በጣና ፀረ – አረም ገንዘብ ማሰባሰብ ዙሪያ የተደረገው የፋሲል ጊዎርጊስና የእንቦጭ ጨዋታ በፋሲል ጊወርጊስ ከፍተኛ አሸናፊነት ተጠናቋል

 በጣና ፀረ – አረም ገንዘብ ማሰባሰብ ዙሪያ የተደረገው የፋሲል ጊዎርጊስና የእንቦጭ ጨዋታ በፋሲል ጊወርጊስ ከፍተኛ አሸናፊነት ተጠናቋል። ዳኝነቱን በበላይነት የመረው ጣና ሲሆን ይህ ቅዱስ ተግባር እንደሚቀጥል ታውቋል። –Gashaw Agegne
አረምን ለመንቀል ከእሁድ ጀምሮ በባህር ዳር የከተመው
የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዋች
በቦታው ላይ ተገኝተው አረምን በመንቀል
ተግባራቸውን አስመስክረዋል
እኛም በዚህ ድንቅ ተግባራችሁ ተደምመናል ምስጋናም ልከናል ይሄ ትውልድ በኢትዮጵያ ያለ ማንኛውም አረም እንደማያሸንፈው በተግባር አሳይቶል ።
እጅ ነስተናል–Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia

ጉድ እኮነው በ40 ካሚዮኖች የአጼ ዎቹ ደጋፊዎች ወደ ውቢቱ ባህርዳር ነጎዱ። የሚገርመው ደግሞ የድፍን ጎንደር ልብ ከአጼዎቹ ጋር መሆኑ ነው። ክብር ለልዑላኖቻችን አጼዎች። ልያ ፋንታ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ወቅት ነው። ባህር ዳር። ይሄ ሁሉ ታጣቂ ስታዲየም ዉስጥ ምንድን ነው የሚሰራው ? እነርሱማ “ሰላም ለማስጠበቅ ነው” ባዮች ናቸው። ሕዝቡ ግን ድሮም ሰላማዊ ነው። ዛሬም ሰላማዊ ነበር። ወደፊት ሰላማዊ ነው። እነርሱ ናቸው ሰላም አደፍራሾች፣ ሰውን አላስቀምጥ አላስወጣ የሚሉት !!!!!! ምን ያህል ሰው እንደጠላቸውና እነርሱን ማየት እንደማይፈልግ መቼ እንደሚረዱ አይገባኝም !!!!

 ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
_________________________
በኢትዮጵያ ውስጥ በትልቅነቱ፣ በታሪካዊ መስህብነቱ እና የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልብ የሚስበው ታላቁ የጣና ሀይቅ በእንቦጭ አረም ወረርሽኝ ህልውናው በከፍተኛ አደጋ ላይ መውደቁ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ይህንንም ታሳቢ በማድረግ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብና የአምናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በባህር ዳር ከተማ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ መስከረም 21 ቀን 2010 ዓ/ም ቀጠሮ መያዛቸው ይታዎሳል፡፡
ጨዋታው እንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚደረገው ዘመቻ አንዱ አካል ሲሆን በመጭው እሁድ የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎችና ተጫዋቾች በተገኙበት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለገብ ስታዲየም ይደረጋል፡፡ጣና ሐይቅን ከእንቦጭ እንታደግ የወዳጅነት ጨዋታ
Amanuel Paramera

በጣናው ሞገድ እና በአፄዎቹ መካከል የወንድማማችነት መንፈስ እጅግ ያስቀናል

አጀይብ ደጋፊ
አጀይብ ከተማ
አጀይብ ህዝብ

የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊ ነኝ፣
የሁለቱም አርማ ልቤን “ዘጭ” ያደርገዋል፣

በጣም ወደ ምወዳት ከተማ ባህርዳር ጎራ ብለው በሚያምር ድባባቸው ከተማዋን ሞሸሯት። ጣና አይሞትም የሚለው የወጣቶች መፈክር እውን ይሆናል።

የባህርዳር ከተማ ደጋፊዎች ያደረጉት አቀባበል አጀይብ ነው።

እንኳን ደህና መጣችሁ ፈረሰኞቹ፣
እንኳን ደህና መጣችሁ አፄዎቹ፣
እወዳችሗለሁ እንደ ቹቹ!!

እንግዲህ አፄዎቹ በጣና ላይ ያንዣበበውን እምቦጭ አረም ላይ እየሰነዘሩት ያለውን ጥቃት በድል ለመወጣት ዛሬም ከአቻው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ እንዲህ በሚያስደምም ሁኔታ አየገሰገሰ ይገኛል።የጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከነማም እነሆ ከውቢቷ ባሕርዳር ወጣ ብላ በእጭር ርቀት ላይ በምትገኛው ዘንዘልማ ከተማ ላይ በመገኘት የደመቀ አቀባበል አድርገዋል። በጣናው ሞገድ እና በአፄዎቹ መካከል የወንድማማችነት መንፈስ እጅግ ያስቀናል።

 

 

የብአዴን አመራሮች ቀፈታቸው በተወጠረ ቁጥር የሚጨምረውን ኮሌስትሮል በዘመቻ ለመቀነስ ለሚያደርጉት የጤና ስፓርታዊ ጨዋታ የሚከፈት ይሆናል::
ጣና እንዲህ ታሞ ባለበት ሁኔታ ለገቢ ማሰባሰቢያ ለሚደረግ የእግር ኳስ ጨዋታ ይህን ‘የስፓርት ማዘውተሪያ’ በተልካሻ ምክንያት አልፈቅድም ማለቱ ለህዝቡ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ያሳየበት ክስተት ነው:

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.