ዛሬ ኢሬቻ በዓል በጣም ሰላማዊ ነው! እንደባለፈው ዘግናኝ ተግባር አለመፈፀሙ ተመስገን ነው

የህዝቡን ሰላም የማይፈልገው “መንግስት” ነኝ ባይ ያደፈርሰዋል እንጅ! ባለፈው አመት የተፈጠረው ዘግናኝ ድርጊትን ተከትሎ በዛሬው በዓልም ህዝብ ተጨንቆ ነበር።

ኢሬቻ በሰላም ነበር የሚጠናቀቀው። ነገር ግን መንግስት ነኝ የሚለው ይህን አይፈልገውም። በሰላም በተጠናቀቁት ኢሬቻ ቀናት ተገኛታችሁዋል፣ ተገኝታችሁም አደራጃችሁ፣ ዘመራችሁ ተብለው የተቀጠቀጡ፣ የተከሰሱ ኦሮሞ ወጣቶች አውቃለሁ። ትህነግ የኢሬቻን በሰላም መከበር ብቻ ሳይሆን ኢሬቻን አይፈልገውም። የኦነግ መገናኛ መድረክ ነው ብሎ ፈርጆታል። እናም በሰላም እንዲጠናቀቅ አይፈልግም።

ዛሬም እንደባለፈው ዘግናኝ ተግባር አለመፈፀሙ ተመስገን ነው። ከዝግጅቱ ይልቅ ያስጨነቀን መጨረሻው ነው። ከዚህ መድረሳችን ግን ያሳዝናል። ሰላማዊ የሆነው በዓል ላይ ችግር ይፈጠራል ብለን በእጅጉ መፍራት ላይ ደርሰናል! ድሮ በሰላም ሲጠናቀቅ ምንም የማንለው ዛሬ እልልል እንድንል ተገደናል! እንደድሮው በሰላም እንዳይከበር ስለተደረግን ከበዓሉ በላይ በዓሉ በሰላም ተከበረ ብለን እየተደሰትን ነው። በዓሉን በስጋት አክብረን በሰላም መጠናቀቁን እናከብራለን!

የጥምቀትን ዝግጅት ከማክበር በላይ ዝግጅቱን በስጋት ጨርሰን በሰላም መጠናቀቁን በእልልታ እናከብራለን! መስቀልንና ኢሬቻን ዝግጅት ተጨንቀን አሳልፈን በሰላም መጠናቀቁን እልል ብለን እናከብራለን! ዝግጅቱ በሰላም አይጠናቀቅልልንም ብለን ሰግተን ነው! የደስታ ቀናችን፣ የሰላም፣ የምስጋና ቀናችን የስጋት አድርገውብን ነው!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.