
ኣዛውነት ፣ከመላው የሃገራችን የመጡ ኣማኒያን
ተበርኮላቸው በሰላማዊ ኣጀባ ተመርቋል ለመቀሌ ወጣቶች ለሁሉም ኃላ ቀር መሰናክሎች ሰብራችሁ እንኳን ድሉን ተጓነጸፋችሁ ።

ከላይ ያስቀመጥኩት ሓቅ እንዳለ ሆኖ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ግን
የመቀሌ ህዝብ በኡሁድ እና በሰኞ በመስቀል በኣል ጅግጅቱ የተደረገው የግማደ መስቀል ምርቃ ምንም እንኳን በኡሁዱ በኣክሱም ሆቴል የተደረገው ፓኔል የጠቂት ካድሬዎች የባኣሉ ዝግጅት የሀይማኖት መድረክ ኣቅጣጫውን ኣስተው የትሪዙም ትግራይ ዝግጅት ለማስመሰል ተጽእኖ ቢያደርጉም ፣ የባኣሉ ኣዛጋጆች የመቀሌ ወጣቶች ትልቁ ክፍሉ ካለፉት ኣመታት በገዥዎች ይፈጸም የነበረ ጥርጣሬና ያልሆነ ስም መለጠፍ እንደ ኣሸነፉ ነበር የሚያመለክተው ።

በዛሬው ቀን ግን የህወሓት መሪዎች ባለፉት ኣመታት የሁሉም የሃይማኖት በኣላት መድረክ ለፓለቲካቸው መጥመቂያ ሆኖ እንደቆዬና በለፉት ሁለት ቀናት የመቀሌ ህዝብ መድረኩ በጳጳሳትና ኣማኒያን ተይዞ በመሰንበቱ እነዚህ ሰዎች የሀይማኖት መድረካች ለስርኣታቸው መጥመቂያ ኣድርገውት የቆዩ ያህል ትተውት መሰል ብለው ነበር ።
በዛሬው ቀን ግን ቡዙ ሳይራመዱ በኣይማኖት መድረክ ይደሰኩሩት የነበረ ኣገርሽቶባቸው የዛሬው የጮምዓ የመስቀል በኣል ማጣቃለያ ኣባይ ወልዱና ደቀመዛምርቱ የሀይማኖት መድረኩ ተቆጣጥረውት ውለዋል ።
ይህ ማለት ደግሞ የመቀሌ ወጣቶችና ህዝበ ክርስትና በመጨረሻ ያዛጋጁት የሃይማኖት በኣል መድረኩ የህወሓት መሪዎች የሃይማኖት መድረኩ የፓለቲካቸው መጥመቂ መሆኑ እንዳላቋረጠ ስለገባቸው በየቤታቸው ሆነው ተቃውማቸውን ማሰማት ጀምረዋል ።
በተጨማሪም ኣንድ ኣንድ ወገኖች በመስቀሉ የሃይማኖት በኣሉ በተለይ ደግሞ ግማደመስቀሉ በማቆም ወሳኝ ሚና የተጫወቱ ግለሰዎች በክርስትያን ህዝብም ተወዳጅነት ፈጥረው የነበሩ በዛሬው ቀን ግን በጮምዓ ተራራ መስቀሉ ስር ሆነው ባደረጉት ዲስኩር ማምሻውን ግን የነበራቸው ተወዳጅነት ወርዶ በከተማው ጎደናዎችና በካፌ ፣በታክስ ውስጥ የህዝብ ትችት ሲነገርላቸው ነበር ።

በመሆኑም በኡሁዱ የፓኔሉ ውይይት የመሩት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብሪሂወት የህወሓት ማ / ኮ ነበር የኣሁኑ የህወሓት ኣማራር ታማኝ ካድሬ በፎቶ ተመልከቱት ፣ እንዲሁም ፕሮፌሰር ሙቱኩ ሀይለ ማ / ኮ ነበር በኣሁኑ ጊዜ ታማኝ ካድሬ ፣
ኣቶ ከበደ ኣማረ የትሪዙም ቢሮ ሃላፊ የነበረ ኣሁንም ታማኝ ተላኪ ካድሬ ፣
በመጨረሻም የመቀሌ ዞን ጳጳስ ቡራኬ ሰጥተዋል ።
በሰኞው በመቀሌ ወጣቶች የተተከለው መስቀል የሃገራች ፓትሪያሪክ ኣውነ ማቲያስ እነዲሁም የዞናችን ጳጳስ ቀሳውስት ከአዲስ ኣበባ የመጡ ጳጳሳት ነበሩ ።
እስከዚህ ድረስ ከፍተኛው ስራው የሀይማኖት በላይነት ያሳይ ነበር ።
የዛሬው የመጨረሻ በኣል ግን የመቀሌ ከንቲባና የሀወሓት ማ/ ኮ ዳኒኤል ኣሰፋ ።
የህወሓት ሊቀመንበር ፣የትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪ እንዲሁም የኢህኣደግ ስራ ፈጻሚ ኣባይ ወልዱ ፣ የእነዚህ ሁለቱ ኣማራር ፓለቲካዊ ንግግር ወይ ዲስኩር ለሃይማኖት በኣሉ ወደፓለቲካ ቀይሮታል ። ከነሱ ጋርም የመቀሌ ዞን ጳጳሱ ነበሩ ። በበለጠ ደግሞ ለመድረኩ የሃይማኖት መድረኩ (በኣል ) ወደ ፓለቲካ የቀየረው በመሌ ወጣቶችም ተቀባይነት የነበረው ከባኣሉ ኣዛጋጆቹ ኣንዱ ግለሰው ነበር ።
ለተጠቀሱ የፓለቲካ ባለስልጣናት በፎተው ተመልከቱ ።
ነገ የመቀሌ ዋናው ዳሜራስ ማን ይመራው ይሆን ነገ እነዬው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.