ኦጄ ሲምፕሰን ከዘጠኝ ዓመት በሃላ ተፈታ – በወንድወሰን ተክሉ

በ2007 በተካሄደ በመሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘውና የ33ዓመት እስር ቅጣት የተፈረደበት አሜሪካዊው የፊልም ተዋናይና እግር ካስ ተጫዋች ኦጄ ሲምፕሰን ከዘጠኝ ዓመታት እስር በሃላ ዛሬ በምህረት መፈታቱን የዛሬይቱ አሜሪካ [USA Today]ድረ-ገጽ ዘገበ።

ኦጂ ሲምፕሰን በ2007 ላይ ከአምስት ግብረ አበሮቹ ጋር ሆኖ በ1994 የግድያ ወንጀል ጋር ንክኪነት ያለውን ፋይል በኔቫዳ ሆቴል ዘረፋ በመፈጸሙ የ33 ዓመት እስራት እንደተፈረደበት ይታወቃል።

በ1994 የቀድሞ ባለቤቱ ኒኮል ብራውን እና ፍቅረኛዋ ሮናልድ ጎልድማን ክስ መጀመሪያ ፍርድ ቤቱ ነጻ ያሰናበተው ቢሆንም መልሶ ግን በ1997ላይ ኦጄን ጥፋተኞች በማድረግ ለማች ቤተሰቦች ካሳ የ33.5ሚሊዮን ዶላር ክፍያ እንዲከፍል መደረጉ አይዘነጋም።

የ75ዓመቱ ኦጄ ሲምፕሰን ወደ ፍሎሪዳ እስቴት እንዲሄድ ያልተፈቀደለት መሆኑን እና እስከ 2022 የሚዘልቅ የግዜ ገደብ እንደተጣለበት መረዳት ተችላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.